Accessibility links

Breaking News

የሰሜን ኮሪያ የሚሳዬል ሙከራ አደጋ ደቀኗል


ዩናይትድ ስቴትስ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊት ሪፐበሊክ ኮሪያ በቅርቡ ያደረገቸውን የባለስቲክ ሚሳዬል ሙከራ አውግዛለች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ እንዲህ ብለዋል

እነዚህ የሚሳዬል ሙከራዎች በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የተቀመጡ ውሳኔዎችን የሚጥሱ ፣ በህዝባዊ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮሪያ አጎራባች አገሮችና ለሌሎች የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አባላት አደጋ መደቀናቸውን እናውቃለን”

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጆን ከርቢም እንዲህ ይላሉ

“እነዚህ እንቃስቃሴዎች አለመረጋጋት ፈጣሪ የሆነውን የሰሜን ኮሪያን የጦር መሳሪያ መርሃ ግብር ተጽእኖ በግልጽ ያሳያሉ የደቡብ ኮሪያ ሪበሊክና ጃፓንን ከጥቃት ለመከላከል ያንን ቁርጠኝነት እንደ ብረት የጠነከረ ሆኖ ይቀጥላል፡፡”

በሰሜን ኮሪያ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለው የኒዩክለር ስምምነት ድርድሮች እኤአ ከ2019 ጀምሮ ተቋርጠዋል፡፡ ይሁን እንጂ የባይደን አስተዳደር ግን እንደገና ለማደስ ፍላጎቶቹን ግልጽ አድርጓል፡፡

የውጭ ግዳይ ሚኒስትሩ ኔድ ፕራይስ ስለዚሁ ሲናገሩ ይህን ብለዋል

“እኛ አሁንም ቢሆን መነጋገር ዋነኛ ግባችንን ለማስፈጸም ያስችለናል በሚለው መርሃችን ጸንተናል፡፡ ያም በቀላሉ የኮርያን ባህረ ገብ አካባቢ ከኒዩክለር ነጻ ማድረግ ነው፡፡ በህዝባዊ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮሪያ ጋር ጠላትነት የለንም፡፡”

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በዩናይትድ ስቴትስና በአካባቢው ባሉ አገሮች መካከልም ሰሜን ኮሪያን ዋነኛ መነጋገሪያ አጀንዳ ያደረገ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴዎች ብዙ ናቸው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፕራይስ “እነዚህ ስብሰባዎች የዩናይትድ ስቴትስ ተሳትፎና ዲፕሎማሲ የቱን ያህል አስፈላጊ መሆናቸውን ያሳያሉ” ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ እንዲህ ብለዋል፡፡

እኛ ማድረግ የምንፈልገው በዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ በአካባቢ ባሉ አጋሮቻችን ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመቀነስ ነው፡፡ ያንን ደግሞ እናስፈጽማለን ብለን የምናስበው በዴፕሎማሲ አማካይነት ነው፡፡

XS
SM
MD
LG