Accessibility links

Breaking News

በምዕራብ ትግራይ የሚፈጸሙ የሰብአዊ ጥቃት ዘገባዎች


የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በኢትዮጵያ ምዕራብ ትግራይ በአማራ ባለሥልጣናት አሁን ድረስ ቀጥሏል ያላቸውን የብሄር ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በእጅጉ የሚያሳስበው መሆኑን በድጋሚ የሚገልጽ መሆኑን ያስታውቃል፡፡ ከእነዚህ ብዙዎቹ በሂዩማን ራይትስ ዎች እና በአምነስቲ ኢንተናሽናል በሰነድ የተመዘገቡ ናቸው፡፡

በተለይም የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ባወጡት መግለጫ “በእነዚህ ሪፖርቶች የተመለከቱ ግኝቶች የዘር ማፅዳት ወደሚለው እያደጉ መሆናቸው አሳስቦናል” ብለዋል፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናልና የሂዩማን ራይትስ ዎች በምዕራብ ትግራይ ዞን በአማራ ክልል አዲስ የተሾሙት አስተዳዳሪ፣ የክልሉ ባለሥልጣናትና የደኅንነት ኃይሎች ጦርነቱ ከተጀመረበት እኤአ ህዳር 2020 ጀምሮ የትግራይ ተወላጆች በሆኑ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በክልሉ በሚካሄደው የዘር ማፅዳትና በሰብአዊነት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎችና ጦር ወንጀሎች የተካሄዱ መሆኑን ደምድመዋል፡፡

ቃልአቀባዩኔድ ፕራይስ

“በምዕራብ ትግራይ በሺዎቹ የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በዘፈቀደ እየተያዙ ለህይወታቸው አስጊ በሆነ ሁኔታ ይታሰራሉ፡፡ ሰዎቹ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ እያሳሰብን ዓለም አቀፍ ተመልካቾች እስር ቤቶቹን ሁኔታ እንዲመለከቱ አግባብ ያለው ሥልጣን እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን፡፡” ብለዋል፡፡

ይህ “አቋማችን እንደሆነ ጸንቶ ይቀጥላል” ያሉት ሚስተር ፕራይስ፣ ተአማኒ የሆነ ምርመራ ተደርጎ በየትኛውም ወገን ቢሆን ለተፈጸመው ግፍ ተጠያቂነት እንዲኖርና ለቀውሱ ዘላቂ መፍትሄ እንዲኖር አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግሥትት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባለሙያዎች ጋር እንዲተባበር እናሳስባለን ብሏል፡፡

“እየቀጠሉ ያሉት የግፍ ዘገባዎች ወታደራዊ ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆሙ የሚያሳስቡ ናቸው፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በኢትዮጵያ ግጭቱ እንዲቆም በኢትዮጵያ መንግሥት እና በትግራይ ክልል ባለሥልጣናት መካከል የተገለጸውን ሥምምነት እሱንም ተከትሎ የነፍስ አድን እርዳታ የጫነው የተሽከርካሪ ቡድን ከቦታው መድረስ መጀመሩን በደስታ ይቀበለዋል፡፡

ከሥምምነቱ ተግባራዊነት ጋር ዩናይትድ ስቴት ሁሉም የግጭቱ ተዋናይ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚያደርጉትን ጥቃት እንዲያቆሙ በድጋሚ ታሳስባለች፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ኃይሎች ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ እንዲሁም የአገር ውስጥ የደኅንነት ኃይሎችን ከአጎራባች ክልሎች እንዲያስወጡ የድጋሚ ጥሪዋን ታቀርባለች” ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ኔድ ፕራይስ

“ሁሉም ወገኖች የሚያስፈለገውን እርምጃ በመውሰድ የግጭቱን መቆም እንዲያረጋግጡ፣ ያልተገደበ የሰብአዊ ተደራሽነት እንዲኖር እንዲያደርጉ፣ በሁሉም ወገን የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ጥቃቶች ቆመው በመላው ኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኙ” አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG