Accessibility links

Breaking News

በምስራቅ አፍሪካ የጦር መሳሪያ ዝውውር መረብ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ


ፎቶ ፋይል - የሶማሊያ ወታደሮች በሞቃዲሾ
ፎቶ ፋይል - የሶማሊያ ወታደሮች በሞቃዲሾ

“በምስራቅ አፍሪካ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ቡድኖች በሶማሊያ ሰላማዊ ዜጎችን፣ የመንግሥት ሠራተኞችን እና የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን ዒላማ ያደረገ ጥቃታቸውን በመቀጠል በህዝብ ላይ ፍርሃትን በማንገስ ከፍተኛ ውድመት በማድረስ ላይ ናቸው” ሲል ይንደረደራል የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ።

እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ጥቅምት 29/2022 ሞቃዲሾ ላይ ለደረሰው እና ከ100 በላይ ሰዎች ለተገደሉበት፤ በተጨማሪም 300 ያህል ሰላማዊ ዜጎች ለቆሰሉበት አውዳሚ የቦምብ ጥቃት አልሸባብ ኃላፊነት እንደሚወስድ አመልክቷል።ርዕሰ አንቀጹ ይቀጥላል።

አያይዞም የዩናይትድ ስቴትሱ የገንዘብ ነክ እና የሽብር ጉዳዮች ክትትል ረዳት ሚንስትር ብሪያን ኔልሰን ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ “በዚህ አሰቃቂ ጥቃት ዘመዶቻቸውን ላጡ እና ለተጎዱት ሁሉ የተሰማንን ሃዘን እየገለጥን፣ ይህን ምክኒያት አልባ የሽብር ድርጊት አጥብቀን እናወግዛለን” ማለታቸውን ያትቷል።

ርዕሰ አንቀጹ አክሎም ረዳት ሚንስትሩ አገራቸው "በሶማሊያው አይሲስ እና ለአልሸባብ የገንዘብ አለያም ሌላ ድጋፍ በሚያደርጉ የትስስር መረቦች ላይ በቀጥታ የተነጣጠረ እርምጃ ወስዳለች።" ማለታቸውን አውስቷል።

"ዩናይትድ ስቴትስ የአይሲስ-ሶማሊያ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎችን መረብ፣ አጋሮቻቸውን እና ሌሎች የንግድ ድርጅቶችን ለሽብር ቡድኑ በጦር መሣሪያ አስተላላፊነት መፈርጇን ይዘረዝራል።

“በጦር መሳሪያ አዘዋዋሪነት የተፈረጁት ግለሰቦች አይሲስ-ሶማሊያ ከተባለው ከዚህ የሽብር መረብ ጋር በእጅጉ የተሳሰሩ ናቸው። እነዚህ የሕገ ወጥ አዘዋዋሪ መረቦች በዋናነት በየመን እና በሶማሊያ መሃከል የሚሰሩ ሲሆን፤ በአረብ ባሕረ ገብ መሬት ከሚንቀሳቀሰው አልቃይዳ እና ከአልሸባብ ጋር ጠንካራ ግንኙነት አላቸው።” ብሏል።

የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር ኦሳማ አብደልሞንጊ አብደላ በከርን’ም በብራዚል የአይሲስ ቀንደኛ ደጋፊነት ፈርጇል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2016 ዓም የአይሲስ ከፍተኛ አመራሮች ለአሸባሪው ቡድን መሣሪያዎችን እና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን አንዲያፈላልጉ ባከርን እንደታዘዘም ተዘግቧል።

“እነኚህ በድርጊታቸው የተለዩት ወገኖች የባህር ላይ ውንብድናን እና በህገ ወጥ መንገድ አሳ ማስገርን ጨምሮ በተለያዩ ሌሎች የወንጀል ተግባሮች ተሰማርተው መገኘታቸው ISIS-ሶማሊያ ከተለያዩ ህገ-ወጥ ቡድኖች እና በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ሌሎች አሸባሪ ድርጅቶች ጋር ያለው

ቁርኝት የቱን ያህል ስር እንደሰደደ ያሳያል።” ያለው የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ በተመሳሳይ በአሸባሪነት የሰየመውን የሽብር ቡድኑን ቀንደኛ መሪም ጠቅሷል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የካቲት 27/2018 የሽብር ቡድኑን አይሲስ የሶማሊያን እና እንዲሁም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነሃሴ 11/2016 ደግሞ ፕሬዚዳንታዊ ማዘዣ 13224 በሚፈቅደው መሰረት በዓለም አቀፍ አሸባሪነት መዝግቧል።

አይሲስ በአንጻሩ ምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ገንዘብ የሚያገኝባቸውን የተለያዩ መንገዶችን መሞከሩን የጠቆመው ርዕሰ አንቀጽ አያይዞም ቡድኑ በሰላማዊ ሰዎች የሚፈጽመውን የሽብር ጥቃት መቀጠሉን እና የየአካባቢ ማኅበረሰብ አባላትን በማስፈራራት ገንዘብ እንደሚሰበስብ፤ እንዲሁም ምልመላ እንደሚያካሂድ አመልክቷል።

ቡድኑ በተጨማሪም የገንዘብም ሆነ ቁሳቁስ ድጋፍ የማያደርጉ የሶማሊያ ነጋዴዎችን እና ሰላማዊ ዜጎችን ይገድላል፣ መቀጮ ይጥላል፣ያስፈራራል።

ዩናይትድ ስቴትስ የአይሲስ እና የአልሸባብን የገንዘብ ምንጭ ለማድረቅና የሽብር ቡድኖቹን ዕድሜ ለማሳጠር የሚያግዙ እርምጃዎችን በመውሰድ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ አጋሮቿ ጋር ተባብራ መስራቷን ትቀጥላለች።” ሲል የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ ሃተታውን ደምድሟል።

XS
SM
MD
LG