Accessibility links

Breaking News

ዲሞክራሲን በማሰናከላቸው በኡጋንዳ ባለሥልጣኖች ላይ የተደረገ የቪዛ እገዳ


የኡጋንዳው የ76 ዓመት ዕድሜ ፕረዚዳንት ዮወሪ ሙሴቬኒ፣ እአአ ከ1986 አንስቶ በሥልጣን ላይ የቆዩ ሲሆን፣ ባለፈው ጥር ወር በተካሄደው ምርጫም አሸንፈዋል። ነገር ግን ዩናይትድ ስቴትስ የምርጫው ሂደት ፍትሀዊም ነጻም አልነበረም በማለት፣ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ለተካሄደው ግጭትና ዲሞክራሲን በማሰናከል ተግባር ተጠያቂ የሆኑት ላይ፣ እርምጃ ለመውሰድ ቃል ገብታለች ሲል፣ የዕለቱ ርዕሰ-አንቀጽ ሀተታውን ይጀምራ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ እአአ ባለፈው ሚያዝያ 16 ባውጡት መግለጫ፣ የኡጋንዳ መንግሥት ተግባር የሀገሪቱን የዲሞክራሲ ጎዳናንና የኡጋንዳ ህገ-መንግሥት በሚፈቅደው መሰረት፣ የሰብአዊ መብት መከበር ማሽቆልቆል መቀጠልን ይወክላል ብለዋል።

“ተቃዋሚ ተወዳዳሪዎች በተደጋጋሚ ወከባ ተፈጽሞባቸዋል። ታስረዋል ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ካለክስ ተይዘዋል። ለበርካታ ንጹሃን ተመልካቾችና የተቃዋሚዎች ደጋፊዎች ህልፈት እንዲሁም መቁሰል፣ ከቅድመ-ምርጫው፣ በምርጫው ወቅትና በድህረ-ምርጫው፣ በጋዜጠኞች ላይ ለተፈጸመው ሀይል መጠቀም ተጠያቂዎቹ፣ የኡጋንዳ የጸጥታ ሃይሎች ናቸው።

የምርጫ ተቋማትን ለመርዳት እንዲሁም ግልጽ የሆነ ምርጫ እንዲካሄድ ለማገዝ፣ ሲሰሩ የቆዩትን የሲቪል ድርቶችና አክቲቪስቶችን የማዋከብ ተግባር፣ የማስፈራራት፣ የእስራትና ከሃገር የማባረር እርምጃ፣ የውሸት ክስና የባንክ ሂሳባቸው፣ ተደራሽነት መንፈግ ኢላማ ሆነዋል ይላል የዕለቱ ርዕሰ-አንቀጽ።

ርዕሰ-አንቅጹ አያይዞም፣ የኡጋንዳ መንግሥት የዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች እንዲሁም የሲቪል ማኅበራት ፈቃድ ማግኘትን ገድቧል። የምርጫ ሂዳቱን ለመታዘብ የቻሉት ታድያ፣ በቅድመ-ምርጫው፣ በምርጫው ወቅትና በድህረ-ምርጫው፣ ሰፊ የማጭበርበር ተግባር እንደነበር ገልጸዋል። ይህም የምርጫው ሂደት ተአማኒ እንዳይሆን አድርጓል ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን።

ይህን መሰረት በማድረግም፣ የምርጫ ሂደቱንም ጨምሮ የኡጋንዳን ዲሞክራስያዊ ሂደትን በማሰናከል ተግባር፣ ተጠያቂ ናቸው በሚባሉት ላይ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የቪዛ ዕገዳ እንደምትጥል፣ አንተኒ ብሊከን አስታውቀዋል።የቪዛ እገዳ የተጣለባቸው ሰዎች፣ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመግባት አይችሉም። እገዳው ቤተሰቦቻቸውንም ሊመለከት ይችላል።

“የኡጋንዳ መንግሥት በጉልህ በሚታይ መልኩ፣ ገጽታውን ማሻሻል ይኖርበታል። በምርጫው ሂደት መዛነፍ፣ በግጭቱና በማስፈራራቱ ተግባር የተሳተፉትን፣ ተጠያቂ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ።

ዩናይትድ ስቴትስ የኡጋንዳን ዲሞክራሲና የሰብአዊ መብት መከበርየምርጫ ሂደቱንም ጨምሮን

በማሰናከል ተግባር፣ እጃቸውን በዶሉ ግለሰቦችና ቤተሰቦቻችው ላይም፣ ተጨማሪ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ማከላቸውን፣ ርዕሰ አንቀጹ ጠቅሷል።

የኡዳንዳ ምርጫ ከመካሄዱ በፊት፣ ዩናይትድ ስቴትስ የምትደግፈው ተወዳዳሪ እንደማይኖር፣ የምትደግፈው ነጻና ፍትሃዊ የሆነ ዲሞክራስያዊ ሂደት መሆኑን፣ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣኖች፣ ግልጽ አድርገው ነበር። አለመታደል ሆኖ የኡጋንዳ ምርጫ በሚጠበቀው መንገድ አልተከናወነም።

ያም ሆኖ ግን ዩናይትድ ስቴትስ የኡጋንዳን ህዝብ አጥብቃ እንደምትደግፍ አስምራበታለች። በሁለቱም ሀገሮቻችን ዲሞክራሲን ለማራመድና የጋራ ብልጽግና እንዲኖር አብረን ለመስራት ባለን ቁርጠኛነት እንቀጥላለን ሲል፣ የዕለቱ ርዕሰ-አንቀጽ ሀተታውን አብቅቷል።

XS
SM
MD
LG