Accessibility links

Breaking News

የአል-ሻባብ አባሉ ያለበትን ለጠቆመ 5 ሚሊዮን ዶላር ይሽለማል


አሊ ሞሃመድ ራጌ የተባለውን የሽብርተኛው የአል-ሻባብ ቀንደኛ አባል ማንነት ወይም ያለበትን ለጠቆመ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት 5 ሚሊዮን ዶላር ይሸልማል ሲል የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ ይጀምራል፡፡

የገንዘብ ሽልማቱን የሚሰጠው የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ‘ለፍትህ ሽልማት’ የተሰኘው እና በዲፕሎማቲክ ደህነት አገልግሎት የሚተዳደረው ፕሮግራም ነው ብሏል ርዕሰ አንቀጹ።

እአአ በ1966 ሶማሊያ ሞቃዲሾ የተወለደው አሊ ሞሃመድ ራጌ አሊ ዲር በሚል ስምም ይታወቃል፡፡ የአል-ሻባብ ቁልፍ መሪ ሲሆን የቡድኑ ሹራ ም/ቤት አባልና እአአ ከ2009 ጀምሮ ደግሞ የሽብር ቡድኑ ዋና ቃል አቀባይ ነው። ኬንያና ሶማሊያ ውስጥ የተፈጸሙ የሽብር ጥቃቶችን በማቀድም ተሳትፏል።

በኬንያ፣ ሶማሊያ እንዲሁም በሌሎች ጎረቤት አገሮች ለተፈጸሙትና የአሜሪካ ዜጎችን ጨምሮ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ለተገደሉባቸው የሽብር ጥቃቶች አል-ሻባብ ተጠያቂ ነው። ይህ የሽብር ቡድን በአሜሪካ፣ በጥቅሟ፣ በሸሪኮቿና በውጪ አጋሮቿ ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ማሰብ፣ ማቀድና ማሴሩን ቀጥሏል ሲል ርዕሰ አንቀጹ አክሏል፡፡

ከ19 ወራት በፊት የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ራጌን በተለየ ሁኔታ የሚታይ ዓለም አቀፍ አሸባሪነት ፈርጆታል። ይህም ማለት በዩናይትድ ስቴትስ ሥልጣንና ግዛት ስር የሚገኝ ንብረቱ በሙሉ ይታገዳል። እንዲሁም አሜሪካውያን ከእርሱ ጋር ምንም ዐይነት ንግድ ወይም ሌላ ገንዘብ ነክ ግንኙነት እንዳያደርጉ ይከለክላል፡፡

በተጨማሪም በየካቲት 2022 የተመድ የጸጥታው ም/ቤት የሶማሊያ ማዕቀብ ኮሚቴ በውሳኔ ሃሳብ ቁጥር 2093 አንቀጽ 43(a) መሠረት፣ የሶማሊያን ሰላም ጸጥታና መረጋጋትን የሚያውክ ሥራ ውስጥ በመሳተፍ ወይም ድጋፍ በማድረግ በሚል ራጌን ማዕቀብ የተጣለባቸው ግለሰቦች ዝርዝር ውስጥ ከቶታል።

እርስዎ ወይም ሌላ እርስዎ የሚያውቁት ሰው አሊ ሞሃመድ ራጌ ያለበትን የሚጠቁም መረጃ ካለዎ ከመላው ዓለም በስልክ ቁጥር +1 202 702 7843 በሲግናል፣ በቴሌግራም ወይም በዋትስአፕ እንዲሁም ኬንያ ውስጥ ከሆኑ በቁጥር +254 71 87 12 366 ሶማሊያ ካሉ ደግሞ በ+252 68 43 43 308 ‘ለፍትህ ሽልማት’ ፕሮግራምን ያሳውቁ። ሁሉም መረጃዎች ምስጢራውነታቸው የተጠበቀ ይሆናል ብሏል ርዕሰ አንቀጹ።

ይህን ሽልማት በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ‘ለፍትህ ሽልማት’ ፕሮግራም ድረ ገጽ www.rewardsforjustice.net ላይ ያገኛሉ።

በሚቀርቡት አሳማኝ መረጃዎች ላይ ሁሉ ምርመራና ማጣራት ይደረጋል፡፡ የመረጃ ሰጪዎቹም ማንነት በሚስጥር ይያዛል ሲል ርዕሰ አንቀጹ ደምድሟል።

XS
SM
MD
LG