Accessibility links

Breaking News

ዩናይትድ ስቴትስ የተቀበሩ ፈንጂዎችን አጠቃቀም ገደበች


“ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዓለም ዙሪያ የተቀበሩ ፈንጂዎች አጠቃቀምን ለመገደብ ቁርጠኛ ሆነዋል፡፡ የዚህ ፖሊሲ ለውጥ መኖር፣ ፕሬዚዳንቱ፣ እነዚህ መሳሪያዎች ጦርነቱ ከቆመ ረጅም ጊዜ በኋላ፣ ህጻናትን ጨምሮ በሲቪሎች ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት የተገነዘቡ መሆኑን ያሳያል” ይላል ርዕሰ አንቀጹ ሀተታውን ሲጀምር፡፡

“አዲሱ ስምምነት ከኮሪያ የባህር ሰርጥ ውጭ ያለውን የዩናይትድ ስቴትስን የተቀበሩ ፈንጂዎች ፖሊሲ በኦቶዋ ስምምነት ከተገለጹ ቁልፍ መስፈርቶች፣ እንዲሁም ጸረ ሰው ፈንጅዎችን መጠቀም፣ ማከማቸት፣ማምረት ማሰተላለፍን ከሚከለክለው ዓለም አቀፍ ስምምነት ጋር ይስማማል፡፡” ያለው ርዕሰ አንቀጽ

“በኮሪያ የባህር ሰርጥ ያለው ልዩ ሁኔታና የዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ኮሪያን ለመላከላ ያላት ቁርጠኝነት ዩናይትድ ስቴትስ በአሁኑ ወቅት በኮሪያ ሰርጥ ያላትን የጸረ ሰው ፈንጂዎች ፖሊሲ እንዳትቀይር ይከለክላል፡፡” ሲል አመልክቷል፡፡

“ዩናይትድ ስቴትስ የተቀበሩ ፈንጂዎች አታመርትም፣ አትሰራም ወይም የጸረ ሰዎች ፈንጅዎችን በይዞታነት አትይዝም ወይም አንዳንድ ነገሮችን ለመደምሰስ ወይም የተቀበሩ ፈንጂዎችን ለማስወገድ ካልሆነ የጸረ ሰው ፈንጅዎችን አትጠቀምም፡፡” ሲልም የርእሰ አንቀጹ ጽሁፍ የመንግሥትን አቋም አስታውቋል፡፡

ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠል “ዩናይትድ ስቴትስ ከከኮሪያ የባህር ሰርጥ ውጭ የተቀበሩ ፈንጂዎችን አትጠቀምም ወይም እንዲጠቀሙ አታበረታታም አታግዝም ወይም ከኮሪያ የባህር ሰርጥ ውጭ የኦቶዋ ስምምነት የተከለከሉትን እንዲጠቀሙ አታነሳሳም። ዩናይትድ ስቴትስ የኮሪያን የባህር ሰርጥ ለመከላከል የማይጠቅሙ የጸረ ሰዎች ፈንጂዎችን ክምችት ለማስወገድ ትፈልጋለች፡፡” ብሏል፡፡

“ዩናይትድ ስቴትስ የኦቶዋ ስምምነት እንዲከበር የሚያስችሉ አስፈላጊ ቁሳቁሶችና መፍትሄዎችን ማፈላለጓን ትቀጥላለች፡፡ በዚያው መጠነም ዩናይትድ ስቴትስ ከአጋሮችዋ ጋር የገባችውን ቃል መጠበቅ መቻሏን ታረጋግጣለች፡፡” ሲልም ጽሁፉ አመልክቷል፡፡

የፖሊቲካና ወታደራዊ ጉዳዮች ዋና ረዳት ሚኒስትር ስታን ብራዎን “የዩናይትድ ስቴትስ ድርጊት ሩሲያው ዩክሬን ውስጥ ከምታደርገው ድርጊት ተቃራኒ ነው” ማለታቸውን የጠቀሰው ርዕሰ አንቀጽ፣ ዩክሬን ውስጥ “የሩሲያ ኃይሎች የምድር ውስጥ ፈንጂዎችን ጨምሮ፣ ተቀጣጣይ መሳሪያዎችን፣ ኃላፊነት በጎደለው መንገድ በሲቪሎችና ለሲቪሎች ጠቀሜታ ባላቸው መሠረተ ልማቶች ላይ እጅግ የከፋ ጉዳት ያደርሳሉ” ማለታቸውን ጠቅሷል፡፡

በመጨረሻም ረዳት ዋና ሚኒስትሩ ብራወን በመቀጠል “ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም መደበኛ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን የማስወገድ ርምጃን በመምራቷ ኩራት ይሰማታል፡፡

እኤአ ከ1993 ጀምሮ ከ100 በላይ በሚሆኑ አገሮች፣ ለዓለም አቀፍ ሰላም መስፈንና ደህንነት መረጋገጥ፣ መደበኛ የጦር መሳሪያዎች እንዲወድሙ በሚያደርጉት ፕሮግራምቻችን አማካይነት ከ4.2 ቢሊዮን ዶላሮች በላይ ኢንቨስት አድርገናል፡፡” ብለው መናገራቸውን ገልጾ “አሁንም ሰብአዊነት ላይ ትልቅ ጉዳት የሚያስከትሉትን ጸረ ሰው ፈንጂዎችን ለማስወገድ የምናደርገውን ይህንን አስፈላጊ ሥራችንን በመቀጠል ትብብራችንን እንቀጥልበታለን” ሲል የእለቱ ርዕሰ አንቀጽ ሀተታውን ደምድሟል፡፡

XS
SM
MD
LG