Accessibility links

Breaking News

የዩናይትድ ስቴትስ እርዳታ ለደቡብ ሱዳን


ፎቶ ፋይል፦ ከደቡብ ሱዳን በቦር ከተማ የተፈናቀሉ ሰዎች የምግብ ዕርዳታ ሲያገኙ እአአ 2/21/2022
ፎቶ ፋይል፦ ከደቡብ ሱዳን በቦር ከተማ የተፈናቀሉ ሰዎች የምግብ ዕርዳታ ሲያገኙ እአአ 2/21/2022

“ደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የሰብአዊ እርዳታ በምትፈልግበት ሁኔታ ውስጥ ናት፡፡ ታይቶ ለማይታወቅ የምግብ ደህንነት ዋስትና እጦት ተጋልጣለች፡፡” ሲል ርዕሰ አንቀጹ ሀተታውን ሲጀምር፡፡

“አንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎችም ወደ ከፍተኛ የረሀብ ቸነፈር የመግባት አደጋ ተደቅኖባቸዋል፡፡ ይህ በበርካታ ችግሮች ሳቢያ የተከሰተ ውስብስብ ሁኔታ ነው፡፡” ያለው ርዕሰ አንቀጽ አክሎም፣ “በየቦታው ያሉ ግጭቶች፣ አማካዩ የዝናብ መጠን ከአራት ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ ከተጠበቀው በላይ በመሆን ያስከተለው በ አስርታት ታይትቶ የጎርፍ አደጋ፣ መስኮችን በማጥለቅለቅ፣ ከብቶችን በመፍጀት፣ በመቶ ሺዎችን ማፈናቀሉና፤ በሩሲያው የዩክሬን ወረራ የተነሳ ከውጭ የሚገዛው እህል አጥረት ያመጣው ተጨማሪ ችግር፤ እንዱሁም የተራዘመው የኮቪድ-19 ወረረሽኝ ጉዳት ለችግሩ አስተዋጾ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውን ርዕሰ አቀንጹ ዘርዝሯል፡፡

አያይዞም በዩናይትድ ስቴጽ ዓለም አቀፍ የልማትና ተራድኦ ድርጅት ዩኤስአይዲ የሚመራውና የከፍተኛ ረሀብ አደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስልቶች መረብ፣ የተባለው ተቋም እንዳመለከተው ቁጥራቸው ከ፯ እስከ ፰ ሚሊዮን የሚደርሱ ደቡብ ሱዳናውያን የምግብ እርዳታ ሊያስፈልጋቸው እንደሚችልና ከዚህም ውስጥ ከፍተኛው እርዳታ

የሚያስፈልገው ከሀምሌ እስከ መስከረም ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሆንም ዩኤስአይዲ ማስታወቁን” ጠቅሷል፡፡

“ደቡብ ሱዳን ከሱዳን ተነጥላ ነጻ አገር መሆኗን ይፋ ባደርገች ከሁለት ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተጀመረውና ለአምስት ዓመታት የዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት መጠነ ሰፊ ውድመት፣ በሲቪሎች ላይ የተፈጸመ ከፍተኛ ጥቃት፣ የህዝብ መፈናቀልና የምግብ ምርት መቋረጥን አስከትሏል፡፡” ብሏል ርዕሰ አንቀጹ፡፡

ከእነኚህ መካከል ቁጥራቸው ፸0ሺ የሚደርሱ ዜጎች ባለፉት በርካታ ወራት ወደ ደቡብ ሱዳን ተመልሰው ኑሯቸውን መልሰው

ለመገንባት ጥረት በማድረግ ላይ ሲሆኑ፣ ለዚያ የሚያውሉት ያላቸው ሃብት ግን አነስተኛ ነው፡፡”

ይህ በእንዲህ እንዳለም ቁጥራቸው “አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ተጨማሪ ሰዎች ባለፈው ዓመት በደረሰው የጎርፍ አደጋ የተፈናቀሉ ሲሆን፣ በዚህ ዓመትም እየሰፋ ከመጣው የጎርፉ መውረጃ መንገድ አቅራቢያ የሚኖሩ ሌሎች ቁጥራቸው ስድስት መቶ ሺህ የሚደርስ ሰዎች የመፈናቀል እጣ አንደሚጠብቃቸው ርዐሰ አንቀጹ አመልክቷል፡፡

“የደቡብ ሱዳን ምጣኔ ሀብትም ሆነ የእርሻው ዘርፍ ከጦርነቱ ገና አላገገሙም። ራሷን ለመመገብ የማትችል በመሆኑም ምግብ ከውጭ ማስገባት አለባት። ይሁንና ቀደም ሲል ከዩክሬን ይገቡ የነበሩት እና በመደበኛነት በየዕለቱ ለሚዘወተሩ የምግብ ዓይነቶች መስሪያ የሚውሉ የሰብል ምርቶች ያለመኖር ከፍተኛ የምግብ እጥረት ፈጥሯል፡፡” ያለው የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ

“ደቡብ ሱዳን እስከዛሬ ካየችው ሁሉ ወደ ከፋ የረሀብ ቀውስ ውስጥ እየገባች ነው፡፡” ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያለውን አስታውሷል፡፡

የዩናይትድ ስቴት ስ መንግስት በዩኤስአይዲ አማካይነት ከ፩፩፯ ሚሊዮን ዶላር በላይ ለደቡብ ሱዳን ህዝብ ተጨማሪ የሰብአዊ እርዳታ ማበርከቱን የጠቆመው ርዕሰ ኣንቀጽ “የገንዘብ ድጋፉ ለዓለም አቀፉ የምግብ ድርጅት ፕሮግራም አንደሚላክና ደቡብ ሱዳን ውስጥ በምግብ ቀውሱ ለተጎዱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ አቅርቦት እንደሚውል አስረድቷል፡፡

በመጨረሻም “ደቡብ ሱዳን የተወሳሰበ ቀውስ ውስጥ እያለፈች ባለችበት ባሁኑ ወቅት ዩናይትድ ስቴት ስ ከደቡብ ሱዳን ህዝብ ጎን መቆሟን ትቀጥላለች።

የስነምግባር ግዴታ በመሆኑና የዩናይትድ ስቴ ስን ጥቅም የሚያስጠብቅ በመሆኑ ጭምር በዓለም ዙሪያ በምናደርገው የሰብአዊ እርዳታ ለመቀጠል ቁርጠኞች ነን፡፡” ሲል የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ ሀተታውን ደምድሟል፡፡

XS
SM
MD
LG