በመሠረቱ ዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ቀውስ ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ይቺ ሁላችንም የምንጋራትን ስስ የሆነችውን ዓለም ለመጠበቅና ለመከላከል ነው፡፡ ይህን የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የአየር ንብረት ለውጥ ልዩ ልኡክ ጆን ኬሪ ናቸው፡፡ እንዲህ ይላሉ ኬሪ
“ጉዳዩ የአየር ንብረት ለውጡን አስመልክቶ ምንም ነገር አለማድረግ አንድ ነገር ከማድረግ የበለጠ ዋጋ እንደሚያስከፍል የመረዳት ጉዳይ ነው፡፡ደግሞም ያለምንም ማጋገነን የህልውና ጉዳይ ነው፡፡”
በለንደን በተደረገው ጉባኤ ይህን የተናገሩት ጆን ኬሪ “የአየር ንብረት ለውጥ የወቅቱ ፈተናችን ሲሆን ጊዜውም እያለፈብን ነው ብለዋል፡፡ እኤአ በ2015 ዓም 196 አገሮች የፓሪሱን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱም የምድር አጠቃላይ የሙቀት መጠን ከሁለት ነጥብ ዲግሪ ሴልሽየስ በላይ እንዳያልፍና በ1.5 እንዲወሰን ጥረት ለማድረግ ነው፡፡
በስምምነቱ መሠረት፣ እያንዳንዱ አገር፣ በየግሉ ለማድረግ የገባውን ቃል እንዲፈጽም፣ ቁርጠኝነቱን የገለጸበት እና በጋራ ደግሞ ዓለምን ትክከለኛ አቅጣጫ ለማስያስዝ የተገባ ስምምነት ነው” ብለዋል ጆን ኬሪ፡፡
እያንዳንዱ አገር በፓሪሱ ስምምነት የገባውን ቃል እንኳ ቢያከብር የፕላኔታችን የሙቀት መጠን አሁንም 2.3 ወይም 3 ዲግሪ ሴንትግሬድ መጨመሩ አይቀርም፡፡ “ያ ደግሞ ምን እንደሚያስከትል ከወዲሁ አይተናል”
አሁን የምንኖረው ከዚህ በፊት ሰብሎች ይበቅሉባቸው በነበሩበት ቦታ ላይ ዛሬ የማይበቅሉባቸው በሆኑበት ዓለም ነው፡፡ የውቅያኖሶቹ ይዘት በበለጠና በፈጠነ ሁኔታ እየተለዋወጠ ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለመኖሪያነት በማይገቡ ቦታዎች እንዲኖሩ የሚገደደቡት ሁኔታ እየጨመረ ነው፡፡ ምናልባትም በዓመት ወደ 20 ሚሊዮን ሰዎች ከቦታ ወደ ቦታ ይሰደዳሉ፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው ፖለቲካ በስደት ላይ የሚያስከትለውን ተጽእኖ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተመልክተናል፡፡ ስለዚህ አሁን ሰዎች የሚሰደዱባቸው ቦታዎች ነገ ጨርሶ ሰው ሊኖርባቸው የማይችሉ ቢሆኑስ ብላችሁ አስቡ? ሁሉም ሰው፣ የሰው ልጅ ሊኖር ወደ ሚችልባቸው ቦታዎች ብቻ ቢሰደድ ሊመጣ የሚችለውን ነገር ይታያችሁ?
አሁን የምድር ሙቀት በ1.2 ዲግሪ በማደጉ እያየነው ያለነው እሱን ነው፡፡ ጆን ኬሪ “ያንን በእጥፍ ለመጨመር ማሰብ የቀውስ አደጋን መጋበዝ ነው፡፡” ይላሉ፡፡
ይሁን እንጂ ግን “አሁንም ቢሆን ልናስወግደው እንችላለን፡፡ይሁን እንጂ ግን ፍጹም ከልባችን በሆነ ስሜት፣ በፍጥነት ተነሳስተን፣ በዓለም ላይ ያሉትን አገራት በሙሉ፣ በአስቸኳይ፣ አንድ ላይ ማምጣት አለብን፡፡
“ዓለም የካርቦን ዳይ ኦክሳይድን ጋዝ ልቀት መቀነስ አለበት፡፡ በተለይም በተለይም በክፍለ ዘመኑ አጋማሽ ወደ ዜሮ ዲግሪ እንዲቀንስ በሚያዘው የሳይንስ ምክረ ሀሳብ መሠረት እኤአ በ2030 በ45 ከመቶ መቀነስ ይኖርበታል፡፡ ይህ ደግሞ በተወሰኑ አገራት ወይም ክልሎች ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም መሆን አለበት፡፡ ያ ከሆን ይህን ዘመን ወሳኙ አስርተ ዓመት ያደርገዋል፡፡ 2021ንም ወሳኝ ዓመት ይሆናል፡፡”
“በተለይም የኛን ምርጫ የሚጠብቁትን ሁለት የድልና አሳዛኝ አማራጮች በማወቅ ይህን አብረን ማሳካት እንችላለን፡፡ ደግሞም ይኖርብናልንም፡፡” ያሉት ጆን ኬሪ “ዓለም በጣም የሚያስፈልጋትን ስናውቅ ያ ሁልጊዜ እኛ ያደረግነው ነገር መሆኑን እናውቃለን፡፡ ስለዚህ አብረን እንሁን!