Accessibility links

Breaking News

በዩናይትድ ስቴትስ በግዳጅ ላይ የተሰው አርበኞች መታሰቢያ ቀን ነው


በግዳጅ ላይ የተሰዉ አርበኞች መታሰቢያ በዓል መታሰቢያ ቀን ወታደሩ የአሜሪካን ባንዲራ በእርሊንግተን በመቃብር ላይ እያስቀመጠ አርሊንግተን፣ ቨርጂኒያ እአአ 26/2022
በግዳጅ ላይ የተሰዉ አርበኞች መታሰቢያ በዓል መታሰቢያ ቀን ወታደሩ የአሜሪካን ባንዲራ በእርሊንግተን በመቃብር ላይ እያስቀመጠ አርሊንግተን፣ ቨርጂኒያ እአአ 26/2022

በግንቦት ወር የመጨረሻው ሰኞ፣ አሜሪካኖች ሀገራቸውን የማገልገል ጥሪ ተቀብለው የተሰው ዜጎቻቸውን ያስባሉ።

"አሜሪካ በውጊያ እና በጦርነት እሳት ተፈትና የተሰራች ናት" ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን "የኛ ነፃነት እና ሌሎች ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሰዎች ነፃነት የተጠበቀው የታሪክን ጥያቄ በተቀበሉ እና ያላቸውን ሁሉ አሜሪካን ለማገልገል በሰጡ ሴቶች እና ወንዶች ነው" ብለዋል።

ሚሞሪያል ዴይ በመባል በየዓመቱ የሚከበረው የአርበኞች መታሰቢያ ቀን ለሀገራቸው ብሄራዊ ጥቅም የወደቁ ዜጎች፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ፍልስፍናዎቿን ለመጠበቅ ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚዘከርበት ቀን ነው።

ሚሞሪያል ዴይ መከበር የጀመረው እአአ በ1860ዎቹ መጨረሻ ሀገሪቱ ከአውዳሚ የእርስ በእርስ ጦርነት መውጣት በጀመረችበት ጊዜ ነበር። እአአ በ1868 ግጭቱ አብቅቶ ሦስት ዓመት ቢያቆጥርም የሚወዷቸውን ሰዎች በሞት የተነጠቁ ሰዎች ቁስል ገና አልሻረም ነበር እና በወቅቱ የአርበኞች ህብረት ቡድን የጦር አዛዥ የነበሩት ጀነራል ጆን ኤ ሎጋን ግንቦት 30 በእርስ በእርስ ጦርነቱ የተገደሉ ከ620 ሺህ የሚበጡ የአሜሪካ ወታደሮች ፣ መቃብሮቻቸውን በአበባ በማስዋብ የሚታሰቡበት ቀን እንዲሆን አወጁ።

ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ የተካሄደውን የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ተከትሎ ግን 'የማስጌጥ ቀን' በብሎ ይጠራ የነበረው ቀን - ሚሞሪያል ዴይ በሚል ስሙ ተቀይሮ ዩናይትድ ስቴትስ በየትኛውም የዓለም ክፍል በተካፈለችባቸው ግጭቶች የተሰው ሰዎች መታሰቢያ ቀን እንዲሆን ተደረገ።

ይህን ቀን አስመልክቶ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ባደረጉት ንግግር "ጦርነት እና ግጭት፣ ሞት እና ማጣት የአሜሪካ ቅርሶች ብቻ አይደሉም። የአሜሪካ ታሪክ አካል ናቸው። እዚህ አርሊንግተን በሚገኘው ብሄራዊ መካነ መቃብር ያረፉት ጀግኖቻችን ፕሬዚዳንት ሊንኮሊን እንዳሉት "የመልካም አገልሎት የመጨረጃውን ደረጃ" የሰጡ ናቸው።" ያሉ ሲሆን

አክለውም "የሞቱት በጌቲዝበርግ ውይም በፍላንደርስ ሜዳ፣ አሊያም በኖርማንዲ የባህር ዳርቻዎች ላይ ብቻ አይደለም፣ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ በአፍጋኒስታን ተራራዎች እና በኢራቅ በረሃማ ስፍራዎችም ጭምር ነው።" በማለት አብራተዋል።

"በዚህ የሚሞሪያል ዴይ መታሰቢያ ቀን ታሪካቸውን እና መስዋዕትነታቸውን እናስባለን" ያሉት ጆ ባይደን "ሀላፊነት፣ ክብር፣ ሀገር፣ - ለነዚህ ኖረው፣ ለነዚህ ሞተዋል። እኛ ደግሞ እንደ ሀገር ለዘለአለም ውለታችውን እናስባለን።" ሲሉ ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG