“ይህ የማይመስል የተንቀሳቃሽ ስዕል ይዘት አይደለም” ብለዋል የፌደራል ምርመራ ቢሮ ረዳት ስራ አስኪያጅ ዊልይም ስዊኒ፣ በኒው ዮርክ ደቡባዊ ወረዳ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ አቃብየ ህግ ጽህፈት ቤት ሆነው፣ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ። “አንድ የ ኢራን መንግስትን የሚደገፍ ቡድን፣ እዚህ ዩናይተድ ስቴትስ የምትገኝ ጋዜጠኛን ጠልፎ፣ በግዴታ ወደ ኢራን ለመመለስ ማሴሩን ገልጸናል” ሲሉ መናገርቸውን በመጥቀስ፣ የዛሬው ርዕሰ-አንቀጽ ሀተታውን ይጀመራል።
የጠለፋው ሴራ ኢላማ፣ የኒው ዮርክ ነዋሪ፣ ትውልደ ኢራን አሜሪካዊት ጋዜጠኛ ማሲህ ዐሊነጃድ መሆንዋን ገልጻለች። ኢራን እያለች ለአመታት ያህል በጋዜጠኛነት ሰርታለች። የጋዜጠኝነት ስራዋም የኢራንን መንግስት አስቆጥቷል።
ዐሊነጃድ ከ12 አመታት በፊት፣ ከሀገርዋ ሸሽታ ከወጣች ወዲህ፣ የኢራን ሴቶች ሂጃብ እንዲለብሱ መገደዳቸውን የሚቃወም ዘመቻ፣ በማህበርዊ ሚድያ በኩል በማካሄድ ታዋቂ ሆናለች። በአሜሪካ ድምጽ ተወዳጅነት ያለው የቴሌቪሽን ፕሮግራም በማስተናገድ ተግባርም ትሰራከች ይላል፣ የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ።
የዋይት ሀውስ ቤተመንግስት ቃል-አቀባይ ጄን ሳኪ፣ አደገኛ ያሉትን የኢራን ጋዜጠኛን የመጥለፍ ሴራን አውግዘዋል። ኢራን ውስጥም ሆነ ከሀገሪቱ ውጭ፣ በሰላማዊ መንገድ የሚሰሩትን ሰዎች ድምጽ ለመሸበብ የምታደርገውን ጥረት ዘግናኝ ብለዋታል።
የድንበር አልባ ጋዜጠኞች ቡድን፣ የዚህ አመቱን የአለም ነጻ ፕረስን አስመልክቶ ባወጣው አሃዝ፣ ኢራን ከ 180 ሃገሮች 174ኛ ሆናለች። የሚድያ ነጻነት ድርጅት፣ መንግስት ጋዜጠኞችን ለመቆጣጠር ስለሚያደርጋቸው፣ ጭካኔ የተመላባቸው ጥረቶች ጠቅሷል። ምርመራዎችን፣ እስራቶችንና ግድያዎችን እንደሚያካትቱ፣ ድርጅቱ ጠቁሟል።
የጋዜጠኞች ህይወት አደጋ ላይ የሚወድቅባቸው ሃገሮች፣ ኢራን ብቻ አይደለችም ይላል።
ርዕሰ-አንቀጹ። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ አንተኒ ብሊንከን እንደገለጹት፣ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ፣ በቅርቡ ያወጣው የሰብአዊ መብት ዘገባ፣ በስራቸው ምክንያት የተገደሉ፣ ጥቃት የተፈጸመባቸውና ወከባ የሚደርስባቸው በርካታ የጋዜጠኝነት ሰራተኞች እንዳሉ ያመለክታል።
ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ኮሚቴ፣ ባለፈው አመት በስራቸው ምክንያት የተገደሉት ጋዜጠኞች ቁጥር ከእጥፍ በላይ ሆኗል። ብዙ ጋዜጠኞች የተገደሉባቸው ሀገሮች፣ ሜክሲኮና አፍጋኒስታን ናቸው ሲል ዘግቧል። /CPJ/ በሚል የእንግሊዘኛ አህጽሮት የሚታወቀው ኮሚቴ፣ ድርጅቱ መመዝገብ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ አምና በስራቸው ምክንያት የታሰሩት ጋዜጠኞች ብዛት፣ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አስገንዝቧል። ባለፈው አመት ከታሰሩት ጋዜጠኞች አብዛኞቹ፣ ቻይና ቱርክና ግብጽ ውስጥ መሆናቸውን CPJ ገልጿል።
ማሲህ ዐሊነጃድ ስለ መጠለፉ ሴራ ከሰማች በሁዋላ፣ በስራዋ ለመቀጠል ቁርጠኛ ሆናለች። “እነዚህ ቁስሎች ሁሉ እንድጠነክር አድርገውኛል” ብላለች። ይህም በአለም ዙርያ ያሉት፣ ለባለስልታኖች ሀቁን የሚናገሩ ጋዜጠኞች ሁሉ የሚሰማቸው ነገር መሆኑን ገልጻለች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እንዳሉት፣ በነጻ ሚድያ የሚቀርቡት በሀቅና በትክክለኛነት ላይ የተመሰረቱ መረጃዎች፣ የበለጸገና የዲሞክራስያዊ ህብረተሰብ መሰረት ናቸው። ሁሉም መንግስታት፣ የሚድያ ደህንነትን እንዲያረጋግጡ፣ ጋዜጠኞች ስራቸውን ካለምንም ፍርሃት፣ ጥቃት፣ ዛቻና ፍትህ የጎደለው እስራት ለመስራት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር እንዲያደርጉ፣ ጥሪ እናቀባለን ሲል፣ የዕለቱ ርዕሰ-አንቀጽ፣ ሀተታውን አብቅቷል።