Accessibility links

Breaking News

አሜሪካ የጀግኖች ቀን መታሰቢያን አከበረች


የአሜሪካ ባንዲራ
የአሜሪካ ባንዲራ

በግንቦት ወር የመጨረሻው ሰኞ፣ አሜሪካውያን የጀግኖች ቀን መታሰቢያን ያከብራሉ፣ ሲል ይጀምራል የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ።

ቀኑ፣ በወታደራዊ አገልግሎት ውስጥ ያሉና፣ አገራቸውንና አገራቸው የቆመችበትን ዓላማ ከጥቃት በሚጠብቁበት ወቅት ሕይወታቸውን ያጡ ወንዶችና እና ሴቶች የሚታሰቡበት፣ ለመስዋትነታቸውም ክብር የሚሰጥበት ነው።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ቀኑን በማስመልከት ያደረጉትን ንግግር ርዕሰ አንቀጹ በምስል አስደግፎ አቅርቧል።

“በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ልዩ የሆነውን ሃሳብ፣ የዩናይትድ ስቴስ ኦፍ አሜሪካ እሴትን ከጥቃት ለመጠበቅ እና ለትውልድ ለማስተላለፍ፣ በሙሉ ድፍረት እና በሙሉ መስዋትነት ሁሉን የሰጡ የአሜሪካ ውድ ሴትና ወንድ ልጆች፣ እዚህ በአርሊንግተን መታሰቢያ፣ በአውሮፓ ባሉ የመቃብር ስፍራዎች፣ በመላ አገሪቱ ባሉ ትልቅም ሆነ ትንሽ ከተሞች፣ በጸጥታና በክብር አርፈዋል” ብለዋል ባይደን።

“እያንዳንዱ ትውልድ የዲሞክራሲ ጠላቶችን መደምሰስ አለበት፡፡ እጅግ የምንሳሳላቸውን እሴቶቻችንን ለመጠበቅ፣ ደማቸውን ሊያፈሱ ፈቃደኛ የሆኑ ጀግኞች በእያንዳንዱ ትውልድ ውስጥ የፈጠራሉ” ሲሉ ይቀጥላሉ ፕሬዝደንት ባይደን።

“የእኛ ዲሞክራሲ ለአገራችን ትልቅ ስጦታ ነው። ይህ ዲሞክራሲም በጉዟችን ውስጥ መስዋትነትን በከፈሉ ሰዎች ቅዱስ ሆኗል” ብለዋል ፕሬዝደንቱ።

“ይህ የዘመናችን ትልቅ ተልዕኮ ነው። መስዋትነትን ለከፈሉ ሰዎች የምናደርገው መታሰቢያ ለአንድ ቀን ቆም ብለን በመጸለይ ብቻ የምናደርገው መሆን የለበትም። ለተከፈለው መስዋአትነት የሚገባውን ዋጋ ለመስጠት፣ በአንድነት ቆመን በየዕለቱ ቁርጠኝነታችንን በተግባር ማሳየት አለብን” ሲሉ መናገራቸውን አስደምጦ ርዕሰ አንቀጹ የዕለቱን መልዕክት ደምድሟል።

XS
SM
MD
LG