Accessibility links

Breaking News

አሜሪካ የፕሬዚዳንቶችን ቀን አከበረች


ፎቶ ፋይል፦ የአሜሪካ ዶላር
ፎቶ ፋይል፦ የአሜሪካ ዶላር

በየዓመቱ፣ የካቲት ወር በገባ በሦስተኛው ሰኞ፣ አሜሪካውያን የፕሬዚዳንቶች ቀን ያከብራሉ። ዛሬ በመላው አሜሪካ እየተከበረ ያለው ይህ በዓል በሥልጣን ላይ ላሉትም ሆነ ላለፉት ፕሬዚዳንቶች መታሰቢያ ቢሆንም፣ በተለይ ደግሞ የልደት ቀናቸው በዚህ ወር፣ በአስር ቀን ልዩነት የሚከበረው ጆርጅ ዋሽንግተን እና አብርሃም ሊንከን ይታሰባሉ።

ሆኖም የበዓሉ የመጀመሪያ አከባበርም ሆነ፣ እ.አ.አ በ1971 በዓሉ እውቅና ከተሰጠው በኃላ የሚካሄዱ ሥነስርዓቶች፣ የዋሽንግተንን የልደት ቀን ወደ ፕሬዝዳንቶች ቀን ያልቀየረ ሲሆን፣ ሊንከንንም በልዩነት አያከብርም። ይልቁኑም ከመነሻው አንስቶ እንደሚደረገው፣ እለቱ የሀገሪቱ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት ለሆኑት ጆርጅ ዋሽንግተን ምስጋና እና እውቅና የሚሰጥበት ቀን ነው።

ጆርጅ ዋሽንግተን፣ አሜሪካ ከእንግሊዝ ንጉሳዊ አገዛዝ ነፃ እንድትወጣ ያደረገውን አማፂ ጦር የመሩ ናቸው። እጅግ በጣም ተወዳጅ መሪም ነበሩ። ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ተመዝግቦ የሚገኘው የልደታቸው ክብረ በዓል፣ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1778 ከፊላደልፊያ ከተማ ወጣ ብሎ፣ ቫሊ ፎርጅ ውስጥ በሚገኘው የጦሩ ካምፕ ውስጥ የተደረገው አከባበር ነው። በወቅቱ የከበሮ መቺዎች እና ትንሽ ዋሽንት መሰል የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾች ከማደሪያ ድንኳናቸው ፊት የሙዚቃ ትርዒት አሳይተዋል። በኋላ ላይ ዋሽንግተን ይህ ዐይነት አከባበር (የእንግሊዙን) "ንጉስ ጆርጅን ችላ ማለታችንን ለማሳየት የተጀመረ ነው" ብለው ነበር።

ዋሽንግተን ለመደሰት እና ለመከበር የሚፈልጉ ሰው አልነበሩም። ነገር ግን ለአዲሷ ሀገር ጥቅም ህዝቡን በአንድነት የሚያሰባስብ እና አብሮ እንዲሠራ የሚያነሳሳ ግለሰብ አስፈላጊነትን ተረድተው ነበር።

ዋሽንግተን እ.አ.አ በ1799 ከሞቱ በኋላም አሜሪካውያን የልደት በዓላቸውን ይፋ ባልሆነ መልኩ ማክበር ቀጠሉ። የካቲት ወር ብሄራዊ በዓል ሆኖ መታሰብ የጀመረው እ.አ.አ በ1879 ሲሆን በዓሉ የካቲት ወር በገባ በሦስተኛው ሰኞ እንዲሆን በህግ የተደነገገው ደግሞ እ.አ.አ በ1971 ነው።

ዋሽንግተን ከሳቸው በኋላ የሀገሪቱን ከፍተኛውን የሥልጣን እርከን ለሚረከቡ ሰዎች ትልቅ ምሳሌ ትተው አልፈዋል። ሀገሪቱ የተረጋጋ የገንዝብ መሠረት ላይ እንድትቀመጥ እና አዲስ የተመሰረተችው ዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያውን ከባድ የምጥ ህመም በፍጥነት አልፋ የተረጋጋ፣ ዲሞክራሲያዊ እና ህጋዊ መንግስት እንድትመሰርት አድርገዋል። ከሁለት አራት ዓመታት የሥልጣን ዘመን በኋላ በፈቃደኝነት ሥራውን በመልቀቅ እና እርሳቸውን ተክተው ለተመረጡት መሪ ሥልጣን በሰላም እንዲተላለፍ በማድረግም፣ ጆርጅ ዋሽንግተን ለወደፊት ፕሬዚዳንቶች ወሳኝ የሆነ መሠረት ጥለዋል።

XS
SM
MD
LG