Accessibility links

Breaking News

የሩስያው ተቃዋሚ መሪ አለክሰይ ናቫልኒ፣ ከኮማ መውጣት


ፎቶ ፋይል፦አለክሰይ ናቫልኒ
ፎቶ ፋይል፦አለክሰይ ናቫልኒ

የሩስያው ተቃዋሚ መሪ አለክሰይ ናቫልኒ፣ ከኮማ ወጥተው ለመናገር እንዲችሉ ለሚደረገው ጥረት፤ ምላሽ ለመስጠት እየቻሉ መሆናቸውን፣ የበርሊን ሃኪሞቻቸው ተናግረዋል። ይህ መልካም ወሬ ነው ሲል፣ የዛሬው ርዕሰ አንቅፅ ሃተታውን ይጀመራል።

የናቫልኒ ሃኪሞች ህይወታቸውን ስተው ኮማ ውስጥ እንዲገቡ ያደረጉት፣ ለህክምናቸው አስፋላጊ ስለሆነ እንደሆነ ተገልጿል። ያም ሆኖ ግን የደረሰባቸው ከባድ መመረዝ፣ ለወደፊቱ ሊያደርስባቸው ስለሚችል ጉዳት ለመናገር ገና መሆኑን፣ የሚታከሙበት ሆስፒታል ባወጣው መለጫ ማስጠንቀቁ እንዳልቀረ ርዕሰ አንቀጹ አውስቷል።

ሚስተር ናቫልኒ ከሩስያ ወደ በርሊን የተወሰዱት፣ እአአ ነሃሴ 20 ከሳይቤርያ ወደ ሞስኮ በአውሮፕላን ሲጓዙ በመታመማቸው ነው። የበሽተኛው ቤተሰብ በጠየቀው መሰረት፣ የሩስያ ሀኪሞች በርሊን ሄደው እንዲታከሙ መፍቀዳቸውን፣ ርዕሰ አንቀጹ ገልጿል።

የበርሊን ሃኪሞች ታድያ፣ ናቫልኒ ኖቪቾክ የተባለው የኬሚካል መሳርያ አካል በሆነ የነርቭ ኤጀንት እንደተመረዙ ተናግረዋል። ኖቪቾክ በሩስያ የሚሰራ የኬሚካል መሳርያ ነው። ሚስተር ናቫልኒ የሩስያውን ፕረዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲንን፣ አጥብቀው ሲነቅፉ የቆዩ የተቃውሞ መሪ ናቸው።

የጀርመን የህክምና ጠቢባን ናቫልኒ መመረዛችውን ካስታወቁ በኋላ፣ ሩስያ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ጆን ሱሌቫን፣ የሩስያ ባለሥልጣኖች ለድርጊቱ ተጠያቂ በሆኑት ሰዎች ላይ፣ “አሁኑኑ የተሟላና ግልፅ ምርመራ እንዲያካሄዱ ጥሪ አድርገዋል። የዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ቃል አቀባይ ኬይላይት ማክኒ፤ የናቫልኒን መመረዝ “ፍጹም ዘግናኝ” ነው ማለታቸውን ርዕሰ-አንቀጹ ጠቅሷል።.

“ሩስያ ከዚህ ቀደምም የነርቭ ኤጀንት ኬሚካል ተጠቅምለች። ድርጊቱን የፈጸሙትን ሰዎች ተጠያቂ ለማድረግ ከአጋሮቻችንና ከአለም-አቀፉ ማህበረሰብ ጋር እየሰራን ነው። ለከይሲው ተግባራቸው የገንዘብ ማዕቀብ ይጣላል። የሩስያ ህዝብ ካለምንም ስጋት በተለይም የኬሚካል ኤጀንት ስጋት ሳያድርበት የመሰለውን ነገር በሰላማዊ መንገድ የመግለጽ መብት አለው።” ብለዋል ኬይላይት ማክኒ።

የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪድን ሀገሮች ድርጅት/ኔቶ/ ዋና ፀሀፊ የንስ ስቶልተንበርግ፣ የኔቶ አጋር ሃገሮች፣ በናቫልኒ ላይ የተፈጸመውን ዘግናኝ ጥቃት፣ በተባበረ ድምጽ አውግዘዋል ብለዋል።

ዋናው ፀሃፊ ስለ ግድያው ሙከራ በዓለምቀፍ ደረጃ በሚደረገው፣ ወገን ያልለየ ምርመርና አጥቂዎቹን በመፈልግ ጥረት ላይ ሩስያ እንድትሳተፍ ጥሪ ማድረጋቸውን፣ ርዕሰ አንቀጹ ጠቁሟል።

ቡድን ሰባት በሚል ስያሜ የሚታወቁት፣ በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሃገሮች ቡድንም፣ በጉዳዩ ላይ መግለጫ አውጥቷል። “የዚህ ዘግናኝ የምረዛ ጥቃት ተጠያቂዎችን ለይቶ ለማውቅና ለፍርድ ለማቅረብ በሚደረገው ምርመራ፣የተሟላ ግልጽነት እንዲኖር መግለጫው ጠይቋል። ሩስያ የኬሚካል መሳርያ ውልን በሚመለከት የገባችውን ቃል ታሳቢ በማድረግ መስራት እንዳለባት፣ ቡድን ሰባት ማሳሰቡን ርዕሰ-አንገጹ ገልጿል።

ቡድን ሰባት አይይዞም “በተቃውሞው መሪ ናቫልኒ ላይ የተፈጸመው ጥቃት፣ ሩስያ ውስጥ በዲሞክራሲና በብዘሃነት ላይ የሚካሄደው ሌላ ትልቅ በደል ነው። ሩስያ ዓለማቀፍ ማኅበርሰብ ላቀረበው ጥሪ የምተሰጠውን ምላሽ፣ በጥብቅ መካታተሉን እንቀጥላለን ይላል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮም፣ የቡድን ሰባት መግለጫን አስተጋብተዋል።

“እንዲህ አይነቱ ጥቃት፣ ኬሚካል መሳርያን መጠቅም የሚያግደውን ዓለምቀፍ ውልን ይፃረራል” ብለዋል ሲል፣ የዕለቱ ርእሰ-አንቀጽ፣ ሀተታውን አብቅቷል።

XS
SM
MD
LG