Accessibility links

Breaking News

ፑቲን መስሏቸው ነበር


ፎቶ ፋይል፦ ፕሬዚዳንት ባይደን የሃገራቸው ሁኔታ መግለጫ ንግግር ሲያደርጉ እአአ መጋቢት 02/2022
ፎቶ ፋይል፦ ፕሬዚዳንት ባይደን የሃገራቸው ሁኔታ መግለጫ ንግግር ሲያደርጉ እአአ መጋቢት 02/2022

የካቲት 14 የሩሲያው ፕሬዚዳንት ፑቲን የሩሲያ ጦርና የደህንነት አገልግሎት ዩክሬንን እንዲወሩ ትዕዛዝ ሰጡ፡፡ ፑቲን ይህን ሲያደርጉ የሩሲያ ጦር እንደከዚህ ቀደሙ የዩክሬንን ድንበር ጥሶ ሲገባ የሚገጥማቸው ዓለም አቀፍ ተቃውሞ መጠነኛ እንደሚሆን ገምተው ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ዩናይትድ ስቴትስና አጋሮችዋ ለረጅም ጊዜ የሩሲያ የደህንነት ስጋት አስመልከቶ ለመነጋገር የተደረገውን የዲፕሎማሲ ጥረት ተከትሎ ትልቅ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ጠናካራና ዘርፈ ብዙ እርምጃ ወስደዋል፡፡ ፑቲን ስሌታቸው ትክክል አልነበረም፡፡

ብላድሚር ፑቲን የነጻነውን ዓለም መሰረት የሚያናጉ ስለመሰላቸው ለሳቸው የክፋት መንገድ የሚንበረከክ መስሏቸው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በፍጹም ተሳስተዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ባይደን የካቲት 22 ስቴት ኦፍ ዘዩኒየን በተሰኘው ዓመታዊ ንግግራቸው ፑቲን “ወደ ዩክሬን ዘው ብለው ሲገቡ ዓለም ዝም ብሎ የሚቀጥል አድርገው ወስደውታል፡፡ ምዕራቡ ዓለም እናኔቶ ምን እምርጃ የማይወስዱ አድርገው ቆርጠውታል፡፡ እኛንም በቤታችን የሚከፋፍሉን መስሏቸዋል፡፡ ፑቲን ተሳስተዋል፤ እኛ ዝግጁነን፡፡” በማለት ተናግረዋል፡፡ ባይደን፡፡ አያይዘውም እንዲህ አሉ

“በሚገባና በጥንቃቄ ዝግጅት አድርገናል፡ ፑቲንን ለመጋፈጥ ከአውሮፓ፣ አሜሪካስ፣ እስያና አፍሪካ የረጅም ጊዜ ሥራ በመስራት ነጻነት አፍቃሪ የሆኑ አገራትን ትብብር ገንብተናል፡፡”

ባይደን “ፑቲንምን ሊያደርጉ እንዳቀዱ፣ወረራቸውን በሀሰት እንዴት አድርገው ምክንያት ሊያበጁለት እንደሞከሩ የምናውቀውን ለዓለም አስቀድመን አሳውቀናል፡፡” ብለዋል፡፡ አስከትለውም “የሩሲያን ውሸት በእውነት መክተናል፡፡አሁን ያንን ስለፈጸሙ ነጻው ዓለም ተጠያቂ ያደርጋቸዋል፡፡” በማለት የሚከተለውን ተናግረዋል፡፡

“ትልቁን የሩሲያ ባንክ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ስርዓት ነጥለናል፡፡ የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የወደቀውን የሩሲያን ሩብል መከላከል እንዳይችል በማድረግ የፑቲን 630 ቢሊኒዮን ዶላር የጦርነት ፈንድ ዋጋ እንዲያጣ አድርገናል፡፡ የሩሲያን የቴክኖሎጂ አቅርቦት በመቁረጥ ምጣኔ ሀብቷና የመከላከያ በጀቷት ለመጭዎቹ ዓመታት እንዲዳከም አድርገናል፡፡”

ሩሲያ የበለጠ እንድትነጠል፣ ምጣኔ ሀብቷ እንዲገታ ለማድረግ የአሜሪካን የአየር ክልል ዘግተንባቸዋል፡፡የሩሲያን ከበርቴዎችና ሙስና ውስጥ የሚገኙ የአገዛዙን ቡድን አባላትና መሪዎች በክፋት ያካበቱትን ሀብት በሙሉ ኢላማ አድርገናል፡፡ በዚያው መጠንም የሩሲያን ወረራ በጀግንነት እየተዋጋላለው የዩክሬንን ህዝብ አቅም እያጠናከርን ነው፡፡

“ከአጋሮቻችን ጋርበመሆን ዩክሬናውያን ለነጻነታቸው እንዲታገሉ የሚያስፈልጋቸውን እግዛ እያደረግን ነው፡፡ ወታደራዊ ድጋፍ፣ የምጣኔ ሀብት እና ሰብአዊ ድጋፍ እየሰጠን ነው፡፡ ለዩክሬን ከ1ቢሊዮን ዶላር በላይ የቀጥታ ድጋፍ ሰጥተናል፡፡ ዩክሬናውያን ለነጻነታቸው መታገሉን እንዲቀጥሉና ስቃያቸውን ለማቅለል የምንሰጠውን ድጋፍ እንቀጥልበታለን፡፡”

“በእስከዛሬው ታሪካችን ይህን ተምረናል፡፡አምባገነኖች ለሚያደርጉት ጠበኝነት ዋጋ የማይከፍሉ ከሆነ የበለጠ ቀውስ ይፈጥራሉ፡፡” ያሉት ባይደን “ፑቲን ጥቃትና ቀውስ መፍጠር ጀምረዋል፡፡ በጦር ሜዳ የሚያገኙት ድል ሊኖር ይችላል፡፡ ለዚያ ግን ለረጅም ጊዜ የሚከፍሉ ትከፍተኛ ዋጋ ይኖራል፡፡” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG