Accessibility links

Breaking News

አሜሪካ ወደ ፊት እየተራመደች ነው


የዩናይተድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ጆ ባይደን
የዩናይተድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ጆ ባይደን

የዩናይተድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ጆ ባይደን፣ ለሀገሪቱ ምክር ቤት ለመጀመርያ ጊዜ ባደረጉት ንግግር፣ አሜሪካ እንደገና እየተራመደች ነው ሲሉ አስታውቀዋል በማለት፣ የዕለቱ ርዕሰ-አንቀጽ ሀተታውን ጀምሯል። “በመታደስና በዕድል ላይ በማትኮር” ሀገሪቱ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመታገልና በኢኮኖሚ ላይ ያስከፈለውን ዋጋ በማሻሻል ተግባር ያሳየችውን እድገት አሞግሰዋል። ፕረዚዳንቱ በተጨማሪም፣ መንግስት በጤና ጥበቃ፣ በትምህርት፣ በመሰረተ-ልማትና በአየር ንብረት ለውጥ ለይ አዲስ መዋዕለ-ነዋይ እንዲያፈስ የሚጠይቁ፣ የተለያዩ ሃስቦችንም አቅርበዋል።

አለምን ሲመለከቱ ደግሞ ፕረዚዳንት ባይደን፣ አሜሪካ ወደፊት እየተራመደች ነው። ነገር ግን አሁን ለማቆም አንችልም” ማለታቸውን ርዕሰ-አንቀጹ ጠቅሷል።

“በ 21 ኛው ምዕተ-አመት አሸናፊ ሆነን ለመውጣት ከቻይናና ከሌሎችም ሀገሮች ጋር እየተወዳደርን ነው። በሀገሪቱ ታሪክ ትልቅ የለውጥ እምርታ ላይ ነው ያለነው። አሁን ካለው በበለጠ ጠንክረን መወዳደር አለብን።” ብለዋል።

ፕረዚዳንት ባይደን “መግባባት ላይ ለመድረስ ከሚገባው በላይ ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ፣ ዲሞክራሲ እየተዳከመ ነው የሚለውን አባባል አልተቀበሉም። ዲሞክራሲ ለፍትህና ለቅን ተግብር እስከቆመ ድረስ፣ ዘላቂና ጠንካራ መሰረት ያለው ነው” ሲሉ ተናግረዋል። በአለም ዙርያ ላሉት መሪዎች፣ “አሜሪካ ተመልሳለች” ብለዋል ፕረዚዳንት ባይደን።

“ብቻችን አይደለም የምናደርገው። ከአጋሮቻቻን ጋር ሆነን በመምራት እናከናውነዋለን። ከአሸባሪነት እስከ የኑክሌር ዝውውር፣ የፍልሰት ፍሰት፣ የሳይበር ደህንነት፣ የአየር ንብረት ለውጥና የኮቪድ ወረርሽኙ ያደረሰዋቸው ቀውሶች አንድ ሀገር ብቻ ልትወጣቸው አትችልም።” ብለዋል።

የቻይና ህዝባዊ ሪፑብሊክን በሚመለከት፣ ውድድሩን በጸጋ እንቀበለዋለን ብለዋል ፕረዚዳንት ባይደን። ግጭት የመፍጠር ፍላጎት የለንም። ነገር ግን ዪናይትድ ስቴትስ ፍትህ የጎደለው የንግድ አሰራርንና የአሜሪካ የአዕምሮ ንብረት ስርቆትን አትቀበለም ብለዋል ባይደን። ዩናይትድ ስቴታስ በተጨማሪም፣ በኢንዶ-ፓሲፊክ ላይ ጠንካራ ወታደራዊ ህልውና ይኖራታል።

”ግጭትን ለመተንኮስ ሳይሆን ለማስወገድ ነው” ሲሉ፣ፕረዚድንቱ መናገራቸውን፣ ርዕሰ አንቀጹ ጠቁሟል።

የሩስያን ከይሲ ተግባሮች ያሉትን አስመልክቶ፣ ቀጥተኛና ተመጣጣኝ ምላሽ ለመስጠት ቃል ገብተዋል። ለክረምሊኑ የሳይበር ጥቃትና ባለፈው አመት፣ በዩናይትድ ስቴትስ በተካሂደው ምርጫ፣ ሩስያ ላደረገችው ጣልቃ ገብነት እንደሰጡት ምላሽ ሁሉ ይላል ርዕሰ-አንቀጹ። ነገር ግን ሩስያና ዩናይትድ ስቴትስ ለጋራ ጥቅማቸው ሲሉ፣ ሊተባበሩ በሚችልዋቸው ጉዳዮች ላይ፣ ሊተባበሩ አንደሚችሉ ግልጽ አድርግዋል።

በኢራንና በሰሜን ኮርያ የሚደቀነውን የኑክሌር ፕሮግራም አደጋ አስመልክቶ፣ በዲፕሎማሲና በጠንካር መከላከል በኩል ለመፍታት፣ ከወዳጆችና ከአጋሮች ጋር ለመስራት ፕረዚድንት ባይደን ቃል ገብተዋል።

በአሜሪካ ህዝብ ቁርጠኝነት ምክንያት የሚያሽንፉት አምባገነኖች ሳይህኑ” አሸናፊዋ አሜሪካ ናት” ሲሉ ፕረዚዳንቱ መናገራቸን በመግለጽ፣ የእለቱ ርዕሰ-አንቀጽ ሀተታውን አብቅቷል።

XS
SM
MD
LG