ዩናይትድ ስቴትስ እና ፓኪስታን የፓኪስታን የጤና ዋስትና እና የበሽታዎች ቅኝት ስራዎች ለማሻሻል የታለሙ ሁለት የጋራ መርሐ ግብሮችን አውጥተው ሰርተዋል

አንዱ የመድሃኒት ደህንነት እና አዋጭነትን የሚገመግም የተሻሻለ ዘዴ ላይ የሚሰራ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ፓኪስታን የተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመከታተል ያላትን ዓቅም ማጎልበት ላይ ያነጣጠረ መሆኑን በማውሳት ርዕሰ አንቀጹ ጽሁፉን ጀምሯል።

እናም ባለፈው ታህሳስ ወር መጀመሪያ የፓኪስታን የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ከዩናይትድስ ስቴትስ(ዩ ኤስ አይ ዲ) ጋራ በቅመማ እና ስራ ላይ እንዲውሉ ፈቃድ ማግኘት ሂደት ላይ ያሉ አዳዲስ መድሃኒቶችን በመቆጣጠር ረገድ የሚሰራ አዲስ ውጥን ይፋ አድርገዋል።

ይህ የጋራ መርሃ ግብር የፓኪስታን ኩባኒያዎች መድሃኒት ለመቀመም ሲነሱ ፈጥነው ፈቃድ እንዲያገኙ ባነሰ ወጪ ፈጥነው ደህንነቱ የተጠበቀና ፍቱን መድሃኒት ገበያ ላይ ማቅረብ እንዲችሉ ይሰራል።

ኩባኒያዎች ዓለም አቀፍ የመድሃኒት ቅመማ መስፈርቶችን እንዲያከብሩም በማድረግ ይረዳል ማለታቸውን ርዕሰ አንቀጹ አውስቷል።

የዩናይትድ ስቴትስ እና የፓኪስታን ባለስልጣናት አለ በመቀጠል ይፋ እንዳደረጉትየጤና ባለስልጣናት በሃገሪቱ ዙሪያ ኮቪድ አስራ ዘጠኝን የመሳሰሉ በሽታዎችን ስርጭት የመከታተል ዐቅማቸውን የሚያጠናክሩ አንድ መቶ ሃምሳ አምስት የበሽታ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎችን በአውራጃዎች ደረጃ እንዳስመረቁ ርዕሰ አንቀጹ ጠቅሷል።

በተላላፊ በሽታዎቹ ቅኝት ጣቢያዎች ለሚሰሩ የፈጣን ምላሽ ባለሙያዎች የዩናይትድ ስቴትስ የዐለም አቀፍ ልማት ርዳታ ድርጅት ዩ ኤስ ኤድ የስልጠና ድጋፍ ተሰጥቷል።

ሰዎች በኮቪድ አስራ ዘጠኝ ሲጠቁ ከነሱ ጋር የቅርብ ንክኪ ኖሮአቸው ለቫይረሱ ሊጋለጡ የሚችሉ ሰዎችን በመከታተል ረገድ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፥ ባጠናቀሩዋቸው መረጃዎች ላይ ተመርኩዘው በየወረዳው ኮሮና ቫይረስ በብዛት ሊቀሰቀስ የሚችልባቸውን ቦታዎች ፈጥነው በመለየት በወረዳ እና በክፍለ ሃገር መካከል በተሻለ ቅንጅት መስራት የሚያስችላቸውን ትምህርትም አግኝተዋል።

የተገኙት ድጋፎች እጅግ ጠቃሚ መሆናቸውን ያመለከቱት የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር የጤና አማካሪ ዶክተር ፋይዘል ሱልታን የዩናይትድ ስቴትስን መንግሥት አመስግነዋል። ሁለቱ ሃገሮቻችን ዓለም አቀፍ የጤና ጥበቃ አጀንዳ ስብስብ ውስጥ ያለንን የጋራ የመሪነት ጥረት ጨመሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መርሃ ግብሮች በህብረት በግንባር ቀድምነት በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን ሲሉም አክለዋል።

የዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ሚሽን ድሬክተር ጁሊ ኮነን በበኩላቸው ኮቪድ አስራ ዘጠኝን የመሳሰሉ የህዝብ ጤና ስጋቶችን ፈጥኖ በመከታተል ምላሽ መስጠት መቻል ወሳኝ በመሆኑ እኛንም ከፓኪስታን መንግስት ጋር ሆነን የበሽታዎች ቅኝት እና ምላሽ ጣቢያዎች እንድናቋቁም እና ሶስት ሽህ የሚሆኑ የጤና ሰራተኞችን ዓቅም ለመገንባት እንድንሰራ ያነሳሳን እሱ ነው ሲሉ የተናገሩትን ጠቅሶ ርዕሰ አንቀጹ ጽሁፉን ደምድሟል

ዩናይት ግብሮችን አውጥተው ሰርተዋል።