Accessibility links

Breaking News

ትኩረት ለዓለም የምግብ ቀውስ


“እኤአ ከ2005 እስከ 2015 በረሀብ አንጀታቸውን እንደቆለፉ በየምሽቱ ወደ መኝታቸው የሚሄዱ ሰዎች ቁጥር በ30 በመቶ በመቀነስ ከነበረበት 805 ሚሊዮን ወደ 590 ሚሊዮን ሰዎች ወርዷል” ሲሉ የዩናትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማትና ተራድኦ ድርጅት አስተዳዳሪ ሰማንታ ፓወር መናገራቸውን ይጠቅሳል የእለቱ ርዕሰ አንቀጽ ሀተታውን ሲጀምር፡፡

ይሁን እንጂ እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቅርብ ዘገባ “ዛሬ እስከ 828 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ረሀብተኞች ናቸው” ብሏል ርዕሰ አንቀጹ፡፡

ሰማንታ ፓወር “ከዚህ ችግር አብዛኛው ክፍል በኮቪድ 19 እና በጣም በቅርቡ ደግሞ ከሩሲያው ተገቢ ያልሆነው የዩክሬን ጦርነት ሳቢያ ነው፡፡ ይህን ነባራዊ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ የሚያንቀሳቅሰው ትልቁ አደጋ ግን የአየር ንብረት ለውጥ ነው “ማለታቸውንም ርዕሰ አንቀጹ ጠቅሷል፡፡

ፓወል አያይዘውም

“የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም ረሀብ ላይ የደቀነው ትልቅ አደጋ ድንገት የመጣ አስደንጋጭ ነገር አይደለም፡፡ ለአንድ ወቅት ብቻ የሚቆይም ድርቅ ሳይሆን ረጅም ጊዜ ለዓመታት የዘለቀ አደጋ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

አስተዳዳሪዋ ፓወል “ረሀቡ በከፍተኛ ደረጃ በትሩን እያሳረፈ ያለው በምስራቅ አፍሪካ ነው” ማለታቸውንም አመልክቷል፡፡

“ሰዎች ይህን ነገር መመዝገብ ከጀመሩበት እኤአ በ1900ዎቹ ጀምሮ የአፍሪካ ቀንድ በተከታታይ ሶስት የድርቅ ወቅቶችን አሳልፋለች፡፡ ይሁን እንጂ ግን እስከዛሬ አካባቢው አራት ተከታታይ የዝናብ ወቅቶችን ሳያገኝ ቀርቶ አያውቅም፡፡”

አሁን ያለው ትንበያችን የሚያመለከተው ብዙ ጊዜ በህዳር የሚመጣው ቀጣዪ የዝናብ ወቅት በጣም አነስተኛ ዝናብ የሚኖረው መሆኑን ነው” ብለዋል ሰማንታ ፓወር፡፡

ይህ የሚያስከትለውን አደጋ ለመከላከል “ዩናይትድ ስቴትስ፣ እርዳታ፣ ኢንቨትመንትና ዲፕሎማሲ ሶስቱ በግንባር እየመራችባቸው ያሉ ነገሮች ቢሆኑም ሊሎቹም በዚህ ዘርፍ፣ በአስቸኳይ ተሳትፏቸውን ከፍ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡” ሲሉ አስተዳዳሪዋ አክለው መናገራቸውንም ተጠቅሷል፡፡

ዛሬ አጣዳፊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የሶማሊያ፣ ኬንያ፣ እና ኢትዮጵያ ህዝቦች ወደ 1.2 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ይፋ አደርጋለሁ፡፡

በአደገኛው የምግብ ቀውስ ብዙ ሰዎች የሚሞቱት ከረሀቡ ይልቅ በበሽታ ነው፡፡ ያሉት ፓወር “ የእርዳታችን አካል በመሆን የተንቀሳቃሽ የጤናና የምግብ ደህንነት ቡድን በከፍተኛ ደረጃ ለታመሙት የሚሰጡትን ክትባትና እንክባቤ ተደራሽነት በፍጥነት ይጨምራሉ፡፡” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ሰማንታ ፓወርል በቀውስ ደረጃ በሚገኝ ችግር ሁልጊዜም እጅግ በጣም ተጎጂ ለሚሆኑ ሴቶችና ልጃገረዶች ልዩ እርዳታ እንሰጣለን፡፡ “ይሁን እንጂ ግን ከምንሰጠው ህይወት አድን የአጣዳፊ የሰብአዊ እርዳታ ውስጥ ባልተመጣጠነ ምግብ ለተጎዱ ህጻናት የምንሰጠው ምናልባት የበለጠ ሊሆን ይችላል፡፡” ማለታቸውንም ርዕሰ አንቀጹ አትቷል፡፡

ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠል አስተዳዳሪዋ “ዩናይትድ ስቴትስ እርዳታው ይበልጥ የሚያስፈልጋቸው የአፍሪካ ቀንድና ሳህልን ጨምሮ ለተባበሩት መንግሥታት ህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ 200 ሚሊዮን ዶላር፣ ልዩ አልሚ የምግብ ንጥረ ነገሮችን ታበረክታለች፡፡” ማለታቸውን ጠቅሷል፡፡

በመጨረሻም “አደጋውን ለማስቆም የሚያስችለን አቅም እያለን ማንም ህጻን ባልተመጣጠነ የምግብ እጥረት መሞት አይገባውም” ያሉት አስተዳዳሪዋ ፓወል፡፡ “ ይህ ረሀብን ለመካለከልና ያልተመጣጠኑ ምግብ ችግሮችን ለማስተናገድ የሚስችለን በጣም ጥሩ ከሆኑ ኢንቨርስትመንቶች በእጃችን ካሉ መሳሪያዎች መካከል አንዱ ነው፣ ለልማትም

XS
SM
MD
LG