ሁሉንአቀፍ የትምህር መብት በተለይም ለሴቶች ማዳረስ መልሶ ፍሬ የሚሰጥ ኢንቨትመንት ነው፡ ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማትና ተራድኦ ሥራ አስኪያጅ ሰማንታ ፓወር በቅርቡ ባሰሙንት ንግግር አስታውቀዋል፡፡ ይላል ርዕሰ አንቀጹ ጽሁፉን ሲጀምር:: ሰማንታ
“በቅርብየተደረገአንድ ጥናት፣ በታዳጊ አገሮች፣ በሴቶች መብትና ትምህርት ላይ ኢንቨስት የሚደረግ እያንዳንዱ ዶላር፣ የ2ዶላር ከ80 ሳንቲም ትርፍ ያስገኛል፡፡ ለሴቶች የሚደረግ አንድ ተጨማሪ የትምህርት ዓመትም፣ ገቢያቸውን ከአስር እስከ 20 ከመቶ ያሳድጋል፡፡” ብለዋል፡፡
ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠል ፤ ከዚህም በላይ እያንዳንዱ ተጨማሪ የትምህርት ዓመት፣ ወደ ግጭት ሊገባ ከተዘጋጀው ወንድ ልጅ በ20 ከመቶውን ያስቀራል፡፡” ብሏል፡፡
“አንድ ጥናት በዓለም ላይ ያለውን የህጻናት ሞት በግማሽ እንዲቀንስ የረዳው ከእኤአ ከ1970 ጀምሮ ለአቅመ ሄዋን ለደረሱ ሴቶች የተሰጠው ትምህር ነው፡፡” ማለቱንም ጽሁፉ ጠቅሷል፡፡
ሰማንታፓወል “እንዳለመታደል ሆኖ ግን የኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ በመላው ዓለም ያለውን የትምህር ሥርዐት አዛብቶታል፡፡ ብለዋል” ያለው ርዕሰ አንቀጽ “ለዚህ ችግር ምላሽ ለመስጠት የዩናይትድ ስቴትስ የልማትና ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ በ50 አገሮች ውስጥ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ትምህርታቸው ለተስተጓጎለ ከ24 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች የሚሆን የትምህር መርሃ ግብር” ማውጣቱን አስታውቋል፡፡
“የሆኖ ሆኖ፣ ብዙ ሴቶች፣ ስደተኞች፣ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች አሁንም ቢሆንም የትምህር እድል እያገኙ አይደሉም፡፡” ያለው ርዕሰ አንቀጽ፣ ይህ በመሆኑም ዩኤ ኤስ ኤድ “ትምህር አይቆይም” ለተባለው መርሃ ግብር የሚውል አዲሲ የ37 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብቷል” ብሏል፡፡
ከዚህገንዘብውስጥ 14 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው ከውጭ ጉዳይ ምኒስቴር የስነህዝብና ስደተኞች ቢሮ የተገኘ መሆኑንም አመልክቷል፡፡
የርዕሰ አንቀጹ ጽሁፉ በመቀጠል፣ Education Cannot Wait ወይም “ትምህርት አይቆይም” የተሰኘው መርሃ ግብር፣ ትምህርት በህይወት ውስጥ የማያቋርጥመርሃ ግብር መሆኑን ለመግለጽ፣ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በፊት፣ ቀደም ብለው ትምህር ቤቶች በተዘጉባቸውና፣ በግጭት እየታመሱ ባሉ፣ እንደ መካከለኛውና ሰሜን፣ ማሊ አካባቢዎች የነበረ መርሃ ግብር ነው፡፡ ከትምህር ቤት መማሪያ ክፍሎች ውጭ ባሉ ቦታዎች በጸሀይ ብርሃን በሚሰሩ ሬዲዮዎች ጭምር ትምህርት ይሰጥ ነበር፡፡” ብሏል፡፡
“ጦርነት በደቆሳቸውና በተራዘመ ቀውስ ውስጥ በሚገኙ እንደ አፍጋኒስታን፣ የመን እና ኢትዮጵያ ውስጥ “ትምህርት አይቆይም” የሚለው መርሃ ግብር ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የተዘነጉና የተጎዱ ህጻናትንና አዋቂዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ይረዳቸዋል፡፡” ሲልም ርዕሰ አንቀጹ አስታውቋል፡፡
“ዩናይትድ ስቴትስ ትምህርት አይቆይም የሚለው መርሃግብር ከተጀመረበት እኤአ 2016 ጀምሮ በታላቅ ኩራት ደግፈዋለች” ያሉት ሰማንታ ፓወር የሚከተለውን አክለዋል፡፡
“የትምህርት ተደራሽነትንና፣ የትምህርት ውጤታማነትን ለማሳደግ፣ የተገለሉ ተማሪዎችን፣ በተለይም ሴቶችን፣ ስደተኞችን፣ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን፣ የጾታና ንኡሳን የወሲብ ማህበረሰብ አባላትን፣ የአካል ጉዳተኛ ህጻናትን ተሳትፎ እንዲያድግ፣ የምናደርገውን ጥረትና ትብብር እንቀጥላለን፣”
በመጨረሻም፣ “የትምህር ተደራሽነት ከትምህርት ጥራት ጋር እኩል ሲሆን፣ ውጤቱ ግልጽ ነው፡፡ ትልቅ የምጣኔ ሀብት እድገት፣ የተሻሻለ የጤና ውጤት፣ ጠንካራ ዴሞክራሲ፣ ይበልጥ ሰላማዊ የጠነከረና ሁሉንም መቋቋም የሚችል ማህበረሰብ፣ ጤናማናይበልጥ የተሳካላቸው ህጻናትንም ይፈጥራል፡፡ ያሉት አስተዳዳሪዋ ሰማንታ “ዓለም ልዩ ችሎታና ብቃት ያላው ትውልድ እንዳያመልጠው፡ እርግጠኞች እንሁን” ብለዋል ሲል ርዕሰ አንቀጹ ጽሁፍን ደምድሟል፡፡