Accessibility links

Breaking News

ብሊንከን በዓለም የምግብ ዋስትና ጉባዔ


 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን

በዓለም ዙሪያ ከ200 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በአጣዳፊ የምግብ ዋስትና እጦት እየተሰቃዩ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በቅርቡ በተካሄደው የዓለም የምግብ ዋስትና ጉባኤ ላይ መናገራቸውን በመግለጽ የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ ሀተታውን ይጀምራል።

በግንቦት ወር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 'የተግባር ጥሪ' ሲል ለዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትና ፍኖተ ካርታ ያወጣ ሲሆን አባል ሀገሮቹ፣ የምግብና የግብርና ገበያ ክፍት ማድረግን፣ የማዳበሪያ ምርትን ማሳደግ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ግብርና ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስን ጨምሮ ሰባት እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ ማቅረቡን ርዕሰ አንቀሱ ያመለክታል።

ከ100 የሚበልጡ ሀገሮች በላይ ፍኖተ ካርታውን ተቀብለው የፈረሙ ሲሆን ብዙዎቹ የገቧቸውን ቃል ኪዳኖች ወደተግባር ለመቀየር እየሰሩ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን "እርምጃው ወሳኝ ነው" ማለታቸውን የጠቀሰው ርዕሰ አንቀፅ "ምክንያቱም አሁን ያለው ችግር የትኛውም ሀገር ወይም የሀገሮች ስብስብ ብቻውን ሊፈታው የሚችለው አይደለም" ማለታቸውን አውስቷል።

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባሰሙት ንግግር ዓለም አቀፉን የምግብ ዋስትና ችግር ለመታገል ዩናይትድ ስቴትስ በዚህ አመት ቃል ከገባችው 6.9 ቢሊየን ዶላር በተጨማሪ ከ2.9 ቢሊየን ዶላር በላይ አዲስ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

ነገር ግን አስተዋፅዖ እያደረጉ ያሉት ሁሉም አይደሉም ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን "እጅግ ጥቂቱን አስተዋጽዖ እያደረጉ ካሉት መካከል ብዙ የማድረግ አቅም ያላቸው አንዳንድ ሀገሮች አሉባቸው ፣ ያ መለወጥ አለበት። ሀገሮች እስካሁን ያደረጉት ምንም ያህል ቢሆን አሁንም እያንዳንዱ ሀገር የበለጠ ማድረግ ይኖርበታል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ርዕሰ አንቀፁ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ብሊንከን "ሌላው አፋጣኝ እፎይታን የምንደግፍበት መንገድ፣ እህል እና ሌሎች የግብርና ምርቶች ከጥቁር ባህር ወደቦች ወደ ውጪ ለመላክ ያስቻለውን፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ቱርክ ሸምጋይነት በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የተደረሰው ስምምነት እንዲራዘም በመገፋፋት ነው።" ያሉትን ጠቅሷል።

ሁለተኛው ርምጃ ደግሞ ሀገራት የራሳቸውን ምግብ የማምረት አቅም እንዲያዳብሩ መርዳት ነው ማለታቸውንም አመልክቷል፡፡

"በሚቀጥሉት አምስት አመታት ዩናይትድ ስቴትስ ለዚህ ዘላቂ የግብርና ምርት ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ ለመደገፍ ከምክር ቤቱ ጋር ትሰራለች። ባለፈው ወር ስምንት አዳዲስ የአፍሪካ አገሮችን 'መጪውን ትውልድ እንመግብ' ወደሚለው ፕሮግራማችን ውስጥ ጨምረናል። ይህ የማህበራዊ ደህንነት መረቦችን የምናሰፋበት፣ የምግብ ስርዓቶችን የምናጠናክርበት፣ አመጋገብን የምናሻሽልበት ዋና ፕሮግራማችን ነው።"

በመጨረሻም መንግስታት፣ የክልል አካላት፣ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በጋራ እየሰሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የተሻለ ቅንጅት ሊኖር ይገባል ያለው ርዕሰ አንቀፅ ብሊንከን "ግን ምናልባት ከምንናገረው በላይ በጣም አስፈላጊው ነገር፣ የምናደርገው ነገር ነው።" "የህዝባችን ጤና፣ መረጋጋት እና ደህንነት መሰረት የሚያደርገው በጋራ በምንገነባው የምግብ ዋስትና ላይ ነው" ማለታቸውን ጠቅሶ የዛሬውን ርዕሰ አንቀፅ ጽሁፉን አጠቃሏል።

XS
SM
MD
LG