Accessibility links

Breaking News

የማርቲን ሉተር ኪንግ ቀን 2022


የቄስ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ /ጁኒየር/ በዓል በሚከበርበት ግዜ ግለሰቡ በመታሰቢያው ስፍራ ሲያልፍ
የቄስ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ /ጁኒየር/ በዓል በሚከበርበት ግዜ ግለሰቡ በመታሰቢያው ስፍራ ሲያልፍ

በአውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በየዓመቱ ወርሃ ጥር በገባ በሦስተኛው ሰኞ አሜሪካውያን የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየርን መታሰቢያ ይዘክራሉ።

ዶ/ር ኪንግ በደቡባዊ የዩናይትድ ስቴትሷ አላባማ ክፍለ ግዛት የባፕቲስት ቤትክርስቲያን ቄስ እና የዘር መድልዖ ተቃዋሚ፣ የነጻነት ታጋይ እና መሪ ነበሩ። ሲል ይንደረደራል የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ።

ኪንግ በህይወት ቢኖሩ ኖሮ ባለፈው ቅዳሜ በአውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ጥር 15/2022 ዘጠና ሦስተኛ ልደታችውን ያከብሩ ነበር።

ርዕሰ አንቀጹ አያይዞም ዶ/ር ኪንግ በጊዜው በአንዳንድ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ውስጥ የሚፈጸሙባቸውን የዘር መድሎ ይፈቅድ የነበረ ሥርዓት ለማስቆም በተንቀስቀሱ ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የሚሰነዘረውን አስከፊ ጥቃት ለመታገል የታለመ እና ከግጭት በራቀ

ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረ የሲቪል መብቶች ንቅናቄን መምራታቸውን ያስታውሳል።

ማሃተማ ጋንዲ ያራምዱት የነበረውን በሰላማዊ መንገድ የሚካሄድ የተቃውሞ እንቅስቃሴ አሠራር ከልባቸው የተቀበሉት ዶ/ር ኪንግ በሲቪል መብት ተቃውሞ አድራጊዎች በህብረት የሚከናወኑ የማህበራዊ አገልግሎቶችን ያለመጠቀም ወይም ከተመረጡ የንግድ ድርጅቶች ምርቶችን ያለመግዛት እና ከቤት የመቀመጥ አድማ፣ ሰላማዊ ሰልፍ እና ሌሎች የህዝባዊ እምቢተኝነት ድርጊቶች የሚመሩባቸውን

‘ወደነጻነት የሚደረግ እርምጃ’ በተባለው መጽሃፋቸው የዘረዘሯቸውን ስድስት መርሆዎች አዘጋጁ።” ርዕሰ-አንቀጹ ይቀጥላል።

የመጀመሪያው ከብጥብጥ የጸዳ ተቃውሞ ደፋሮች የሚከተሉት የአኗኗር ዘይቤ እና የክፋት ምግባርን መመከቺያ መሳሪያ መሆኑን ይገልጻል።

ሁለተኛው ደግሞ ነውጥ-አልባ ተቃውሞ የሌሎችን ወዳጅነትን እና መግባባትን ጸጋው ለማድረግ ይሻል። እንዲሁም ቤዛነት እና እርቅን ይፈጥራል።

“የክፋት ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች እርኩስ ሰዎች ሳይሆኑ ራሳቸውም የዚያ የክፋት ሥራ ሰለባዎች መሆናቸውን ስለሚረዳ ነውጥ-አልባ ተቃውሞ የግፍ አድራጎቶችን ለማምከን ይታገላል እንጂ፤ በሰዎቹ ላይ የተነጣጠረ ግብ የለውም።”

አራተኛው መርህ በመከራ ውስጥ ማለፍ ትምህርት ለመቅሰም እና ለመለወጥ እንደሚያግዝ እናም ስቃይን ያለ በቀል እንደሚቀበል ያስረዳል። የማይገባ መከራም ትምህርታዊ እና የመለወጥ እድሎችን እንደሚያጎናጽፍ ያስታወሳል።

በአምስተኛው መርሆም መሰረት፣ ነውጥ-አልባ የነጻነት ትግል ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን ይመርጣል።

በመጨረሻም ስድስተኛው መርህ ድፍን አጽናፈ-ሰማይ ከፍትህ ጎን እንሚሰለፍ ያሳያል።

ማርቲን ሉተር ኪንግ ከመገደላቸው በፊት በነበረው የሳምንት ውስጥ ነው "እናሸንፋለን። ምክንያቱም የትክክለኝነት ሞራል የሚደርስበት አድማስ ረጅም፤ ነገር ግን ወደ ፍትህ ያዘነበለ ነውና!" የሚለውን እና የነጻነት ተስፋቸውን ያዘለ ሃሳብ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ሚያዝያ 31, 1968 ዓም ከዋሽንግተን ዲሲው ብሔራዊ ካቴድራል ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ያመለከቱት።

ለዶ/ር ኪንግ እና ለሚመሩት የሲቪል መብቶች ንቅናቄ ታላቅ ስኬት የተገኘው ግን እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1964 ዓ.ም. በህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ጥቁሮችን የሚያገልለው አሰራር እና እንዲሁም በዘር፣ በቀለም፣ በሃይማኖት፣ በፆታ ወይም በብሄር ማንነት ላይ የተመሰረተ የስራ ዕድል ላይ የሚፈጸምን አድልዎ ሕገ ወጥ ያደረገው “የዜጎች መብት አንቀጽ” በፀደቀበት ወቅት ነው።

እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ሚያዝያ 4, 1968 ዓም ነፍሰ ገዳይ በተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ሲገደሉ፣ ዶ/ር ኪንግ ገና የሰላሳ ዘጠኝ ዓመት ጎልማሳ ነበሩ። ይሁንና በህይወት ዘመናቸው የሰሯቸው ሥራዎች ሕያው ሆነው ይቀጥላሉ። በተከተሉት አስር ዓመታት ውስጥም በጊዜው የነበሩት አግላይ ህጎች ተሻሩ። እናም ዛሬ መድልዎ የተወገዘ እና በህግ የሚያስቀጣ ወንጀል ሊሆን በቅቷል።

የማርቲን ሉተር ኪንግም ህይወት “የሰው ልጅ የመጨረሻው መለኪያ በምቾት እና ሲያመቸው ብቻ በሚቆምለት መርህ ሳይሆን በፈተና እና ውዝግብ በተቀሰቀሰ ጊዜ ጭምር ላመነበት ዓላማ መቆም መቻሉን ሲያስመሰክር ነው” ሲሉ ራሳቸው የተናገሩት አባባል በሚታይበት መነጽር ሊመረመር ይችላል።

"ሥራቸው እንደሚያሳየው እርሳቸው ግን ያን ምርጫ ሲያደርጉ አይገኙም።” ሲል በጥቁሮች መብት ታጋዩ ማርቲን ሉተር ኪንግ መታሰቢያ ላይ ያተኮረው የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ ሃተታውን ደምድሟል።

XS
SM
MD
LG