"የዩናይትድ ስቴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከቡድን ሰባት አገራት፣ ከካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ የጃፓን እና የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ምኒስትሮችና፣ ከአውሮፓ ህበረት ከፍተኛ ልኡካን ጋር በመሆን፣ በቅርቡ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ያለውን የሰአብአዊ መብት ጥሰትና ጥቃት፣ እንዲሁም የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህግ ጥሰትን አስመልከቶ፣ እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች፣ እጅግ ያሳሰባቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡” ይላል የእለቱ ርእሰ አንቀጽ ጽሁፉን ሲጀምር፡፡
ርእሰ አንቀጹ በመቀጠል፣ "ግጭቱ የተጀመረው ባለፈው ህዳር ወር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ ትግራይን ያስተዳደሩ የነበሩትን የህዝባዊ ሃርነት ድርጅትን በማስወገድ፣ “ህግና ሥርዓትን ለማስከበር” የፌደራል ወታደሮችን ወደ ትግራይ በመላካቸው ነው” ብሏል፡፡
ጦርነቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ፣ በርካታ ሰዎች፣ ትግራይን ለቀው በመውጣት በጎረቤት ሱዳን እንደተጠለሉም ርእሰ አንቀጹ ጠቅሷል፡
ርዕሰ አንቀጹ እንዳመለከተው ፣ የቡድን ሰባት አገራት ባወጡት መግለጫ “ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ፣ አሰገድዶ መድፈርና የጾታ ነክ ጥቃቶች፣ የጅምላ ፍጅቶች፣ የትግራይ ነዋሪዎችና የኤርትራ ስደተኞችን በኃይል እንዲፈናቀሉ ማድረግን አበክረው የሚያወግዙ መሆኑን አስታውቀዋል”
“ሁሉም ወገኖች ከድርጊቱ እንዲቆጠቡ የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት መከበሩን እንዲያረጋግጡና እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችንና ህግጋትን እንዲያከብሩም አባል አገራቱ ጠይቀዋል፡፡
ርእሰ አንቀጹ “ዩናይትድ ስቴትስና አጋሮቹዋ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የተባሉትን ጥቃቶች የፈጸሙትን ተጠያቂ ለማድረግ፣ የገባውን ቃል ተግባራዊ ማድረጉን ማየት ይፈልጋሉ” ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛው የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ በሁሉም ወገኖች ተፈጽመዋል የተባሉትን የሰብአዊ መብት ጥቃቶች በጋራ ለመመርመር መወሰናቸውንም ርእሰ አንቀጹ ጠቅሷል፡፡
ሪፖርት በተደረጉ ወንጀሎችና በሰአብዊ መብት ጥቃቱ ተጠያቂ የሆኑት ላይ፣ ገለልተኛ ግልጽና ወገንተኛ ያልሆነ ምርመራ በማካሄድ፣ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረጉም፣ እጅግ አስፈላጊ መሆኑንም አመልከቷል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ እና የቡድን ሰባት አባል፣ አጋሮችዋ፣ “በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ የሰአብአዊ እርዳታው ተደራሽነት እንዳይደናቀፍ እንዲያደርጉ አሳሳቧል፡፡ የምግብ እጠረቱ እየተባባሰ የሚሄድ ለመሆኑ ከፍተኛ ስጋት ያለ ሲሆን፣ በሰፊው ማዕከላዊና ምስራቃዊ ትግራይ አካባቢዎች፣ አጣዳፊ እርዳታ የሚሹ ችግሮች መታየታቸውም ተጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቅርቡ የኤርትራ ኃይሎች ትግራይን ለቀው እንደሚወጡ ማስታወቃቸውን ርእሰ አንቀጹ በመጥቀስ “ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮችዋ ሂደቱ ወዲያኑ፣ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ የሚፈጸምና ሊረጋገጥም የሚችል መሆን አለበት ብሏል፡፡
የጋራ መግለጫው ግጭትና ጥቃቶች እንዲቆሙ፣ ግልጽ የሆነ ሁሉንም ወገኖች ያካተተ የፖለቲካ ሂደት፣ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ በትግራይ ውስጥ ባሉትም ሁሉ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲደረግና ስፋት ያለው ብሄራዊ የእርቅና መግባባት ሂደት እንዲካሄድ “ ጠይቋል፡፡
በመጨረሻም “እኛ የቡድን ሰባት አገሮች፣ የሰአብዊ እርዳታ ጥረቶችን እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ የሚደረጉ ምርመራዎችን ለማገዝ፣ ዝግጁነታችንን እንገልጻለን” ብሏል ርእሰ አንቀጹ ጽሁፉን ሲደመድም፡፡