Accessibility links

Breaking News

ጸረ አደንዛዥ እጽ ዝውውር ውጊያ በላይቤሪያና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች


የእስያ እና ደቡብ አሜሪካ አደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎች፣ ከሰሀራ በታች ያሉትን የአፍሪካ አገሮችን ውስን የመሰረተ ልማት አውታሮችን በመጠቀም፣ አደንዛዥ እጾቻቸውን ያለምንም ችግር የሚያስተላለፉባቸው መንገዶች አድርገዋቸዋል፡፡ ይላል የእለቱ ርእሰ አንቀጽ ሀተታውን ሲጀምር፡፡ እኤአ በ2019 ሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ፣ በጊኒ ቢሳዎና፣ በካቦ ቨርዴ ውስጥ፣ የተያዘው የኮኬይን የአደንዛዥ እጽ ብዛት፣ እኤአ ከ2013 እስከ 2016 ካለው ጊዜ፣ ከተያዘው ጠቅላላ ድምር በብዛት ይበልጣል፣ ብሏል ርእሰ አንቀጹ፡፡

የዩናትይድ ስቴትስ መንግሥት፣ እያደገ የመጣውን ይህን አደጋ መከላከል የሚያስችሉ፣ የተለያዩ የመከታተያ መሳሪያዎችና ፣ ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን፣ ለላይቤሪያ የደህንነትና ህግ አስከባሪ አካላት በመለገስ እየረዳ መሆኑንም፣ ርእሰ አንቀጹ አስታውቋል፡፡ በቅርቡም ፣የላይቤሪያ የአደንዛዥ እጽ መቆጣጠሪያና መከላከያ ኤጀንሲ ወይም (ሌዳ)፣ የአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎችን ለመዋጋት የሚረዱ፣ የተለያዩ የደንብ ልብሶችን፣ የቦት ጫማዎችን፣ የእጅ ጓንቶችን፣ ላፕቶፖችን፣ ማተሚያና የመሳሰሉ አቅርቦቶችን የተቀበለ መሆኑን ገልጿል፡፡

በላይቤሪያ የአሜሪካ የኤምባሲ፣ የዓለም አቀፍ የአደንዛዥ እጽና፣ የህግ ማስከበር ጉዳዮች ክፍል ፣ ተጠባባቂ ድሬክተር ስቲፌን ኤች ኪሲክ “የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት፣ ከሌዳ ጋር፣ ለብዙ ዓመታት አጋር በመሆን እስካሁን ቆይቷል፡፡” ብለዋል፡፡

ፍሮንት ፔጅ አፍሪካ ከተባለው የላይቤሪያ ጋዜጣ ጋር በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ ስቴፈን ዩናትድ ስቴትስ “ከላይቤሪያ መንግሥት ጋር የጀመረችውን ሥራ፣ ለወደፊቱም ልትቀጥልበት ትፈልጋለች” ማለታቸውን ርእሰ አንቀጹ አመልክቷል፡፡ ኬንያ፣ ጋና እና ሌሎች የአፍሪካ አገሮችም፣ የአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎችና ከነሱም ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩ ችግሮችን ለማስወገድ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በትብብር ይሰራሉ፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የቀድሞ የዓለም አቀፍ አደንዛዥ እጽ ዝውውርና ህግ የማስከበር ጉዳዮች ቢሮ፣ ረዳት ጸሀፊ የነበሩት፣ ሄዘር ሜሪት፣ በቅርቡ እንደተናገሩት፣ ዩናይትድ ስቴት፣ በአፍሪካ የአደንዛዥ ዕጽ አስተላላፊዎችን ለመዋጋት፣ ብዙ ኢንቨስት ያደረገች ስትሆን፣ ዴሞክራሲን ከሚያራምዱ የአፍሪካ መንግስታትም ጋር፣ ትብብሯን የበለጠ ለማስፋት፣ ተስፋ ታደርጋለች ብለዋል፡፡

“እነዚያን የአደንዛዥ እጽ አስተላላፊ ድርጅቶችና ሌሎች መሰል ወንጀለኞችን ከሚዋጉት ጋር አብሮ መስራት፣ የዩናትድ ስቴትስ ፍላጎት ነው፡፡ ምክንያቱም የዴሞክራሲን ፈለግ የሚከተሉ የአፍሪካ አገሮች፣ ደህንነትና ብልጽግናቸው የተጠበቀ እንዲሆን እንፈልጋለን፡፡” ብለዋል፡፡ ሄዘር ሜሪት አስከትለውም የሚከተለውን ብለዋል፣

“የንግድ ፍሰት እንዲኖር እንፈልጋለን፡፡ የሰዎች ለሰዎች ትብብር እንዲኖር እንሻለን፡፡ እኛ የተሻለና ጠንካሮች የምንሆነው በወዲያኛው በኩል ያለው አጋራችንም ሙሉ አቅም ሲኖረው ነው፡፡”

አገራት በአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪ ወንጀለኛ ድርጅቶች ሲበዘበዙ፣ እነሱን ተክትለው የሚመጡ ጥቃቶችና ሙስናዎች፣ የመንግስታትን ህጋዊነትና ጥንካሬ በመፈታተን ህዝቦችን ለአደጋ ያጋልጣሉ፡፡

ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠልም፣ የአፍሪካ መንግሥታትን በመርዳት፣ ከእነዚህ የአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎች ከሚያስከትሉት ችግሮች ቀድሞ መገኘት ይቻላል፡፡ ይህን ማድረግም፣ እንደሙስናና ወንጀል የመሳሰሉትን ሌሎች ችግሮችንም ለመቀነስ እንደሚያስችል ዩናይትድ ስቴትስ ትገነዘባለች ብሏል፡፡

በመጨረሻም፣ ምክትል ረዳት ጸሃፊዋ፣ “የዓለም አቀፍ አደንዛዥ እጽ ዝውውርና ህግ የማስከበር ጉዳዮች፣ በአህጉሪቱ ባሉ ኤምባሲዎቻችን አማካይነት፣ ከአፍሪካ መንግስታት ጋር በመተባበር፣ የወንጀል ህግ ተቋሞቻቸውንናአቅም ለማሳደግ ይሠራል ማለታቸውን በመጥቀስ ርእሰ አንቀጹ ሀተታውን ደምድሟል፡፡

XS
SM
MD
LG