Accessibility links

Breaking News

የ2023ቱ የፕሬዚዳንቶች ቀን


 ፕሬዚዳንት አብርሃም ሊንከን መታሰቢያ
ፕሬዚዳንት አብርሃም ሊንከን መታሰቢያ

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በየዓመቱ በየካቲት ወር በሦስተኛው ሰኞ፣ አሜሪካውያን የፕሬዚዳንቶችን ቀን በመባል የሚታወቀውን ዕለት ያከብራሉ። በዓሉም ከፍተኛ ተደማጭነት እና አድናቆት ያላቸው ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንቶች የልደት ቀናት መሃል ይውላል።

እነርሱም በየካቲት 12 የተወለዱት ፕሬዚዳንት አብርሃም ሊንከን እና በየካቲት 22 የተወለዱት ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሽንግተን ናቸው። ሁለቱም በየፊናቸው ዩናይትድ ስቴትስ እንደ አገር በተመሰረተች እና መሰረትም በጣለችባቸው ጉዳዮች ላይ አይነተኛ የሚሰኝ ተጽዕኖ ያሳደሩ ናቸው።” ሲል ይንደረደራል ዕለቱን ምክኒያት በማድረግ የወጣው ርዕሰ አንቀጽ።

ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሽንግተን አንዳንዴ “የዩናይትድ ስቴትስ አባት” በሚል ቁልምጫ ይታወቃሉ። ለዚህም በቂ ምክንያት አለው። አገሪቱን ከእንግሊዝ የዘውድ አገዛዝ በማውጣት ነፃነቷን ለመቀዳጀት ያበቃውን የአመጽ ወታደራዊ ዘመቻ የመሩ በመሆናቸው፤ ቀዳሚው የዩናይትድ ስቴትስ ጀግና በሚል የተከበሩና በሕዝብ ዘንድ የታመነ በመሆናቸው ነበር።

ደካማ ሰው ቢሆኑ ኖሮ ይህን ከፍተኛ ዕውቅና እና ተወዳጅነታቸውን፣ ራሳቸውን በጊዜው የነበሩት አስራ ሦስቱ የሰሜን አሜሪካ ግዛቶች ንጉስ ለማድረግ፣ የሥልጣናቸው መደላደያ ባደረጉት ነበር” ያለው የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ አክሎም “ይህን ሃሳብ ከዚህ አጥፉ” ሲሉ ያን ያደርጉ ዘንድ ይወተውቷቸው ለነበሩ አድናቂዎቻቸው መመለሳቸውን ያወሳል።

ይልቁንም ይህን ከፍተኛ ተሰሚነታቸውን አዲሲቱን አገር ለመቅረጽ እና ሁነኛ የአገር መሰረት ለመጣል እንዲረዳቸው ተጠቅመውብታል።

ያ አብዮት በተካሄደ ስድስት ዓመታት ዕድሜ ውስጥም ቀድሞ በእንግሊዝ ንጉሳዊ አስተዳደር ይገዙ የነበሩትን ግዛቶች የተናጠል ግዛታዊ ማንነታቸውን እንደያዙ ወደ አንድ የሚያመጣቸው ፌዴራላዊ መንግሥት ለመመስረት ስትታገል የነበረችውን ወጣት ሃገር ለማብቃት ባደረጉት ብርቱ ጥረት በመጨረሻው የተረጋጋች፣ ዴሞክራሲያዊት እና ህጋዊ መንግሥት ባለቤት የሆነች አገር እንድትወለድ አስቻሉ።

ጆርጅ ዋሽንግተን አገሪቱን የሚመራውን የመጭውን ፕሬዚዳንት አቋም በመቅረጽም ከእርሳቸው በኋላ ለመጡት በሙሉ የሚረዱ በርካታ ምሳሌዎችን ትተዋል። ከእነኚህም ውስጥ ትልቁ እና እጅግ ጠቃሚው ምግባራቸው አንድ ፕሬዚዳንት እያንዳንዳቸው ለአራት ዓመታት ከሚዘልቁ ሁለት የአስተዳደር ሥልጣን ዘመኖች በኋላ፣ በገዛ ፈቃዱ ሥልጣኑን በሰላም ለቆ ለተመረጠው ተተኪ ፕሬዚዳንት የሚያስተላልፍበትን ሥርዓት ያበጁበት መሆኑን ርዕሰ አንቀጹ አስታውሷል።

አያይዞም፣ ዩናይትድ ስቴትስ እርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ተዘፍቃ፣ ራሷን ልታፈርስ ተቃርባ በነበረችበት ወቅት አገሪቱን የመሩት ፕሬዚዳንት አብርሃም ሊንከን፣ ራሳቸውን ከአሸናፊው ወገን እንዳለ መሪ ብቻ ያለማድረጋቸው ትልቅ እድል መሆኑን የጠቆመው የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ፣ ጦርነቱ ወደ ፍጻሜው እየተቃረበ ሲመጣም በፌዴራልና በክልል አስተዳደር አካላት መካከል የሥልጣን ክፍፍል እንዲኖር በሰላም ወቅት ተግባር ላይ የሚውል ዕቅድ ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ።

በውጤቱም፣ ዩናይትድ ስቴትስ በጠንካራ የፌደራል መንግሥት የምትመራ እና እውነተኛ የግዛቶች ህብረት ያላት አገር ሆና ከእርስ በርስ ጦርነቱ መውጣት መቻሏን አመለከቷል።

የዛሬው የፕሬዚዳንቶች ቀን ሲከበርም የመጨረሻውን የሃገሪቱን የሥልጣን እርከን የመያዝ ዕድል የገጠማቸው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንቶች የሚከበሩ እና የሚዘከሩ መሆናቸውን የገለጸው ርዕሰ አንቀጽ፣ የዚህችን ሃገር እና ህዝቦቿን የዛሬ ማንነት መሰረቶች በቀረጹ ሃሳቦች እና አንድ በማድረግ ከፕሬዚዳንት ዋሽንግተን እና ከፕሬዚዳንት ሊንከን በላይ እጅግ ተፅዕኖ ያሳደረም ሆነ የሚከበር ያለመኖሩን በመጠቆም ሃተታትውን ደምድሟል።

XS
SM
MD
LG