Accessibility links

Breaking News

ለሱዳን ሕዝብ ተጨማሪ ዕርዳታ ጥሪ ቀረበ


ፎቶ ፋይል - በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል በተፈጠረው ግጭት አየር ላይ የቦምብ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ በህንጻዎች ላይ የደረሰው ቃጠሎ፤ ካርቱም፣ ሱዳን
ፎቶ ፋይል - በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል በተፈጠረው ግጭት አየር ላይ የቦምብ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ በህንጻዎች ላይ የደረሰው ቃጠሎ፤ ካርቱም፣ ሱዳን

በሱዳን ጦር ጠቅላይ አዝዥ አብደል ፋታህ አል ቡርሃን እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አዛዥ ሞሃመድ ዳግሎ ታማኝ ወታደሮች መካከል ጦርነት ከፈንዳ አንስቶ፣ ቢያንስ 4ሺሕ ሰዎች ሲሞቱ፣ 6 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ ተጎድተዋል። በሱዳን 25 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ ይሻሉ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሲፈናቀሉ፣ በርካቶች በጎረቤት ሀገራት ከለላ እንዲሹ አድርጓቸዋል፣ ሲል የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ ሃተታውን ይጀምራል።

“ግጭቱ ከጀመረ አንስቶ 400 ሺሕ የሚጠጉ ሰዎች ከዳርፉር ወደ ምሥራቅ ቻድ ተሻግረዋል” ሲሉ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ድንበር ጳጉሜን 1 ቀን የጎበኙት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ተናግረዋል። በቻድ መንግስት፣ በአካባቢው አስተዳደሮች እንዲሁም መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞች ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም፣ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች የምግብ፣ የውሃ፣ የጤና እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች እጥረት ገጥሟቸዋል፣ ሲሉ አምባሳደሯ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ያጋጠመው ከፍተኛ ቀውስ፣ የዓለምን የተባበረ ምላሽ ጠተይቃል፣ ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ የንበኩሏን ለማድረግ ቁርጠኛ ነች ሲሉ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ መናገራቸው ርዕሰ አንቀጥሱ ጠቅሷል። “በቅድሚያ በዚህ ግጭት ተጎጂ የሆኑትን ለመርዳት ተጨማሪ እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል አምባሳደሯ።

“ለሱዳን እንዲሁም ቻድን ጨምሮ በዙሪያዋ ላሉ ጉረቤት ሀገራት ህዝብ፣ ዩናይትድ ስቴስ 165 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንደምትሰጥ አስታውቃለሁ።

ገንዘቡ ሰዎች የምግብ፣ የውሃ፣ የንጽህና፣ የጤና እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ይውላል። በተጨማሪም ገንዘቡ ሴቶች፣ ታዳጊዎች እና አዛውንቶችን ጨምሮ በተለየ ሁኔታ ለአደጋ ለተጋለጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን እና ከግጭቱ የተረፉትን ለመጠበቅ ይውላል ሲል ርዕሰ አንቀጹ ይቀጥላል።

በሁለተኝ ደረጃ አሉ አምባሳደሯ፣ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ውስጥ ከፍተኛ አዛዥ የሆኑት እና የአብደል ፋታህ አል ቡርሃን ውንድም በሆኑት አብደልራሂም ሃምዳን ዳግሎ ላይ፣ ኃይሉ በሲቪሎች ላይ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር ባላቸው ግንኙነት ምክንያት፣ ዩናይትድ ስቴት ስማዕቀብ በመጣል የሰቆቃው ፈጽሚዎች በሃላፊነት እንዲጠየቁ እርምጃ በመውሰድ ላይ ነች፡፡

በተመሳሳይ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ጀኔራል በሆኑት እና በዳርፉር አዛዥ በሆኑት አብዱል ራህማን ጁማ ላይ፣ በጅምላ በተፈጸመ ሰብዐዊ መብት ጥሰት ጋር ባላቸው ግኑኝነት ምክንያት የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የቪዛ ማዕቀብ እንደጣለባቸው አምባሳደር ቶማስ ግሪንፊልድ መናገራቸውን ር ዕሰ አንቀጹ አውስቷል።

“የተጠቀሱትና በዳርፉር የተፈጸሙት ጥሰቶች አሜሪካ በእ.አ.አ 2004 በዳርፉር ‘የዘር ማጥፋት ተፈጽሟል’ ስትል ያወጀችውን በመራር ሁኔታ የሚያስታውስ ነው” ሲሉ አምባሳደሯ አክለዋል።

“ነገር ንግ ለዚህ አስከፊ ግጭት በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተሰጠው እጅግ ያነሰ ትኩረት የሚያሳዝን ነው።”

“በሱዳን በ2023 ሊሰጥ ከታቀደው ሰብዐዊ ምላሽ ውስጥ ገንዘብ የተመደበለት ከ 30 በመቶ ላነሰው” ያሉት አምባሳደር ቶማስ ግሪንፊልድ፣ “ይህ የሚያሳፍር ነው፣ ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ተጨማሪ ሥራ እንዲሠራ እና ተጨማሪ እንዲሰጥ ጥሪ አደርጋለሁ” ሲሉ መናገራቸውን ጠቅሶ ርዕሰ አንቀጹ ሃተታውን ደምድሟል።

XS
SM
MD
LG