“ዛሬ እአአ ሰኔ አሥራ ዘጠኝ (Juneteent እየተባለ የሚጠራው) ቀን ነው፡፡ ይህ ዕለት አፍሪካ አሜሪካውያን ከ150 ዓመታት በላይ ያከብሩት የነበረ ሲሆን፣ አሁን በቅርቡ ብሔራዊ በዓል ሆኖ እውቅና አግኝቷል።” ይላል የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ ጽሁፉን ሲጀምር፡፡
“ጁንቲንዝ በእንግሊዝኛው ሰኔ እና አስራ ዘጠኝ (June እና Nineteenth) የሚሉት ቃላት የተጣመሩበት ነው፡፡ ዕለቱ እኤአ በ1865 በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በባርነት ስር የነበሩ የመጨረሻዎቹ አፍሪካ አሜሪካውያን፣ ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ ነፃ መውጣታቸውን የተረዱበት ቀን ነው።” ሲልም ርዕሰ አንቀጹ ያስረዳል፡፡
ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠል “እአአ ጥር 1/ 1863 ፕሬዝደንት አብርሃም ሊንከን፣ በአመጸኞቹ የኮንፌዴሬሽን ግዛቶች ውስጥ፣ በባርነት የተያዙ ሰዎች ሁሉ ነፃ ናቸው ሲሉ” የነጻነት አዋጅ አወጡ። ስለዚህ በህጉ፣ በባርነት የተያዙ ሰዎች በወቅቱ ነፃ የነበሩ ቢሆንም በተፈጠሩት ሁኔታዎች ምክንያት፣ ቃሉ በየቦታው ለመሰራጨት አዝግሞ ነበር። ስለዚህ አስደሳች ዜናው ራቅ ብለው በመገለል ወደ ሚገኙት ወደ ተሸነፉትና የኮንፈደሬሽን አካባቢዎች የተሰራጨው የእርስ በርስ ጦርነቱ ካበቃ ሁለት ወራት በኋላ ነበር” ሲል ርዕሰ አንቀጹ አስፍሯል፡፡”
“እአአ ከ1866 ዓ.ም ጀምሮ ሰኔ 19 (Juneteenth) በአፍሪካ አሜሪካዊያን ማህበረሰብ ሲከበር ቆይቷል።” ያለው ርዕሰ አንቀጽ “Juneteenth በይፋ እንዲከበር እውቅና ለማግኘት ግን ሌላ 155 ዓመታትን ፈጅቷል።” ብሏል፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ ፣ እዚህ ለመድረስ ረጅም ጊዜ ተጉዟል፡፡ ይሁን እንጂ እኤአ ሰኔ 17፣ 2021፣ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እአአ ሰኔ 19 (Juneteenth) እንደ ፌደራል በዓል ሆኖ እንዲከበር የሚያስችለውን ህግ ፈርመዋል።” በማለት ጽሁፉ አትቷል፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደን ባለፈው ዓመት በተከበረው የሙዚቃ ድግስ ላይ "ለእኔ ሰኔን አስራ ዘጠኝ የፌዴራል በዓል ማድረግ ተምሳሌታዊ ምልክት ብቻ አልነበረም" ማለታቸውን ርዕሰ አንቀጹ ጠቅሷል ።
ባይደን “ለዚህች አገር…ለመጀመሪያው የባርነት ኃጢአት እውቅና መስጠቱ ትክከለኛ መግለጫ ነበር። … የነጻነት አዋጁን ሰነድ ማስታወስ ብቻ አልነበረም። አገሪቱን ያነቃነቀውን የነፃነት ምንነት ያያዘ ነው። አንዳንድ ሃሳቦች የበለጠ ኃይለኛ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡ ሊከለከሉ አይችሉም፡፡ የአሜሪካ የተስፋ ቃል፣ እኛ ሁላችንም በእግዚአብሔር አምሳል እኩል የተፈጠርን መሆናችንን እና በህይወታችን በሙሉ እኩል ልንስተናገድ የሚገባን መሆኑን የሚያስታውስ ነው።” ብለዋል፡፡
ባይደን በመቀጠል ዩናይትድ ስቴትስ “የተመሰረተችው በአንድ ሀሳብ ላይ ነው። በዓለም ላይ ካሉት ከማናቸዉም ሀገራት በተለየ መልኩ፣ እነዚህ እውነቶች ሁሉም ወንዶች እና ሴቶች እኩል እንደተፈጠሩ እና በፈጣሪያቸው የማይገፈፉ መብቶች እንደተጎናፀፉ እንድንገነዘብ ያደረግን ሀሳብ ነው” ማለታቸውን ጠቅሷል፡፡
ባይደን አያይዘውም "ይህን የተስፋ ቃል ሙሉ በሙሉ ባናከብርም፣ ከሱም ደግሞ ርቀን አናውቅም። ያለፉት ጥቂት ዓመታት እንደሚያስታውሰን፣ አሁንም በጣም ኃይለኛ በሆነው ዘረኝነት ነፃነታችን አደጋ ላይ ወድቋል” ሲሉ መናገራቸው ጽሁፍ ጠቅሷል፡፡
በመጨረሻም ባይደን “እአአ ሰኔ 19 እንደ ፌደራል በዓል ይከበራል ሲባል፣ ሁሉም አሜሪካውያን የዚህን ቀን ኃይል እንዲረዱ ለማረጋገጥ እና እንደ ሀገር ልናደርገው የምንችለው ለውጥ እንዲሰማቸው ለማድረግ፣ በአሜሪካ መሰረታዊ ማንነት አዲስ እስትንፋስ እንዲኖር ለማድረግ ነው።” ብለዋል ሲል ርዕስ አንቀጹ ጽሁፉን ደምድሟል፡፡