Accessibility links

Breaking News

በሱዳን የዝግታ እርምጃዎች ወደፊት ማራመድ ይዘዋል


በጊዜው ሱዳንን ይመሩ የነበሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ከሥልጣን ከተወገዱበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2019 ወዲህ ባለፉት አራት ዓመታት፤ በሁለት የማይመስሉ የፖለቲካ ዝምድናዎች እና ወታደራዊው ኃይል ሥልጣኑን በሙሉ ጠቅሎ ከወሰደበት፣ ለአጭር ጊዜ የዘለቀውን የሥልጣን መጋራት ሥምምነት ተከትሎ ሁለት ዓመታት በኋላ፤ በመጨረሻው ነገሮች በዚያች አገር መልካም አዝማሚያ መታየት ጀምረዋል።” ሲል ይንደረደራል በሱዳን በዝግታ የተወሰዱ እርምጃዎች ወደፊት ማራመድ ጀመሩ ያለው የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ።

ከአዎንታዊ እርምጃዎቹም መካከል የመጀመሪያው አንዱ ባለፈው የሚያዝያ ወር አሊ ኩሻይብ በሚለው መጠሪያቸው ይበልጥ የሚታወቁት አሊ ሙሐመድ አሊ አብደልራህማን ለፍርድ የቀረቡበት የሕግ ሂደት ሲሆን፤ በሱዳን መንግሥት የሚደገፈው ጃንጃዊድ የሚሊሻ ቡድን ከፍተኛ መሪ የነበሩት አሊ ኩሻይብ በሱዳን ዳርፉር ግዛት የተካሄደውን ሕዝባዊ አመጽ ለመግታት በሰብአዊነት ላይ በተፈጸመ ወንጀል እና ከፍተኛ ጭካኔ የተመላ የጦር ወንጀል ይጠየቃሉ።

ርዕሰ አንቀጹ አያይዞም በመንግሥታቱ ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ ልዑክ የህግ አማካሪ ማርክ ሲሞንኦፍ "ይህ ለሱዳን የወደፊት ዕጣ ወሳኝ ጊዜ ነው" ሲሉ የተናገሩትን ያስታውሳል።

“ይህ ልዩ ሥፍራ የሚሰጠው ትልቅ ጉዳይ ነው። በኦማር አልበሽር መንግሥት ውስጥ የነበረ አንድ ከፍተኛ ባለ ሥልጣን እና በዳርፉር በመንግሥት የተደገፉ ኃይሎች ለፈጸሙት በደል ተጠያቂ ሲደረጉ ለማየት፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በዳርፉር በተፈጸሙት ጥቃቶች ሰለባ የሆኑ ዜጎች ትክክለኛ ፍትህ የሚያገኙበት የመጀመሪያው እድል ነው።”

“ሌላው የአዎንታዊ እንቅስቃሴው ማሳያ” ርዕሰ አንቀጹ ይቀጥላል። “ሌላው የአዎንታዊ እንቅስቃሴው ማሳያ፡ በአውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር ባለፈው ታሕሳስ 5 የተፈረመው የፖለቲካ ማዕቀፍ ሥምምነት ነው። ይህ በወታደራዊ ገዥዎች እና በሲቪል ኃይሎች መካከል የተደሰ ሥምምነት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2019ዓም የአልበሽርን መንግሥት ከሥልጣን በማስወገድ የተጀመረው በጥቅምት 2021 ዓም በወታደራዊው መንግሥት ከተደናቀፈ በኋላ በሱዳን ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ለመመስረት የተደረገው ጥረት አስፈላጊ የመጀመሪያ እርምጃ ነው።

“ይህ ሥምምነት እና የሲቪል መንግሥት ለመመስረት ከሚያስችል አንዳች የመቋጫ ሥምምነት ላይ ለመድረስ ታልሞ በቅርቡ የተጀመረው ውይይት ሁለተኛ እርከን፣ ተስፋ ሰጪ እርምጃ ነው። እነዚህ ድርድሮች መካሄዳቸው በራሱም ሱዳናውያን ሴቶች፣ ወንዶች እና ወጣቶች በሱዳን የጸጥታ ኃይሎች ብርቱ ጥቃት ቢደርስባቸውም፤

መብታቸውን ለማስከበር እና ብሎም የሲቪል አስተዳደር እውን ይሆን ዘንድ ለመጠየቅ፣ አደባባይ ወጥተው ያሳዩት ጽናትና ቆራጥነት ምስክር ነው።”

ቡድኖቹ በእነዚህ የሁለተኛ ዙር ውይይቶች እና በአንዳንድ ያልተፈቱ ጉዳዮች ላይ በመነጋገር ላይ ባሉበት ባሁኑ ወቅት፤ አንዳንዶቹ ብርቱ ፈተናዎች አሁንም ከፊታቸው እንደተደቀኑ መሆናቸውን የጠቀሰው ርዕሰ አንቀጽ፣ “ይህም ሱዳን በፌዴሬሽን መልክ የምትቋቋምበትን ሥርዓት የሚደነግገውን የጁባውን የሰላም ሥምምነት እና እንዲሁም የሽግግር ፍትህ እና የጸጥታ ዘርፍ ማሻሻያ ጥያቄዎችን ይጨምራል።” ብሏል።

"በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ፣ የሽግግር ፍትህ ዕውን መሆንን ጨምሮ ‘ለበርካታ አስርት አመታት በተፈጸሙ የኃይል እርምጃዎች ተጠያቂነት እና ፍትህ ሊረጋገጥ፣ እርቅና የደረሰው ቁስልስ እንዴት ማጠገግ ይችላል?’ የሚሉትን ጨምሮ ከሱዳን ህዝብ ጎን መቆማችንን እንቀጥላለለን” ሲሉ ሚስተር ሲሞኖፍ የተናገሩትን ጠቅሶ የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ ሃተታውን ደምድሟል።

XS
SM
MD
LG