Accessibility links

Breaking News

በሱዳን የሲቪል መር መንግሥትን በቦታው እንዲመለስ መርዳት


እኤአ ጥቅምት 2021 የሱዳን ሲቪል መር የሽግግር መንግሥትን በመገልበጥ የተደረገው ወታደራዊ እርምጃ ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገው ለውጥ ችግር ላይ መሆኑን ያሳያል ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ እና እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት የፖሊሲና መርኃ ግብር ረዳት አስተድደር ኢዛቤል ኮልማን በቅርቡ በህግ መወሰኛው ምክር ቤት ፊት ቀርበው በሰጡት ምስክርነት ተናግረዋል፡፡

ረዳት ሚኒስትሯ ሞሊ ፊ በምስክርነታቸው “በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተወጣጡ ሱዳናውያን ወደ አደባባዮች በመውጣት ራሳቸውን በአደጋ አጋልጠው የሲቪል አስተዳደርና ዴሞክራሲ ጥያቄ በማንሳት ትግላቸውን መቀጠላቸውን እናደንቃለን” ብለዋል፡፡

ረዳት አስተዳዳሪው ኮለምን ጨምረው እንደገለጹት “በሺዎች የሚቆጠሩ ጀግ ኖቹ ዜጎች በየቀኑ በሚባል ደረጃ ህይወታቸውን ለአደጋ በማጋለጥ ለበርካታ ዓመታት ሊገዛቸው የሚያስፈራራቸውንና በሙስና የተሞላው ወታደራዊ አገዛዝ እንዲወገድ እየጣሩ ነው፡፡” በማለት ተናገረዋል፡፡

በሱዳን ሰላማዊ ዜጎች ተነሳሽነት እኤአ 2018 የተነሳሳው አብዮት ተከትሎ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የሱዳንን ዴሞክራሲያው ሽግግር በመደገፍ ትልቁን እርዳታ የሚያበረክት ሆኗል፡፡ ይህ እርዳታ ቁልፍ የሆኑ የፖለቲካና የምጣኔ ሀብት ተሀድሶዎችን በማምጣት ለሱዳን ህዝብ የሲቪል መር የሆነው ሽሽግግር መንግሥት አማካይነት የሚመሰረተው ዴሞክራሲ ለወደፊቱ አዋጭና ዘላቂ የሆነ ስርዐት የሚያመጣ መሆኑን ለማሳየት ነው ብለዋል፡፡

የወታደሩ ክፍል ለህዝቡ የገባውን ቃሉን ካፈረሰ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ ልትሰጥ የሚገባትን የ700 ሚሊዮን ዶላር የእርዳታ ገንዘብ ለጊዜው እንዲገታ ማድረጓን አስታውቋለች፡፡

የሱዳን ህዝብ ራሱን ለወደፊቱ ለማልማት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመርዳት ዩኤስ ኤ አይዲ የሱዳን ዴሞክራሲ ሽግግርን ለመደገፍ የሚያደርገውን ጥረት በሶስት ዋና ዋና ዘርፎች ይቀጥላል፡፡ የሲቪል ዜጎችን የፖለቲካ አመራር ማጠናከር፣ ሀሳብን በነጻነት መግለጽና የመሰብሰብ ነጻነትን ጨምሮ የሰብአዊ መብቶችን ክብር ማሳደግ እና ፤ በፖለቲካና ምጣኔ ሀብት ላይ ያለውን ረጅም ጊዜ የቆየውን የሱዳን ወታደራዊ አገዛዝ ተጽእኖ እንዲያበቃ የሱዳን ህዝብ የጠየቀውን ጥያቄ መደገፍ ናቸው፡፡

ይህ ባለበት ሁኔታ ውስጥም የሱዳን ህዝብ የሚያስፈልገው የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት አሁንም እየጨመረ ነው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት እንደገመተው በሱዳን ወደ 14.3 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ ወይም ወደ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ህዝብ እኤአ በ2022 የሚፈልገው ሰብአዊ እርዳታ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በሰባት ከመቶ ጨምሯል፡፡ ይህ ለህይወት አስጊ በሆነ ደረጃ በሚገኝ የምግብ እጥረት የተጎዳውን ወደ 9.8 ሚሊዮን የሚመገተውን ህዝብ ይጨምራል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ለሱዳን ህዝብ ለረጅም ጊዜ ትልቁን የሰብአዊ እርዳታ ከሚለግሱት አገሮች አንዷ ናት፡፡ እኤአ በ2021 እና 2022 የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ለስደተኞች መሠረታዊ ፍላጎት ለማሟላት፣ ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮችና የውጭ ተፈናቃዮችን ለሚያስተናግዱ የህብረተሰብ ክፍሎችና ሌሎች 429 ሚሊዮን ዶላር መድቧል፡፡ ዩናይትይድ ስቴትስ የሱዳንን ህዝብ መጠነ ሰፊ ፍላጎት ለማሟላት ሌሎች ለጋሾችም እነዚህን ጥረቶች እንዲያግዙ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የሱዳን ህዝብ ለነጻነት፣ ለሰላምና ለፍትህ ያለውን ፍላጎትና ጥማት እንዲሟላ ለመርዳት ያላት ዓላማና ግብ አሁንም ይቀጥላል፡፡

XS
SM
MD
LG