"እኤአ የካቲት 8፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶንኒ ብሊንከን አሜሪካ ከተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጋር የነበራት የሥራ ግንኙንት እንደገና በአስቸኳይ እንዲጀመር መወሰኗን አስታውቀዋል፡፡" ይላል የእለቱ ርዕሰ አንቀጽ ሀተታውን ሲጀምር፡፡
“ዩናትድ ስቴትስ ዴሞክራሲን ሰብአዊ መብትና እኩልነትን ማዕከል ያደረገው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋ እንዲቀጥል ትጥራለች፡፡”ብሏል ርዕሰ አንቀጹ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ባወጡት መግለጫ “ፕሬዚዳንት ባይደን ይህንን ራዕይ ተግባራዊ ለማድረግ፣ ዘርፈ ብዙ የሆኑ ውጤታማ ስልቶች አስፈላጊ መሆናቸውን በመግለጽ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በአስቸኳይ ከተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር ተመልሶ በቅርበትና በጥልቀት እንዲሰራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡” ማለታቸውን ርእሰ አቀንጹ ያስረዳል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩም አያይዘው በርግጥ የሰብአዊ መብቶቹ ጉባኤ አጀንዳውን፣ አባልነትና ቀዳሚ ትኩረቱ ላይ ማሻሻያዎችን ማድረግ ያለበት መሆኑን ጨምሮ፣ በእስራኤል ያደረገውን አድሏዊነት ማስከተካለል ያለበት መሆኑን መናገራቸውን ርዕሰ አንቀጹ ጠቅሷል፡፡
ይሁን እንጂ ሚኒስትሩ “እኤአ በሰኔ 2018 ከጉባኤው መውጣታችን ትርጉም ያለው ለውጥ አላመጣም፡፡ ይልቁንም የአሜሪካ አመራር አለመኖር አምባገነኖች አጀንዳዎቻቸውን ለማስፈጸም ሙከራዎችን እንዲያደርጉ ክፍተት ፈጥሯል፡፡”ማለታቸውን ርዕሰ አንቀጹ አመልክቷል፡፡
“ዩናይትድ ስቴትስ የተባበሩት መንግሥታትን የስደተኞች ጉዳዮ ኮሚሽን አሰራር ለመለወጥ ከፈለገች መጀመር ያለባት ከውስጥ ነው” ሲሉ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ፕሪይስ የሚከተለውን ተናግረዋል
የታቀደውን ለውጥ ማምጣት ከተፈለገ ጉባኤው መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶችን ለማስተዋወቅ ዋና መሳሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ በመላው ዓለም የሰአብአዊ መብቶችን የሚጥሱትን ተጠያቂ እንዲሆኑ ሲደረግ፣ የሴቶችን፣ የልጃገረዶችን፣ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችና በጥቅል ስማቸው የLGBTQI+ የሚባሉትንም ጨምሮ በማህበረሱ የተገለሉ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን መብት ማስተዋወቅ ይቻላል፡፡
ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠል፣ በተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ውስጥ እንደገና ተመልሶ የመሳተፉ ሂደት የዩናይትድ ስቴትስ ልዑካን በጅኔቭ የኮሚሽኑ መደበኛ ስብሰባም ሆነ በበርማ ጒዳይ ላይ ለመምከር በተጠራው ልዩ ስብሰባ ተጀምሯል፡፡ ቃል አቀባዩም “ለጊዜው አሁን ያለን ተሳትፎ በታዛቢነት ይሆናል፡፡ በጉባኤው ውስጥ እንድንናገር በድርድሮች ላይ ተሳታፊ እንድሆንና ከአጋሮች አግር አብረን እንድሰራ ያስችለናል፡፡ ማለታቸውን ርእሰ አቀንጹ ጠቅሷል፡፡
በመጨረሻም፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብሊንከን እንደሚሉት “ዩናይትድ ስቴትስ ከኮሚሽኑ ጋር ገንቢ በሆነ መንገድ ተሳታፊ ስትሆን፣ ከሌሎች አጋሮችና ወዳጆች ጋር በመሆን አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ ብለዋል ሲል ርዕሰ አንቀጹ ሀተታውን ይደመድማል፡፡