Accessibility links

Breaking News

የሰራተኞች ቀን


Carhartt Labor Day "Hard Hats For Hire"
Carhartt Labor Day "Hard Hats For Hire"

ዩናይትድ ስቴትስ በየዓመቱ በመስከረም ወር የመጀመሪያ ሰኞ የሰራተኞች ቀን በመባል የሚታወቀውን ዓመታዊ በዓል ታከብራለች። “እለቱ በሀገሪቱ የሚገኙ ሰራተኞችና ለዩናይትድ ስቴትስ ብልፅግና ያበረከቱት አስተዋፅኦ የሚከበርበት ነው።” ሲል የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ ይንደረደራል።

በማያያዝም፤ የሰራተኞች ቀን ይፋ የበጋው ወራት መገባደጂያ ተደርጎም እንደሚቆጠር ያብራራው ርዕሰ አንቀጽ፤ “በርካታ አሜሪካውያን እለቱን ከሥራ እረፍት በመውሰድ፣ የበጋው ጊዜ ከማብቃቱ በፊት ከቤተሰብ ጋር በመሰባሰብ ከቤት ውጪ ምግብ በማብሰል እና ዋና መዋኘት በመመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች የሚያከብሩት ቢሆንም ዕለቱ በአውደ አመትነት እንዲከበር ያደረጉት ሁነቶች ግን ስስት፣ ህዝባዊ አመፅ እና ደም መፋሰስ የነገሱበት እንደበር፡ ይተነትናል።

በ19ኛው ክፍለ ዘመን መባቻው የእርስ-በእርስ ጦርነቱ ማግት የኢንዱስትሪ መሪዎች በሚል መጠሪያ የሚታወቁት፤ እንደ ኮርኔሊየስ ቫንደርቤልት፣ አንድሪው ካርኒጊ፣ ጄ ፒ ሞርጋን እና ጆን ሮክፌለር ያሉ ባለው ጸጋ እና ከፍተኛ ተጽዕኖ አድራጊ የንግድ ሰዎች፤ በፍጥነት እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚ እና ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መንገድ ያቆለቆለውን የፈጠራ ሂደት እንደ ልብ በሚገኘ የስደተኛ ሰራተኞች ጉልበት የፈጠሩትን እድል ተጠቅመው መጠነ ሰፊ የንግድ ሥራ ለማቋቋም እና ከፍተኛ ሃብት ለማከማቸት ችለው ነበር።

ይህም በወቅቱ በእጅጉ የሚፈለገውን የሥራ እድል እና ዕድሎችን የፈጠረ ቢሆንም የንግድ አሰራራቸው በቃኝን የማያውቅ፣ በየፋብሪካው፣ ብረት ማቅለጫዎች እና የማዕድን ቁፋሮ ሥራ ተጠምደው የሳምንቱን ሰባት ቀናት ለ12 ሰዓታት በመሥራት፣ ነገር ግን ለመኖር የማያስችል ደሞዝ የሚከፈላቸውን ሰራተኞችን ጉልበት የሚበዘብዝ ነበር።

የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ በመቀጠልም እ.አ.አ በ1880ዎቹ መጨረሻ አካባቢ፣ ሰራተኞች ይህን ሁኔታቸውን ለማሻሻል በ18ኛው ክፍለ ዘመን መዋቀር ጀምረው የነበሩ የሰራተኛ ማህበራትን መቀላቀል እንደጀመሩ፤ የተሻለ ክፍያ፣ አያያዝ፣ ደህነቱ የተጠበቀ የስራ ሁኔታ እና እያደገ ለሚገኘው የአሜሪካ ምጣኔ ሃብት ያበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅና እንዲሰጠውም መጠየቅ መጀመራቸውን ያስረዳል።

እነዚህ ጥያቄዎቻቸው መልስ ሳያገኙ ሲቀሩ ታዲያ የስራ ማቆም አድማዎችን ያዘጋጃሉ። ይህ ግን እጅግ አስቸጋሪ እና አደገኛ ጥረት ነበር። በስራ ማቆም አድማው ላይ የሚሳተፉ ሰራተኞች፣ በተደጋጋሚ አናት አናታቸውን ተብለው ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ኩባኛዎች ጠብመንጃ ያነገቱ ወረበሎችን ይቀጥሩ እንደበር ያትታል።አንዳንዴም አድማ አድራጊዎች ላይ ጉዳት ማድረስ ይበረታታ እንደነበር ርዕሰ አንቀጹ ያመለክታል።

እጅግ ጎልተው ከሚነገሩ ይዚህ አይነት አጋጣሚዎች አንዱ በቺካጎ የተካሄደው 'ፑልማን' የተሰኘው አድማ ሲሆን፣ በወቅቱ የፌዴራል ወታደሮች በባቡር ሀዲድ ላይ አድማ ሲያካሂዱ የነበሩ ተሳታፊዎችን እና የፑልማን መኪና አምራች ካምፓኒ የፈፀመውን የደሞዝ ቅነሳ እና ሰራተኛ መበተን ተቃውመው ሰልፍ ያካሄዱ ሰራተኞችን ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በትነዋቸዋል።

በእለቱም 30 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። የሚገርመው ግን አድማው የተካሄደበት ቀን ፕሬዚዳንት ግሮቨር ክሊቭላንድ የሰራተኞች ቀን ብሄራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር የቀረበውን ረቂቅ ህግ እንዲሆን በፊርማቸው ያፀደቁበት ቀን ነበር።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እለቱን አስመልከተው ባደረጉት ንግግር "ጠንክረው የሚሰሩ አሜሪካውያን የሀገራችን የጀርባ አጥንት ናቸው። መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው ህበረተሰብ ነው አሜሪካን የሰራት፣ ማህበራት ደግሞ መካከለኛ የኑሮ ደረጃን ፈጥረዋል።" ብለዋል። አክለውም "መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎችን ህይወት የሚደግፉ ሁሉም ነገሮች የተቻሉት በሰራተኛ ማህበራት በመሆኑ በዚህ የሰራተኞች ቀን ሁሉንም ሰራተኞች እና ኢኮኖሚያችን ወደፊት እንዲራመድ እና ሀገራችን ጠንካራ እንድትሆን በፅናት ያካሄዱትን ትግል እናከብራለን።" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG