Accessibility links

Breaking News

ቻይንና በተለያዩ መልኮች


የህዝባዊት ሪፐብሊክ ቻይና በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ “በክልሏም ይሁን ከዚያ ውጭ ባሉጉዳዮች ከጊዜ ወደጊዜ ድምጿን በልዩ ልዩመንገድ አጉልታ በኃይል የምታሰማ አገር እየሆነች ነው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ፍራን ኢዝነስታት እና ኢዘንስታት ፋሚሊ ሜሞሪያል በተባለው ዓመታዊ መድረክ ላይ ተናግረዋል ይላል ርዕሰ አንቀጹ ሀተታውን ሲጀምር፡፡፡

ዩናይትድ ስቴት የህዝባዊ ሪፐብሊክ ቻይንና የምታየው በሦስት የተለያዩ መልኮች ሲሆን እንደ ተፎካካሪ ተባባሪ ወይም ጠላት አገር አድርጋ መሆኑን ብሊነክን ገልጸዋል፡፡ ያለው ጽሁፍ ብሊንክን “ከአጋሮቻችን ጋር የምንሰራውን ስራ በቅንጅት ካደረግነው በእነዚህ እያንዳንዱ ነገሮች የተሻለ፣ የበለጠና ውጤታም ሥራልንሰራ እንችላለን” ብለዋል፡፡

“በዓለም አቀፍ መድረክ ካሉ ተቋማት ጋር ግንኙነታችንና ትብብራችንን የበለጠ በማደስና በማጠናከር ላይ ያተኮርንበት ዋናው ምክንያት ቻይናን በሚመለከት የሚደረገውን ነገር ሁሉ አብረን እንድናደርግ ነው፡፡ እንደ ዩናይትድ ስቴትስ እንኳ ሆነን ቢሆን ለብቻችን ከምናደርገው ጥረት የተባበረና የተጣመረው ጥረታችን የበለጠ ክብደት ይኖረዋል፡፡”

ጽሁፉ በመቀጠል ብሊንከን ከአጋሮችችን ጋር በምናደርገው ትብብር በተለይም ከህዝባዊት ሪፐብሊክ ቻይና ቤልት ኤንድ ሮድወይም የቀለበት መንገድ ከተባለው ፕሮጀክት ተነሳሽነት ስምለምታራምደው ፕሮጀክት አማራጮችን ማቅረብ ነው፡፡ ማለታቸውን ጠቅሷል፡፡ ይህ የመሰረተ ልማት ሥምምነት በተለያዩ ዓለም ክፍሎች ላሉአገራት የእዳ ሸክም መሆኑን ብሊንከን እንዲህ ሲሉተናገረዋል፡፡

“አንዱ ችግር ይሄ በመሰረተ ልማት መስክ በሚፈሰው መዋዕለ ንዋይ አንጻር እየተመለከተን የምናደርገው ነገር ነው፡፡ ይህ ግንአገሮችን እጅግ ግዙፍ በሆነ የእዳ ጫናተብትቦ መውጫ እንዳይገኙ ማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም እዳቸውን መክፈል ያልቻሉ አገሮች ከሌሎች የምጣኔ ሀብት ምንጮቻቸው እየወሰዱ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ይሆናል፡፡ መጨረሻው ዞሮዞሮ የሚሆነው አገሮች ሲከስሩ ቻይና ያለውን ሀብታቸውን ትወርሳለች፡፡”

ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠል የህዝባዊ ሪፐብሊክ ቻይና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ስትሰራ የራሷን ሠራተኞ ይዛትመጣለች፡፡ ይህ ደግሞ የአገሬዎቹን ሠራተኞች ያስከፈላል፡፡ ብሏል፡፡

በቻይና ፕሮጀክቶች ላይ የሚሰሩም የአገሬው ሠራተኞች እጅግ አደገኛ በሆነው የሥራ ሁኔታ ውስጥ እንዲሰሩ ይገደዳሉ፡፡ ለመደራጀት ስለማይፈቅድላቸው ለተለያዩ የግዳጅ ሥራዎች ይዳረጋሉ፡፡ የሚገነቡ ነገሮችም ደረጃቸውን ያልጠበቁ ከመሆናቸውም በላይ ለአካባቢው አየርና ተፈጥሮ ክብር የሚሰጡ አይደሉም ሲል የርዕሰ አንቀጹ ጽሁፍ አመልክቷል፡፡

ለዚህ ምላሽ ለመስጠት ዩናይትድ ስቴትስ እናተባባሪዎችዋ የተሻለ ዓለምን መልሶ መገንባትን ጀምረዋል፡፡ ሲል ርዕሰ አንቀጹ አትቷል፡፡

ይህ ከበለጸጉት የቡድን ሰባት አገሮችና ሌሎች ጋር የሚከወን ሲሆን በመላው ዓለም የተሻለ የመሰረተ ልማት ለመገንባትና አገልግሎቱ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉየተሻለ አማራጭ ሊሆን የሚችል ነውሲልም ጽፏል፡፡

በመጨረሻም ዩናይትድ ስቴትስ ከአጋሮችዋና ተባባሪዎችዋ ጋርበመሆን ህዝባዊ ሪፐብሊ ቻይናን በማሳተፍ ካልሆነም አስፈላጊ በሆነ ጊዜሁሉ በመቋቋምና በመከላከል ለመስራት ቁርጠኛ ነችሲል ርዕሰ አንቀጹ ጽሁፉን ደምድሟል፡፡

XS
SM
MD
LG