Accessibility links

Breaking News

ዩናይትድ ስቴትስ የሳይበር ጥቃቶችን በመቋቋም ላይ መሥራት ይኖርባታል


ቁልፍ የመሠረተ ልማት አውታሮች በዓለም ዙሪያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ውድመት ለማድረስ የታለመ የሳይበር ጥቃት ፈጻሚዎች የደቀኑት አደጋ ስጋት ሰለባ እየሆኑ ነው” ሲል ይንደረደራል የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ።

"የምንገለገልበት የቴክኖሎጂ፣ የኢንተርኔት እና የዲጂታል አገልግሎቶች እያደር እያየለ የመጣ ጥቃት ሰለባ እየሆኑ ናቸው።” ሲል በተባበሩት መንግስታት የዩናይትድ ስቴትስ ተወካይ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ የተናገሩትን ያወሳል።

“ይህ አየር እና የውኃ አቅርቦቶቻችንን፤ የኢንተርኔት፣ መብራትና የመጓጓዣ አገልግሎቶቻችን የሚቆጣጠሩ እና የዕለት ተዕለት ህይወታችንን የሚያቀላጥፉ ተቋማት፣ የዜና ማሰራጫ ጣቢያዎችን እና የመንግስት መረጃ ገፆችን ይጨምራል።”

ርዕሰ አንቀጹ በማያያዝም የሳይበር ጥቃት አደጋዎች እየመጡ ያሉት ከወንጀለኛ ቡድኖች ብቻ ሳይሆን፤ የሳይበር ደህንነትን የሚመለከቱ ደንቦችን እና ሕጎችን በሚፈልጉት መልክ ለመቅረጽ በክፉ ዓላማ ከተነሳሱ አንዳንድ መንግስታት ጭምር ነው።” ሲሉ አምባሳደር ቶማስ-ግሪንፊልድ የተናገሩትን አክሏል።

‘ጉዳት ለማድረስ በሚነጣጠሩ የሳይበር ጥቃቶች ላይ ከሚተሳተፉ መንግስታት ምሳሌ የሆነችው ሩስያ፣ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ፍትሃዊ ያልሆነ ጦርነት መጀመሪያ ላይ የዩክሬንን የኃይል ማመንጫዎችና የኃይል ማስተላለፊያ ፍርግርጎች እና የሳተላይት መገናኛዎች የጥቃት ኢላማዋ ስታደርግ፤ ባለፈው ዓመት በአልባኒያ ላይ ጥቃት ያደረሰችው ኢራንም የመንግስቱን የመረጃዎች ክምችት ከማውደሟ ባሻገር በርካታ የህዝብ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ምክኒያት መሆኗን ርዕሰ አንቀጹ አውስቷል።

“እነዚህን ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ብርቱ እና ተለዋዋጭ ስጋቶች ከተመለከትን፣ ለመከላከልም ሆነ ሁነኛ ምላሽ ለመስጠት ሁላችንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን እንሻለን።”

በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት የተካሄዱትን በሳይበር ደህንነት ላይ ያተኮሩ ስብሰባዎች በይሁንታ የተቀበሉት አምባሳደር ቶማስ ግሪንፊልድ፣ “ግንዛቤንበማሳደግ፣ አንዳች ጉዳት ለማድረስ የሚውጠነጠኑ የሳይበር ጥቃቶችን ማውገዝ አለበት” ያሉት የጸጥታው ምክር ቤት፡ የድርጊቱን ፈጻሚዎችም ተጠያቂ ለማድረግ ግንባር ቀደም ሚና መጫወት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩትን ርዕሰ አንቀጹ ጠቅሷል።

"በኮምፒውተር እና በሌሎች የዲጂታል ቴክኖሎጂው ግብአቶች አማካኝነት የሚከናወኑ ሥራዎች፡ በምን ዓይነት ህጎች እና ደንቦች ይዳኙ፤ ይልቁንም (ደግሞ) በዚህ የቴክኖሎጂ ምህዳር አጠቃቀም ኃላፊነት የሚሰማው የመንግስት ባህሪ ማዕቀፍ ምን ይሁን’ በሚል ያለንን የጋራ ግንዛቤን ማጎልበት እና ይበልጥም ማስተዋወቅ አለብን።"

ርዕሰ አንቀጹ አያይዞም፡ “እንደ እድል ሆኖ፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንግስታት ጉዳይ ተከታታይ ባለሞያዎችቡድንይህን መሰሉን ማዕቀፍበማዘጋጀት፣ ጠቅላላ ጉባኤው ያለውን የጋራ መግባባት ደጋግሞ አረጋግጧል” ሲሉ አምባሳደር ቶማስ ግሪንፊልድ ይህንን አስመልክቶ የተናገሩትን ጠቅሷል።

“አለምአቀፍሕጎች በሳይበርስፔስ አጠቃቀም ላይም ተፈጻሚ ይሆናሉ። አገራት በሰላም ጊዜ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረቱ የመንግስት ባህሪያትን እንዲያከብሩ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በአንጻሩ የሳይበር ደህንነትን ለማጠናከር መንግስታት ተግባራዊየትብብርእርምጃዎችንም መውሰድአለባቸው።” ብለዋል።

"የተባባበሩት መንግስታት ከወራት በፊትየአባል ሃገራት ጠንካራ ድጋፍ የተቸረው ‘የሳይበር ቴክኖሎጂ የተግባር ፕሮግራም’ .. በእንግሊዝኛው አጽህሮት POA የሃገራትን የሳይበር ፕሮግራም ማዕቀፍ እና የሳይበር አቅም በመገንባት ላይ ያተኮረ ቋሚ አካል እንዲፈጠር ሊረዳ ይችላል” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትሷ የተባበበሩት መንግስታት ተወካይ አምባሳደር ቶማስ ግሪንፊልድ የተናገትሩትን ጠቅሶ የዕለቱ ርዕሰአንቀጽ ሃተታውን ደምድሟል።

XS
SM
MD
LG