Accessibility links

Breaking News

ዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪካ አገሮች የአየር ንብረት ለውጥ የፈጠረውን ቀውስ ለመቋቋም በመሥራት ላይ ናቸው


ሰሜን ምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ
ሰሜን ምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ

የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ችግር አፍሪካውያን እንዲቋቋሙ እና ፍትሃዊ የሃይል ሽግግርን ለመደገፍ ዩናይትድ ስቴትስ ከአፍሪካ አገራት ጋር አጋርነትን መሥርታለች ሲል የዕለቱ ርዕሰ-አንቀጽ ሃተታውን ይጀምራል።

“የአፍሪካ ሃገራት የአየር ንብረት ቀውስ እንዲፈጠር ያደረጉት አስተዋጽኦ በአንጻራዊ ሲታይ ጥቂት ነው፣ ነገር ግን ቀውሱ ከሁሉ በበለጠ እየጎዳቸው ነው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ተናግረዋል።

የጋራ የሆኑ ዋና ጉዳዮችን ከግብ ለማድረስ እንደ አቻ ሸሪክ በጋራ መሥራት አለብን ብለዋል ብሊንከን። “በቅድሚያ ሥርዓተ-ምእዳሩን ጠብቆ ለማቆየት አብረን መሥራት አለብን፤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት እጅግ አስፈላጊ የሆነውና በዓለም ተወዳጅ የሆነ ሥርዓተ-ምእዳር በአፍሪካ ይገኛል” ማለታቸውን ርዕሰ አንቀጹ ጠቅሷል።

“በኮንጎ ተፋሰስ የሚገኘውን ደን በዘላቂነት ለመንከባከብ፣ ለመካከለኛው አፍሪካ ክልል የአካባቢ ፕሮግራም 600 ሚሊዮን ዶላር መድበናል። ይህም

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትና አፍሪካዊ እንዲሁም አሜሪካዊ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በአንድ ላይ አሳትፏል” ሲሉ አክለዋል ብሊንከን።

ሌሎች ወሳኝ የሆኑ ሥርዓተ-ምድራትን ለመንከባከብ በአፍሪካ መንግስታት፣ በግል ዘርፉና በሲቪል ማኅበረሰቡ መካከል ቅንጅት በመፈጠር ላይ መሆኑን ርዕሰ-አንቀጹ አመልክቷል።

በሁለተኛ ደረጃ፣ በፕሬዚዳንቱ አስቸኳይ የመቋቋሚያና መልሶ ማገገሚያ ፕሮግራም በኩል፣ በማደግ ላይ ባሉ አገራት የሚገኙ ከግማሽ ቢሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለውን ችግር እንዲቋቋሙ ለማገዝ ከሌሎች መንግስታት ጋር አብሮ በመሠራት ላይ ነው።

በሻርም ኤል-ሺክ በተደረገው የኮፕ 27 ስብሰባ ላይ የአየር ንብረትና የውሃ ጥናትን በተመለክተ ያሉትን ክፍተቶች ለመሙላት፤ እንዲሁም በአፍሪካ የቅድመ ጥንቃቄ ሥርዓትን ለመዘርጋት 28.6 ሚሊዮን ዶላር መመደቧን ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቃለች።

በተጨማሪም 24 ሚሊዮን ዶላር ቀጠናዊ የመድኅን አገልግሎትን ለመጀመር፣ 25 ሚሊዮን ዶላር ለምግብ ዋስትና ተነሳሽነት፣ 10 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ መቋቋምንና መልሶ ማገገምን በተመለክተ ትምህርት የሚሰጥበትና በመላ አፍሪካ አቅምን ለመገንባት ያሚያገለግል ማዕከል በካይሮ እንዲጀመር ተመድቧል።

“በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ወደ ንጹህ ሃይል የሚደረገው ሽግግር ፍትሃዊ እንዲሆን አጋርነትን ፈጥረናል” ብለው ተናግረዋል ብሊንከን።

“ወደ ንጹህ ሃይል በሚደረገው ሽግግር፣ አፍሪካ ወሳኝ ቦታን ትይዛለች። በታዳሽ ሃይል ረገድ አፍሪካ ያላት አቅም ተወዳዳሪ የለውም። በንጹህ ኃይል ለሚደገፍ ኢኮኖሚ አስፈላጊ የሆነውን ቴክኖሎጂ ለማሳደግና ታዳሽ ሃይልን ይዞ ለማቆየት ጠቃሚ የሆኑትን እንደ ባትሪ እና የነፋስን ሃይል የሚቀይሩ ማሽኖችን ለማምረት አስፈላጊ የሁኑት ማዕድናትን በተመለከተ በዓለም ካለው ሦስት እጁ የሚገኘው በአፍሪካ ነው” ሲሉ ተናግረዋል ብሊንከን።

ይህን ለመፈፀምም ከሰሃራ ግርጌ የሚገኙና 165 ሚሊዮን ሰዎች ንፁህና አስተማማኝ ሃይል እንዲያገኙ ለማገዝና በአፍሪካ ኃይልን ለማዳረስ በፕሬዚዳንቱ ይፋ የሆነውን ተነሳሽነት ዩናይትድ ስቴትስ በገንዘብ ትደግፋለች።

ዩናይትድ ስቴትስ ሌላ ተጨማሪ 290 ሚሊዮን ዶላር በአፍሪካ ኃይልን ለማዳረስ የተያዘውን ፕሮግራም ለመደገፍ መድባለች።

“እነዚህ ሁሉ ጥረቶች፤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት በምናደርገው ጥረት ልክ እንደሌሎቹ ተግዳሮቶቻችን ወቅት ሁሉ በአፍሪካውያን እንበረታታለን” ያሉት ብሊንከን “በአፍሪካ ይህ ችግር የፈጠረው አደጋ ብቻ ሳይሆን መፍትሄውም ይታየናል” ሲሉ መናገራቸውን ርዕሰ-አንቀጹ በመደምደሚያው አውስቷል።

XS
SM
MD
LG