Accessibility links

Breaking News

ከዓለም የጤና ድርጅት ባሻገር


ፎቶ ፋይል፦ የዩኤስኤድ ዕርዳታ
ፎቶ ፋይል፦ የዩኤስኤድ ዕርዳታ

“ዩናይትድ ስቴት፣ ለረጅም ጊዜ፣ በመላው ዓለም፣ የጤና እና ሰብአዊ እርዳታዎችን ለሚሹ ሰዎች በመለገስ፣ ከማንም በላይ ትታወቃለች፡፡” ይላል፣ የእለቱ ርእሰ አንቀጽ ሀተታውን ሲጀምር፡፡

ይህ እርዳታና ድጋፍ የሚሰጠው፤ ከአሜሪካ ግብር ከፋዮች ከሚሰበሰበው ገንዘብ ሲሆን፣ እርዳታው፣ በትክክል ለሚያስፈልጋቸው ሰዎችና፣ እንዲሁም ለታሰበለት ትክክለኛ ዓላማና ግብ እንደሚውል፣ በመተማመን ነው፡፡ ይላል ርእሰ አንቀጹ፡፡

ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠል፣ “እንዳለመታደል ሆኖ፣ የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት፣ እነዚያን መስፈርቶች የ ሚያሟላ ሆኖ አልተገኘም፡፡ በኮቪድ-19 በሚሰጠው ምላሽ ብቻ ሳይሆን፣ ከቅርብ 10 ዓመታት ወዲህ፣ በሚታዩ የጤና ቀውሶችም ጭምር ነው፣ ብሏል ርእሰ አንቀጹ፡፡ በተጨማሪም፣ የዩናትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፣ “የዓለም ጤና ድርጅቱ፣ ከቻይና ኮሙዩኒስት ፓርቲ ጋር የጀመረውን ጥገኝነት ለመተው፣ የሚያስፈልገውን አጣዳፊ ማሻሻያዎች ማድረግ አልፈለገም” ማለታቸውን ርእሰ አንቀጹ አስታውቋል፡፡

በዚህ የተነሳም፣ ዩናይትድ ስቴት፣ ከሀምሌ 6/2021 ጀምሮ፣ ከዓለም የጤና ድርጅት አባልነት ራሷን በይፋ ማግለሏን፣ ርእሰ አንቀጹ ጠቅሷል፡፡

በመቀጠልም፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለውጭ ዓለም የምታደርገው የጤና እርዳታና ድጋፍ፣ ጠንካራ እንደሆነ ይቀጥላል ብሏል፡፡ ከዓለም ጤና ድርጅት ለመውጣት በነበረው ሂደትም፣ አስተዳደሩ ቁልፍ ከሆኑ የአሜሪካ መንግሥታዊና የግል ተቋማት ጋር በመተባበር፣ ቋሚና ፈጣን እርዳታዎችን፣ ለሌሎች አገሮች መስጠት የሚቻልበትን፣ በሽታዎችን መከላከልና፣ ተላላፊና ወረርሽኞችን በምንጫቸው እንዳሉ ምላሽ ለመስጠት፣ እንዲሁም ፈጣን የሆነ ሰብአዊ እርዳታ ለማድረግ የሚቻልበትን መንገድ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር መመርመሩንና ማጥናቱን ርዕሰ አንቀጹ አስረድቷል፡፡

እኤአ ከ2001 ጀምሮ የኤች አይቪ/ኤድስን፣ ወባን፣ የሳምባ ነቀርሳን፣ ኢቦላንና ሌሎች አስከፊ ፣በሽታዎችንና ቀውሶችን፣ ለመከላከልና ለማስወገድ፣ የዩናይትድ ስቴት ከ142 ቢሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ መለገሷን፣ ርእሰ አንቀጹ አስረድቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ እርዳታ ለጋሹ ድርጅት፣ የዩኤስ ኤድ (“USAID”) ረዳት የዓለም ጤና ጉዳዮች አስተዳዳሪ፣ ዶ/ር አልማ ጎልደን “እኛ በአማካይ፣ በየዓመቱ 10 ቢሊዮን ዶላር፣ ለዓለም ጤና ጉዳዮች እንለግሳለን፣ በተለይ በዚህ የኮቪድ 19 ጊዜ ደግሞ፣ ወረርሽኙን ከዓለም ላይ ለመካከል፣ ይህንን እርዳታችንን በእጥፍ እናሳድጋለን” ብለው መናገራቸውን ርእሰ አንቀጹ ጠቅሷል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ራሷን ከዓለም የጤና ድርጅት ማግለሏ፣ በመላው ዓለም የምታደርገውን አጠቃላይ የጤና እርዳታዎችና፣ በተለይም እርዳታው በጣም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እንዳይቋረጥ ትፈልጋለች፡፡ ያለው ርእሰ አንቀጽ፣ ዶ/ር ጎልደን “ዩናይትድ ስቴትስ በመላው አሜሪካ ጥረት፣ በየትኛውም ዓለም የሚደረገውን የጤናና ሰብአዊ እርዳታ ሥራዎች ትመራለች፡፡” ማለታቸውን ጨምሮ አስታውቋል፡፡

በመጨረሻም ዶ/ር ጎልደን “እርዳታችን በቀጥታ ከመላው የዓለም ህብረተሰብ ዘንድ መድረሱን እርግጠኛ ለመሆን እንሰራለን” ማለታቸውን በመጥቀስ ርእሰ አንቀጹ ሀተታውን ደምድሟል፡፡

XS
SM
MD
LG