Accessibility links

Breaking News

ዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ የኬንያ ባለሥልጣንን በሙስኝነት ፈረጀች


ዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ የናይሮቢ ገዥ የነበሩት ማይክ ሶንኮ ጉቦንና መጠቃቅምን ጨምሮ በሙስና ውስጥ በነበራቸው ጉልህ ተስታፎ ተጠያቂ አድርጋ በጥፋተኝነት ፈርጃቸዋለች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ በሰጡት መግለጫ ሶንኮ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ለወዳጆቻቸው የመንግሥት ኮንትራክ አሳልፈው ሰጥተዋል ብለዋል፡፡ ይህ ድርጊታቸው የህግ የበላይነትና የኬንያ ህዝብ በአገሪቱ የዴሞክራቲክና ህዝባዊ ተቋማት ላይ ያለውን አመኔታ የጣሰ ነው ብለዋል፡፡

የሶንኮ የቅርብ ቤተሰቦች ባለቤታቸውን ፕራይሞር መቡቪና ልጃቸውን ሶንኮ ጨምሮ ተጠያቂ አድርጓቸዋል፡፡ ስለሆነም ውሳኔው በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ኦፕሬሽን እና ተዛማጅ ፕሮግራሞችና ጥቅማ ጥቅሞች ድንጋጌ 7031/ሲ መሰረት ሶንኮ እና የቅርብ ቤተሰባቸው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት የማይችሉ አድርጓቸዋል፡፡

በቅርቡ የወጣው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰብአዊ መብቶች ሪፖርት እንዳመለከተው በኬንያ በሁሉም የመንግስት እርከኖች ሙስና ትልቁ ጥፋት ሆኗል፡፡ ማይክ ሶንኮ እኤአ በ2019 በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የተከሰሱ ሲሆን እኤአ በ2020 ከናይሮቢ ገዥነታቸው በፈጸሙት ከባድ የስነምግባር ጉድለትና ሥልጣናቸው አላግባብ በመጠቀም ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገዋል፡፡ እስካሁን ገና ለፍርድ አልቀረቡም፡፡

እንደ ዓለም አቀፉ የግልጽነት ተቋም ትራንፓረንሲ ኢንተርናሽናል፣ ኬንያ ከ180 አገሮች በሙስና 128ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ “ሙሰኞችን ለፍርድ የማቅረብ ሂደቱ አዝጋሚ መሆንና በፍርድ ቤቶች የሚታየው መጓተት ኬኒያውያንን አሁንም ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሙስናን መቋቋም የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ፖሊሲ መሰረታዊ አካል ሆኖ እንዲካተት አድርገዋል፡፡ ዋይት ሀውስ ባወጣው መግለጫ “ሙስና የህዝብን እምነት፣ የመንግሥትን ለዜጎች አንዳች ነገር የማድረግ አቅም የሚበላና የማህበረሰብን ከውስጥ የሚፈጅ ካንሰር ነው” ብሎታል፡፡ መግለጫው አያይዞ “የማኅበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መዛባትን ፈጥሮ ማኅበረሰብን ጽንፍ ለጽንፍ ይከፋፍላል፣ የንግድ አውድን ዝቅ ያደርጋል፣ የምጣኔ ሀብት እድሎችን በመዝጋት ግጭትን ያባብሳል በመንግሥት ላይ እምነት ያሳጣል” ብሏል፡፡ እነዚያ ሥልጣንን ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉ ሰዎች የቁስ ሀብትን ብቻ ሳይሆን የሚሰርቁት የሰውን ክብርና ደህንነትም ይነጥቃሉ ብሏል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ የቀድሞ የናይሮቤ ገዥ ማይክ ሶንኮ እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸው መፈረጅ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በኬንያ ሙስናን ለመዋጋት፣ የህግ የበላይነት ለማስፈንና የዴሞክራሲ ተቋማትን ለማጠናከር የገባችውን ቃል ተፈጻሚነትና ቁርጠኝነት ያረጋግጣል፡፡ በዚህች ክልልም ሆነ በመላው ዓለም ያሉ ሙስኞች ተጠያቂነትን እንዲኖር ለማድረግ ያለንን ሁሉ አቅም እንጠቀማለን” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG