Accessibility links

Breaking News

ሶሪያ አሁንም የተመድን የኬሚካል ጦር መሳሪያዎችን አጠቃቀም ደንብ እያደናቀፈች ነው


የኬሚካል ጦር መሣሪያ እገዳ ድርጅት (ኦፒሲዳብልዩ)
የኬሚካል ጦር መሣሪያ እገዳ ድርጅት (ኦፒሲዳብልዩ)

“ሶሪያ አሁንም የተመድን የኬሚካል ጦር መሳሪያዎች አጠቃቀም ጥረቶችን እያደናቀፈች ነው” በሚል ርዕስ የወጣው ይህ ርዕሰ አንቀፅ የሶሪያ መንግሥት የኬሚካል ጦር መሳሪያ ሥምምነቶችን አስመልከቶ በሚያወጣው ትክክለኛ ያልሆነና ያልተሟላ መረጃ ላይ ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ እያሳደረ ያለውን ጫና እንዲቀጥልና የአሳድን መንግሥት በሶሪያዊያን ላይ በተደጋጋሚ ላደረሳቸው ጥቃቶች በተጠያቂነት እንዲይዝ ያሳስባል።

ታኅሳስ 27/2015 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት መግለጫ ላይ የድርጅቱ ጦር መሳሪያዎች የማስፈታት ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አዴዴጂ ኤቦ ሶሪያ ከውሳኔ 2118 ጋር በተያያዙና በተንጠላጠሉ ጉዳዮች ላይ ምንም ለውጥ አላሳየችም ሲሉ ለምክር ቤቱ መናገራቸውን ርዕሰ አንቀፁ ያስታውስና ውሳኔው ሶሪያ በይዞታዋ ሥር የሚገኙ ኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን ዝርዝር እንድታሳውቅና ክትትል በሚደረግበትና በሚረጋገጥ ሁኔታ እንድታሳውቅ የሚያዝዝ መሆኑን ማመልከታቸውን ይናገራል።

ኤቦ አክለውም “የኬሚካል ጦር መሳሪያዎች እንዲወገዱ የሚደረጉትን ጥረቶች ለማገዝ የሚሠራው የኬሚካል ጦር መሣሪያ እገዳ ድርጅት (ኦፒሲዳብልዩ) የቴክኒክ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ከሶሪያ መንግሥት ጋር ተከታዩን ምክክር ለማዘጋጀት ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ገልፀዋል።

የሶሪያ መንግሥት ባለመተበበሩ ቡድኑ ጥር ውስጥ ወደ ሶሪያ የላከው በጥቂት ጉዳዮች ላይ ብቻ የሚነጋገር አነስተኛ የቡድኑን አባላት ብቻ መሆኑን ሚስተር ኢቦ ማስታወቃቸውን፣ “የአሳድ መንግሥት የኬሚካል የጦር መሳሪያዎች አጠቃቀም ተጠያቂነት የጎደለው መሆኑንና ለዓለምአቀፉ ሰላም ሥጋትና ለሁላችንም አደጋ ነው” ሲሉ አፅንዖት መስጠታቸውን ርዕሰ አንቀፁ ይናገራል።

በመቀጠልም በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ተወካይ ሪቻርድ ሚልስ “በፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ ውስጥ አዲሱን ዓመት የምንጀምረው፣ በሚያሳዝን ሁኔታ፣ የአሳድ መንግሥት ኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን እንዴት በተደጋጋሚ እንደተጠቀመና በኬሚካል ጦር መሳሪያዎች ስምምነትና በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ቁጥር 2118 ውሣኔዎች መሠረት የተጣሉበትን ግዴታዎች መወጣት እንዳልቻለ እየተነጋገርን መሆኑ ነው” ማለታቸውን አስፍሯል።

ገምጋሚው ቡድን ጥር ውስጥ ሶሪያ እንደሚገባ መነገሩ የሚበረታታ ዜና እንደሆነ አምባሳደር ሚልስ መሆኑን አምባሳደር ሚልስ መናገራቸውን ርዕሰ አንቀፁ ጠቁሞ የሶሪያን የመሣሪያ ዝርዝር መግለጫ አስመልክቶ ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች በመኖራቸው ኦፒሲዳብልዩ ሥራውን ትርጉም ባለው ሁኔታ መቀጠል እንዲችል አገዛዙ ማደናቀፉን እንዲያቆም መጠየቃቸውንም አመልክቷል።

አምባሳደሩ ከጠቀሷቸው መካከል - ይላል ርዕሰ አንቀፁ - (እኤአ) በ2018 ባርዛ በሚገኘው የሣይንሳዊ ጥናቶችና ምርምር ማዕክል ውስጥ የጊዜ ሠሌዳ ላይ የሠፈረ ኬሚካል አሻራ ስለመገኘቱ፤ ዱማ ከተካሄደው ኬሚካል ጥቃት ጋር ተያያዝዥነት ያላቸው ሁለት የክሎሪን ሲሊንደሮች ከኦፒሲዳብልዩ መመሪያ ጋር በሚቃረን ሁኔታ ስለመንቀሳቀሳቸው እና አገዛዙ በኬሚካል መሳሪያዎች መርኃግብሩ ላይ ጠቅላላ እድሳት ስለማድረጉ ግልፅ መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ ተብለው የሚታመኑ መረጃዎችን ለኦፒሲዳብልዩ የዝርዝር መግለጫ ገምጋሚ ቡድን እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ስላለማቅረቡ የሚታመን ማብራሪያ አለመኖሩ ይገኙባቸዋል።

አምባሳደሩ በመጨረሻም “አገዛዙ ግዴታውን እንዲወጣና የሶሪያን የኬሚካል ጦር መሣሪያዎች አጠቃቀም ችግሮች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት እንድንችል የኬሚካል ጦር መሣሪያ እገዳ ድርጅት የባለሙያዎች ቡድን ሥራዎችን ማደናቀፉን በአስቸኳይ እንዲያቆም ዩናይትድ ስቴትስ በድጋሚ ታሳስባለች” ሲሉ ማሳወቃቸውን ርዕሰ አንቀፁ በመቋጫው አሥፍሯል።

XS
SM
MD
LG