Accessibility links

Breaking News

የኢንተርኔት ነጻነትን ማስከበር


የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች የምጣኔ ሃብት እድገትን የማፋጠን፣ ግልጽነትንና የመረጃ ተደራሽነትን ማሳደግ፤ ብሎም ሰላምና ደህንነትን የማረጋገጥ አቅም አላቸው። በአንጻሩ አፋኝ መንግስታት ህዝብን ለመቆጣጠር በሚያደርጉት ጥረት፣ የሃሳብ ልዩነቶችንና የመረጃ ፍሰትን ለመገደብ፤ የሀሰት መረጃዎችን ለማሰራጨት እና ተቃዋሚዎችን ለመከታተል፣ እንዲሁም ሳንሱር ለማድረግ በሚያደርጉት ጥረት፡ በህዝባቸው ላይ የመብት ጥሰት ሊፈጽሙ እና ሊበደሏቸው ይችላሉ።” ሲል ይንደረደራል የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ።

ለዚህም ነው እንደ አዎሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2011 ዓም በኔዘርላንድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አነሳሽነት የኢንተርኔት አገልግሎት ነጻነትን የሚያሳካ ጥምረት የተመሰረተው። ዛሬ ያ ጥምረት በአምስት አህጉራት 35 አባላት አሉት።

ርዕሰ አንቀጹ በማያያዝም "የኢንተርኔት ነጻነት ጥምረት የተባለው ይህግ ስብስብ በተለይም በኢንተርኔት እና በዲጂታል አገልግሎቱ መስክ የሰብአዊ መብቶችን መከበር ለማረጋገጥ የምንሰጠውን ድጋፍ ለማረጋገጥ እና ለማራመድ ተግባር ላይ የዋለ ብቸኛ የዓለም ሃገሮች ጥምረት ቡድን ነው" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ የተናገሩትን ያወሳል።

“ዋና አላማው፣ የኢንተርኔት አገልግሎት ማንም ሊገለገልበት እንደሚችል፣ እንደ አመቺነቱ፣ ደህንነቱ እንደተጠበቀ እና እንደ አስተማማኝ ዓለም አቀፍ አውታረ መረብነቱ ለሰው ልጆች የሰጠው ተስፋ እንዲጠበቅ እና ብሎም ሰዎች ከኢንተርኔት መስመር ውጭ ባለው ሕይወታቸው የሰብአዊ መብታቸው እንደሚከበረው ሁሉ የኢንተርኔት አገልግሎት በሚያገኙበትም መስመር ጥበቃው እንዲረጋገጥላቸው ማድረግ ነው።” ብለዋል።

ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠልም፣ “በያዝነው ዓመት የጥምረቱን አመራር ኃላፊነት የተረከበችው ዩናይትድ ስቴትስ ቡድኑ ከተቋቋመበት ከ2011 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊቀመንበርነቱን ሥፍራ መያዟን፣ ጥምረቱ የሰጠውን የኢንተርኔት ተስፋ በማሳካቱ እና ጉዳቶቹን በማቃለሉም ረገድ የበለጠ ውጤታማ በሚያደርግ ሥራ ላይ እናተኩራለን።” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን የተናገሩትን ጠቅሷል።

“በመጀመሪያ መሰል አመለካከት ከሚያራምዱ መንግስታት፣ የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች፣ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ዜጎች ጋር በመሆን የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነትን በማረጋገጥ እና የአገልግሎቱን መስተጓጎል በመከላከል መሰረታዊውን የነፃነት መብቶች በማስጠበቅ ልዩ ተልዕኮ ላይ ትኩረት እናደርጋለን።

"በሁለተኛ ደረጃ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ያለአግባብ መጠቀምን የሚያስከትለውን ጫና የመቋቋም አቅም እንገነባለን" ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሰብአዊ መብቶችን የሚያስጠብቁ መንገዶች መኖራቸውን የሚያረጋግጡ እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ።” ማለታቸውንም ርዕሰ አንቀጹ አውስቷል።

“በሦስተኛ ደረጃ፣ በሰዎች ይሰሩ የነበሩ ሥራዎችን ሰውን ተክተው እንደሚሰሩ ማሽኖች የመሳሰሉትን እየመጡ ያሉትን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንም ሆነ ቀደም

ሲል ጥቅም ላይ የዋሉትን አሰራር የሚደነግጉ ደንቦች ለመቅረጽ ተግተን እንሰራለን።

በአራተኛ ደረጃ ደግሞ የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በተለይም ሴቶችን እና ልጃገረዶችን፣ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን ያካተተ፤ የጎሳ፣ የዘር እና የሃይማኖት ልዩነት ያላደረገ፤ እንዲሁንም የአካል ጉዳተኞችን እና ሌሎች የተገለሉ ቡድኖችን ሁሉ ያቀፈ አሰራር ማጠናከርና ደህንነቱ መጠበቁን የማጠናከር ሥራችንን እንቀጥላለን።” ብለዋል።

በመጨረሻም “ራሳችንን የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ መፃኢ ዕድሉን መወሰን ከምንችልበት ሥፍራ ላይ አግኝተናል። ሁላችንም ሁኔታው በሚጠይቀው ፍጥነት እና ዓላማውን ማሳካት በሚያስችል መንገድ እንሰራለን። ምክንያቱም የኢንተርኔትን የወደፊት እጣ ፈንታ ከእሴቶቻችን ጋር በሚያስማማ መልኩ ካልቀረፅን ያን ውሳኔ የሚወስኑልን ፈላጭ ቆራጭ ሃገሮች ይሆናሉ።" ሲሉ ብሊንከን የተናገሩትን ጠቅሶ የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ ሃተታውን ደምድሟል።

XS
SM
MD
LG