Accessibility links

Breaking News

በዓለም የአየር ንብረት ቀውስ ማሻሻያዎችና ቀጣይ ትግበራዎች


ባላፈው ህዳር የተደረገው እኤአ የ2021 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ፣ ወይም COP26፣ በእኤአ በ2015 በፓሪሱ ስምምነት ወደ ተደረሰባቸው ግቦች ለመቃረብ ትልቅ ግፊት አድርጓል፡፡

በአየር ንብረት ላይ የደረሰውን ቀውስ በአስቸኳይ ለመፍታት፣ ነፍሳትንና ህይወትን በመታደግ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሥራ እድሎችን እንዲሁም ጤናማና ንጽሁ ዓለምን ለመፍጠር፣ የገባውን ቃል መፈጸም የዓለም ማህረሰብ ድርሻ ነው፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ወይም COP26፣ ወደ 200 የሚጠጉ አገሮች አንድ ላይ እንዲመጡ አድርጓል፡፡ ይህም የዓለምን የሙቀት መጠን በ1.5 ዲግሪ ሴልሸስ ዝቅ ለማድረግ እንዲሁም የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ልቀትን እኤአ እስከ 2030 ድረስ በ45 ከመቶ በመቀነስ፣ በመቶኛው አጋማሽ ዓመት ልቀቱን ወደ ዜሮ ማውረደና ሌሎቹን የግሪን ሀውስ ጋዝ ልቀትና በሚገባ መቀነስን ይመለከታል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የፕሬዚዳንቱ ልዩ የአየር ንብረት ልዑክ ጆን ኬሪ ባለፈው ህዳር፣ ግብጽ ሻርም ኤል ሼክ ውስጥ በተደረገው የCOP27 ጉባኤ ሲናገሩ “አሁን እነዚያን “ቢሆኖች” ወደ ተፈጻሚ ትዕዛዞች ለመቀየር በዝግጅት ላይ ነን” ብለው ነበር፡፡

ጆን ኬሪ የአዳዲሶቹ ተጨማሪው የተፈጻሚ እቅድ የመጣውም እዚህጋ ነው ካሉ በኋላ፡ “ይህ ማለት የተገባውን ቃል መተግበር፣ ያልጠነከሩ ቁርጠኝነቶችን ማጠንከር፣ እንዲሁም እቅዶቹ ጨርሶ በሌሉበት ቦታ ደግሞ አዳዲስ ቁርጠኝነቶችና ጥረቶች መፍጠር ናቸው፡፡”ብለዋል፡፡

65 ከመቶ የሚሆነውን የዓለም አገር ውስጥ ምርቶች የሚያቀርቡት 1.5 ዲግሪ ሴልሽየስ እንዲሆን የገቡትን ቃል ለመጠበቅ ተስማምተዋል፡፡ እነዚያ አገሮች የገቡትን ቃል ተፈጻሚ የሚያደርጉበትም ጊዜ አሁን ነው፡፡

የስሌቱ ተጨማሪ ክፍል እንደሚያመለክተው ከዚያ ውስጥ 35 ከመቶ የሚሆን የምጣኔ ሀብት ድርሻ ያላቸው፣ ሳይንቲስቶቹ እንደሚሉት የህልውናን መቀጠል ለማረጋገጥ አብረው መሰለፍ ይኖርባቸዋል፡፡

ጆን ኬሪ “እውነታው ተፈጻሚ መሆን የሚገባቸው ሌሎች ቃል የተገቡ በርካታ ነገሮች መኖራቸው ነው” ይላሉ፡፡ “ከእነዚህ መካከል በዓለም፣ የዓለም አቀፍ የሜቴይን መጠነን ለመቀነስ የተገባው ቃል፣ እንዲሁም የዚሮ ልቀትና የቅሬተ አካል ነዳጅ ቅነሳ እንዲቆም የደን ጭፍጨፋ እንዲያበቃና በተገባው ቃል ላይ አገሮች ሌላ ተጨማሪ ቃል እንዲገቡ ይጠይቃል” ብለዋል ፡፡

በተጨማሪም ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችና ማህበረሰቦችን ዓለም እንዲጠብቃቸው ጆን ኬሪ ጥሪ አድርገዋል፡፡

“በብዙ ቦታዎች ነገሮች በተለደመው መልኩ ቀጥለዋል፡፡” ያሉት ኬሪ “ሰዎች በመጨረሻ ላይ የሚደረገውን መረባረብ መርጠዋል፡፡ ይህን ማቆም አለብን፡፡ ካሁን በኋላ ከገጠሙን ከባድ አደጋዎች አንጻር እንደወትሮው በተለመደው መንገድ ዝምብን ለመሄድ አንችልም” ብለዋል፡፡

አይያዘውም “አሁን ፍኖተ ካርታ አለ፣ እሱን ብቻ መከተል ይኖርብናል” በማለት “የምናደርገውና የማናደርገውን ነገር መወሰን የሁላችንም ኃላፊነት ይሆናል፡” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG