ብሊንከ በቻይና እና በዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

የዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና ግንኙነት ለዩናይትድ ስቴትስ ዋና ሥጋት መሆኑን እንደቀጠለ ነው በማለት ርዕሰ አንቀጽ ሐተታውን ይጀምራል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በቅርቡ በስታንፈርድ ዩኒቨርስቲ ሁቨር ተቋም በተካሄደ ውይይት ላይ ባደረጉት ንግግር በቅርብ ዓመታት በዢ ጂንፒንግ አመራር ስር “ከበፊቱ በጣም የተለየች ቻይና ብቅ ብላለች” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የቻይና ሕዝቦች ሪፐብሊክ “ወይም ፒ አር ሲ ይበልጡን በሃገር ውስጥ ጨቋኝ፣ በውጭ ደግሞ ጸበኛ ሆኗል፡፡ ይህ በብዙ መልኩ በጥቅሞቻችን እና በእሴቶቻችን ላይ ተግዳሮቶችን የሚደቅን ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

ይሄ ከታይዋን በተያያዘ ላይ በጉልህ የሚታይ ነው ያለው ርዕሰ አንቀጹ ቤጂንግ ሁኔታዎች አሁን ባሉበት መልኩ እንዲቀጥሉ ከማድረግ ይልቅ ታይዋንን ለማዋሃድ ኃይልን ለመጠቀም ሃሳብ እንዳላት አመላክታለች ብሏል፡፡

“ይህ ጉዳይ ዩናይትድ ስቴትስን ብቻ ሳይሆን የዓለም ሀገሮችን ሁሉ በጥልቅ ጥልቅ የሚያሰጋ ነው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን አስገንዝበዋል ካለ በኋላ ርዕሰ አንቀጹ በየቀኑ በታይዋን ሰርጥ በኩል የሚተላለፈው የንግድ አቅርቦት ብዛት በዓለም ምጣኔ ኃብት ላይ ትልቅ አንድምታ ያለው መሆኑን አውስቷል፡፡

በተለይም ደግሞ በዚህ ቀውስ የተነሳ የታይዋን የየኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ሴማይ ኮንዳክተር ኢንደስትሪ ምርት ከተስተጓጎለ በኢንዱስትሪው ላይ ከባድ ጉዳት ይደርሳል ሲል ርዕሰ አንቀጹ አሳስቧል፡፡

“በመሆኑም ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሀገሮች ሁሉ ሲባል የታይዋን መተላለፊያ (ሰርጥን) ሠላም እና መረጋጋት ሊጠበቅ ይገባል፡ ልዩነቶችም በሰላም መፈታታቸውን ማረጋገጥ እጅግ አስፈላጊ ነው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ብሊንክን አስገንዝበዋል፡፡

አያይዘውም “ስለዚህም ቤጂንግ ነገሮች በጉልበት እና በሃይል ከመፍታት ይልቅ በሰላም መፍታት ያለውን እርባና ወደምታስተውልበት ሁኔታ ትመለሳለች ነገሮችን በግድ ሲብስም በኃይል ለማስፈጸም ከመሞከር ትቆጠባለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ በማለት ብሊንክን ማስጠንቀቃቸውን ርዕሰ አንቀጹ አውስቷል፡፡

አክለውም ብሊንከን ታይዋን እሯሷን መከላከል እንድትችል ለመርዳት የገባነውን ቃል ኪዳን ለመፈጸም ባለን ቁርጠኝነት እንደጸናን ነን” ብለዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ “በታይዋን ዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት ድንጋጌ በሦስቱ የጋራ መግለጫዎች እና በስድስቱ ማረጋገጫዎች በመመራት በአንድ ቻይና ፖሊሲዋ ትጸናለች ሲል ርዕሰ አንቀጹ ጽሁፉን ይደመድማል፡፡