Accessibility links

Breaking News

በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁጥሩ 274 ሚሊዮን የሚገመት የአደጋ ጊዜ እርዳታ ይፈልጋል


በሚቀጥለው ዓመት ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁጥሩ 274 ሚሊዮን የሚገመት ሰው የሆነ ዓይነት የአደጋ ጊዜ እርዳታ ይፈልጋል።” ሲል ይንደረደራል የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ።

አዲስ የጀመርነውን የአውሮፓውያኑን 2022 ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ይዞታ ለመገምገም በቪዲዮ አማካኝነት በተካሄደ ሥነ ስርዓት የዩናይትድ ስትቴስ ዓለም አቀፍ የተራዶ ድርጅት አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ሲናገሩ “ለድህነት እና ስቃይ የተጋለጡ ሰዎች ቀድሞ በብዛት ይታዩባቸው ከነበሩ አካባቢዎች ይልቅ ግጭቶች ወደ በዙባቸው ሥፍራዎች ተዛውረዋል።” ሲሉ የገለጹትን የጠቀሰው ርዕሰ አንቀጽ “በመሆኑም እኛም ትኩረታችንንን .. የት ማድረግ አለብን ሳይሆን ከማን ጋር ሃጋር መሆን አለብን በሚል ቀይረናል።” ያሉትን አውስቷል።

"ይህም ማለት የቀይ መስቀል ወይም ቀይ ጨረቃ ቅርንጫፍ ይሁን ወይም ሌላ፤ በምንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች ማህብረሰብ ውስጥ መሰረት ያላቸው እና የተለያዩ ሥራዎችን የሚሰሩ የአካባቢ ሕብረተሰብ እንቅስቃሴ አራማጆች፣ ተቀባይ መንግስታት እና የዕምነት ተቋማትን አቅም ማጠናከር እና ማሳደግ ሊሆን ይችላል። ብለዋል።

“ይህም የዓለማችን እጅግ አስጨናቂ ቀውሶች በሚታዩባቸው እና በግንባር ቀደምትነት የተሰለፉ ነገር ግን በአብዛኛው የሚዘነጉ በሴቶች የሚመሩ ድርጅቶች ዕውነታ ነው።” ሲል ርዕሰ አንቀጹ ያብራራል።

"በአብዛኛውም በጣም የተቸገሩትን ፈልገው ለማግኘት የሚጥሩ፤ ያለውን ሃብት እና እሴት በብቃት አገልግሎት ላይ እንዲውል የሚያደርጉ ሴቶች ናቸው። ይሁንና የሰብዓዊ ዕርዳታ የሚከፋፈልበትን መንገድ አስመልክቶ እና ማን ተጠቃሚ መሆን እንዳለበት ዕቅድ በሚነደፍበት ወቅት ግን በአብዛኛው ቦታ አይሰጣቸውም። የአካባቢ ድርጅቶች በተለይም በሴቶች የሚመሩ ተቋማት ከጅምሩ እንዲሳተፉ መደረግ አለባቸው። የሰብአዊ አገልግሎት ፕሮግራሞች በሚቀረጹበት እና በሚተገበሩበት ሂደት የትኩረት ማዕከል መሆን አለባቸው።" ብለዋል።

ርዕሰ አንቀጹ አያይዞም "የዓየር ንብረትን የመቋቋም አቅም ለመገንባት እና ከአካባቢው ሁኔታ ጋር መስማማት የሚያችል መንገድ ለመፍጠር የታለመ ሥራም ተመሳሳይ ነው" ሲሉ አስተዳዳሪዋ የተናገሩትን ያመለክታል።

“በዓለም አቀፍ ደረጃ የዓየር ንብረት መቃወስን ለመቋቋም የሚያግዝ አቅም ለመገንባት ከአካባቢ ማህበረሰቦች ጋር በምንሰራበት ወቅት፣ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ፕሮግራሞችን መንደፍ እና ተግባራዊ ማድረግ በሚያስችል ስልታዊ መንገድ ማሰብ አለብን። " ብለዋል።

እንዲህ ያሉ በቅጡ የታሰበባቸው እቅዶች ውጤታቸው በራሱ አንደበት አውጥቶ ስለምንነቱ ይናገራሉ። ለምሳሌም ያህል እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1998 ዓ.ም ሚች የሚል ሥያሜየተሰጠው እጅግ ከባድ አውሎ ነፋስ ሆንዱራስ እና ኒካራጓን አቋርጦ የ6 ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ የሆነ አካባቢ ባካለለበት ወቅት ከ10,000 በላይ ሰዎችን ህይወት አጠፋ።

ይህንንም ተከትሎ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ተራዶ ድርጅት በአካባቢ አስተዳደር፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያ፣ አካባቢን ለቆ መውጣት በሚያስፈልግበት ወቅት ለአገልግሎት የሚውሉ እና እንዲሁም ለግንኙነት የሚያስፈልጉ አሰራሮችን፤ ከዚህም በተጨማሪ ለሰዎች ሕይወት እና ኑሮ ጥበቃ የሚያግዙ፣ ለዓየር ንብረት አያያዝ የሚበጁ መሠረተ ልማቶች ላይ የመዋዕለ ወጭ አድርጓል።

“በዚህም ሳቢያ” ርዕሰ አንቀጹ ይቀጥላል። “በዚህም ሳቢያ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2020 ዓም ከዚያ ከፍተኛ ዕልቂት ካስከተለው ‘ሚች የተሰኘ አደገኛ አውሎ ነፋስ የሚወዳደር አውዳሚ አቅም የነበራቸው እና ተመሳሳይ አካባቢ አቋርጠው ተምዘግዝገው የደረሱት ‘ኤታ’ እና ‘ኢዮታ’ የሚል ሥያሜ የተሰጣቸው ሁለት ከባድ አውሎ ነፋሶች አማካኝነት በአደጋው የጠፋው ህይወት ቁጥር ወደ 205 ዝቅ ሊል ችሏል።

በግልጽ እንደታየውም የአደጋ ስጋት ቅነሳ ሥራዎችን በሚነደፉበት ወቅት የአካባቢውን ማህበረሰብ ማሳተፍ ፍሬያማ ውጤት ለማግኘት እንደሚያግዝ ተረጋግጧል።

“ስለዚህም” አሉ የዩኤስኤአይዲዋ አስተዳዳሪ ፓወር። “ስለዚህም ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ድርጅቶች ሙሉ ተሳትፎ፣ ዕቅድ ቀረጻ እና አመራር ለማካተት ከአካባቢ ማሕበረሰብ፣ ሴቶች እና የተገፉ ወይም የተገለሉ ወገኖች ድረስ በገዛ ማህበረሰባቸው ውስጥ ለሚገጥሟቸው አደጋዎች በእርግጥ ዘላቂ የሆኑ መፍትሄዎችን ለማጎልበት የሰብአዊ ርዳታ የምናቀርብበትን መንገድ መቀየር አለብን።” ሲሉ የተናገሩትን ጠቅሶ የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ ሃተታውን ደምድሟል።

XS
SM
MD
LG