Accessibility links

Breaking News

የፕሬዚዳንቶች ቀን


የፕሬዚዳንቶች ቀን
የፕሬዚዳንቶች ቀን

በየዓመቱ የካቲት ወር በገባ የመጀመሪያው ሰኞ ላይ አሜሪካውያን የፕሬዚዳንቶች ቀንን ያከብራሉ፡፡ የክብረ በዓሉ ሀሳብ ሲጸነስ የመጀመሪያውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆር ዋሽንግተንን በማሰብ ነበር፡፡ እኤአ በ1800ዎቹ እሳቸው ከሞቱ በኋላ በእሳቸው እገዛ ለመጀመሪያ ጊዜ በተመሰረተችው መላው አገራቸው ውስጥ የልደት በዓላቸው እኤአ የካቲት 22፣ ይፋ ባልሆነ መልኩም ቢሆን ሲከበር ቆየቷል፡፡ ከጊዜ በኋላ ደግሞ ለመሪዎቹ የሚሰጠው ክብር ወደ ሌላኛው ታላቅ መሪ ወደ አብርሃም ሊንክን ተሸጋግሮ፣ የሳቸውም ልደት ከጆርጅ ዋሽንግተን ጋር ተቀራራቢ በሆነው እለት እኤአ የካቲት 12 መከበር ተጀመረ፡፡

ጆርጅ ዋሽንግተን እና አብርሃም ሊንከን እስከዛሬ የፕሬዚዳንትነቱን ሥልጣን ከያዙት ውስጥ ልቀው የሚታሰቡ ሁለቱ ምርጥ ፕሬዚዳንቶች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ ይህ የሆነው፣ አንድም እነሱ በነበሩበት ዘመን በተፈጸሙ ታላላቅ ሁነቶች ሳቢያ ነው፡፡ እንዲሁም እያንዳንዳቸው አገሪቱን ወደ ጥንካሬ፣ ወደ ብልጽግና፣ እና ወደ ዴሞክራሲ ጎዳና በመምራት፣ በወሰዷቸው ዘላቂ ውሳኔዎችና የግል አመራራቸው ብቃት ነው፡፡

ጆርጅ ዋሽንግተን፣ በጊዜያቸው እጅግ ታዋቂና ተወዳጅ የነበሩ ሰው ነበሩ፡፡ ያለምንም ልዩነት የሁሉንም ክፍለ ግዛት ድምጽ በማግኘት በሙሉ ድምጽ የተመረጡ ብቸኛው ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ ዋሽንግተን በፕሬዚዳንትነት ሲመረጡ ለሳቸው አርአያ ሊሆን የሚችል ምንም ዓይነት መንግስትም ሆነ መሪ ከፊታቸው አልነበረም፡፡ በየትኛውም የዓለም ክፍል ምንም ዓይነት ዴሞክራሲ አልነበረም፡፡ ይሁን እንጂ ጦርነቱን እንዲያሸነፉ የረዷቸውንና በየትኛውም ስፍራ ያሉ ሁሉም ሰዎች እኩል መብት አላቸው የሚለውን መርህ እንዲወጣ አግዘዋል፡፡ መንግሥት የሚታነጽበትን መርህና አሰራር የሚገልጸውንና የዜጎች መብት የሚከበርበትን ህገ መንግሥት እንዲቀረጽና እንዲመሰረት ካደረጉ ኃይሎች መካከል አንደኛው ነበሩ፡፡ በራሳቸው ተግባር አርአያ በመሆን የፖለቲካና ወታደራዊ አሰራር ደንብ እንዲወጣና የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ እንዲቀረጽ አስችለዋል፡፡ የፕሬዚዳንትነት ሥልጣን የዕድሜ ልክ ሥልጣን አለመሆኑን ለማሳየት ሁለት ዙር ካስተዳደሩ በኋላ ከሥልጣናቸው በመውረድ ፕሬዚዳንታዊ ሥልጣን በሰላማዊ ሽግግር መተላለፍ የሚችል መሆኑን አሳይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት አብርሃም ሊነክንም ወደ ሥልጣን የመጡበት ጊዜ፣ አገሪቱ በቀውስ መካከል በነበረችበት ወቅት ነበር፡፡ ዋሽንግተን አዲስ አገረ መንግሥት ለመመስረት በምትጥርበት ወቅት፣ አብርሃም ሊንከን በገጠማት የርስ በርስ ጦርነት ለመፈራረስ ከጫፍ የደረሰችውን አገር ከውድቀት በማዳን ፣ ወደ ጠነከረችና ከመቸውም ጊዜ በላይ አንድነቷ ወደ ተጠበቀ አገር እንድትሸጋገር አድርገዋል፡፡ አብርሃም ሊንከን ባልጠነከረና ልቅ በሆነ የክፍለ ግዛቶች ፌዴሬሽን ህብረት የቆመው ደካማ ማዕከላዊ መንግሥት፣ እውነተኛ ህብረት ወደ ተረጋገጠበት ጠንካራ የፌዴራል መንግሥት የሚሸጋገርበትን አዲስ ዘይቤ ያሳዩ መሪ ነበሩ፡፡

ዛሬ የፕሬዚዳንቶች ቀን የሚከበረው ያንን የፕሬዚዳንት ሥልጣን የጨበጡና አመራር የሰጡ ሰዎችን ሁሉ ለማክበር ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንዳቸውም ቢሆኑ ከዋሽንግተንም ሆነ ከሊንክን ልቀው የተከበረ ሥፍራ ያላቸው አይደሉም፡፡

XS
SM
MD
LG