Accessibility links

Breaking News

የፕሬስ ነጻነትን አስፈላጊነት ማክበር


People hold up copies of the Apple Daily as they protest for press freedom
People hold up copies of the Apple Daily as they protest for press freedom

“ዩናይትድ ስቴትስ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር የፕሬስ ነጻነትን አስፈላጊነት ታከብራለች፡፡” ይላል ርእሰ አንቀጹ ሀተታውን ሲጀምር፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን፣ የዓለም አቀፉን የፕሬስ ነጻነት ቀን አስመልከቶ “ኢንፎሬሜሽን እና እውቀት፣ ኃይል ሰጭ መሳሪያዎች ናቸው፣ ነጻና ገለልተኛ ፕሬስም፣ ህዝብ የሚያስፈልገውን መረጃዎች ሁሉ እንዲያገኝ አገናኝ ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡” ብለዋል፡፡

“ዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም በድረገጽም ይሁን ከዚያ ውጭ ላሉ የፕሬስ ነጻነቶችና ለጋዜጠኞች ደህነንት ጥብቅና የምትቆመውም ለዚያ ነው” ብሏል ር እሰ አንቀጹ፡፡

ሀሳብን በነጻነት መግለጽ ለዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ መሠረት ነው ፡፡ በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌ መሰረት፣ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በየትኛውም መድረክ ቢሆን የሁሉንም ሰው ሀሳብ በሁሉም ሚዲያ “ መረጃ የማግኘት፣ የመቀበልና የማስተላለፍ መብትን ያጠቃልላል፡፡

“ይሁን እንጂ ዛሬ ስለጋዜጠኞች መብት ያለው አመለካከት እጅግ አስፈሪና አሳዛኝ ነው፡፡” ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብሊንከን፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በጭካኔ በተገደለው የሳኡዲው ጋዜጠኛ ጀማል ካሶጂ በሰጠችው ምላሽ “የካሶጂ እገዳ” በሚል መሰየሟን ያሳወቅችበት አንደኛውም ምክንያት ሚዲያን ለማስፈራራት የሚታየውን አዝማሚያ ለመካለከል እንዲረዳ መሆኑንም ርእሰ አንቀጹ አስረድቷል፡፡

ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ)፣ ሥራቸው ላይ እንዳሉ የታሰሩ ጋዜጠኞችን መመዝገብ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ በ2020 የተመዘገበው ትልቁ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት፣ በቻይና፣ በቱርክ፣ እና ግብጽ ውስጥ የታሰሩ ጋዜጠኞች ብዛት፣ ከፍተኛውን ደረጃ ደርሷል፡፡ በራሽያም የራዲዮ ፍሪ ዩሮፕ እና ሬዲዮ ሊበርቲን ጨምሮ ባለሥልጣናቱ ገለልተኛ ዘገባዎችን ማገዱን ቀጥለውበታል፡፡

እንዳለመታደል ሆኖም የኮቪድ 19 ወረረሽኝ ጨቋኞቹ መንግስታት ነጻ ሚዲያዎቹን ላይ የሚያሳድሩት ጫና እንዲበረቱ መንገድ ከፍቶላቸዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብሊንክን፣ “ መንግሥታት የሚዲያ ደህንነት እንዲጠበቅና ጋዜጠኞችም ሥራቸውን ያለምንም ፍርሃት፣ ጥቃትና የዘፈቀደ እስር ሳይደርስባቸው መስራት የሚችሉበት ጥበቃ እንዲደረግላቸው አሳስበዋል፡፡

ርእሰ አንቀጹ በመቀጠል፣ “ዩናይትድ ስቴትስ፣ መንግሥታት በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸሙትን ሁሉንም ወንጀሎች እንዲመረምሩና ተጠያቂነት እንዲኖር እንዲያደርጉ ታሳስባለች፡፡” ብሏል፡፡

“እየተስፋፋ በመጣው የዲጂታል ሚዲያው ዓለም የፕሬስ ነጻነትና የነጻ ኢንፎርሜሽን ፍሰትም እንዲሁ የኢንተርኔት ነጻነትን ይጠይቃል፡፡ ያሉት

ብሊንከን አያያዘውም፣ ኢንተርኔትንና ተደራሽነቱንም በመቆጣጠር ፣ ህዝብን የመረጃ ፍሰትና እውቀት እንዳያገኝ የሚያደርጉ መንግሥታትም እየጨመሩ መምጣታቸው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትን ያሳሰባት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መንግሥታት ኤንተርኔትን ማገድ፣ መዝጋትና ሳንሱር ማድረግ የለባቸውም፡፡ ይህ ድርጊት፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የመሰብሰብ ነጻነትን፣ የመደራጀት መብትን ወይም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን፣ የመሠረታዊ አገልግሎት ተጠቃሚ የመሆን መብትን እንደሚያግደው ሁሉ፣ ኢኮኖሚውንም ክፉኛ ይጎዳል፡፡” ብለዋል፡፡

በመጨረሻም “ዩናይትድ ስቴትስ ከሚዲያው ማህበረሰብ አባላት ጋር፣ ከግሉ ሴክተር፣ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ የመረጃ ነጻነትና ተደራሽነት እንዲኖር ከሚሰሩ፣ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ከሚጠብቁና መብቶቻቸውን ለማስከበር ሲሉ ጥቃትና ማስፈራሪያ የሚደርሰባቸውን ጋዜጠኞችን መብቶች ከሚጠብቁ መንግሥታት ጋር አብራ ለመስራት ቁርጠኝነቱ አላት፡፡” በማለት ርዕሰ አንቀጹ ሀተታውን ደምድሟል፡፡

XS
SM
MD
LG