Accessibility links

Breaking News

ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሰላም የሚያመራ መተማመን


ፎቶ ፋይል፦ የዩናትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ማይክ ፓምፔዮ እና ባለቤታቸው ሱሳን
ፎቶ ፋይል፦ የዩናትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ማይክ ፓምፔዮ እና ባለቤታቸው ሱሳን

የዩናትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ማይክ ፓምፔዮ፣ በቅርቡ ወደ መከካለኛው ምስራቅ ባደረጉት ጉዞ፣ ሁለት አብይት ጭብጦች ተከስተዋል፡፡ የመጀመሪያው፣ አብዛኛው የመካለለኛው ምስራቅ አገሮች፣ ባህሬን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ሱዳን እንዳደረጉት ሁሉ፣ የአብርሃም ስምምነትን በመቀበል፣ ከእስራኤል ጋር ያላቸውን መልካም ግንኙነት እንደሚያሻሽሉ፣ እምነት ማሳደሩ አንደኛው ነበር፣ ይላል ርዕሰ አንቀጹ ሀታውን ሲጀምር፡፡

ሁለተኛው በጠበኛይቱ ኢራን የተደቀነውን አደጋ በመገንዘብ በኩል፣ አካባቢው አንድ አቋም ይዞ መገኘቱን ርእሰ አንቀጹ ያስረዳል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፓምፔዮ፣ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤጃሚን ኔታኒያሁ እና፣ ከባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ አቡዱላጢፍ ቢን ራሺድ አል ዛያኒ ጋር፣ ከመገናኘታቸው በፊት “ ይህ ስምምነት በብዙ ምክንያቶች አሰፈላጊ ነው፣ እነዚህ ስምምነቶች ለመላው ዓለም፣ ለንግድ፣ ለኢኮኖሚና ለልማት በርካታ አስደናቂ እድሎችን ይከፍታሉ፡፡ ስምምነቶቹ እንደ ኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ያሉ፣ እኩይ ተዋንያን፣ በአካባቢው ያላቸውን ተጽእኖ ይቀንሳል፡፡ የኢራን መሪዎች፣ አቅጣጫቸውን የማይቀይሩም ከሆነ፣ የበለጠውን እየነጠላቸው ይሄዳል፣ ብለው መናገራቸውን፣ ርእሰ አንቀጹ ጽፏል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ፓምፔዮ፣ አቡዳቢ ውስጥ ከአል አረቢያ ቴሌቪዥን ጋር፣ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፣ “በአባቢው ያሉት ብዙዎቹ አገሮች፣ የአብርሃምን ስምምነት፣ በራሳቸው ጊዜ ወደፊት እንደሚቀበሉ ገልጸው፣ ይህን የሚያደርጉትም፣ ለአገራቸው ደህንነት እና ብልጽግናን ስለሚጨምር፣ እንዲሁም ደግሞ ይህን ትክክል የሆነ ነገር፣ ለህዝባቸው ማድረግ ስለሚኖርባቸው ነው” በማለት መናገራቸውን፣ ርእሰ አንቀጹ አትቷል፡፡

ፓምፔዮ፣ ቀደም ሲል፣በአካባቢው ሰላም ሊረጋገጥ የሚችለው፣ በፍልስጤምና እስራኤል መካከል ያለው ችግር፣ ሙሉ በሙሉ ሲፈታ ብቻ ነው ተብሎ ይታሰብ እንደነበር በመግልጽ “ይህ እምነት፣ ሁኔታዎችን ያላገነዘበ ስለነበር፣ መሰረታዊ ስህተት ነበር፡፡ አሁን ያለው እውነታ ግን፣ የባህረ ሰላጤዎቹ አገራትና እስራኤል፣ የጋራ ጠላታቸው፣ኢራን መሆንዋን መገንዘባቸው ነው” ብለው መናገራቸውን፣ ርእሰ አንቀጹ ገልጿል፡፡

የእስራኤልና የፍስልጤምን ግጭት መፍታት አስፈላጊነትን አበክረው የገለጹት ፓምፔዮ፣ በአካባቢው ሰላምን ለማምጣት ግን ፣ሁኔታውን እንደቅድመ ሁኔታ ይዘን፣ ለ40 ዓመታት መቆየት የለብንም ማለታቸውም፣ በርእሰ አንቀጹ፣ ተመልክቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፓምፔዮ፣ የአብርሃምን ስምምነት፣ “የመከከለኛው ምስራት የወደፊት እጣ ጠቋሚ ነው” ብለው የጠሩት መሆኑን ርዕሰ አንቀጹ ገልጾ፣ “ይህም የአሜሪካን ተሳትፎና አመራር ጠይቋል” ማለታቸውንም ጠቅሷል፡፡

በመጨረሻም፣ ማይክ ፓምፔዮ “ያንን ስናደርግ፣ አሜሪካ መካከለኛው ምስራቅን ጨምሮ፣ በመላው ዓለም፣ የመልካም ነገሮች አስፈጻሚ ኃይል ስትሆን፣ ሌሎችም አገሮች፣ ተገቢውን ምርጫ በማድረግ፣ ለብልጽናቸው ጭምር ሲሉ ከኛ ጋር አብረው መሰለፍና ከእስራኤልም ጋር መወዳጀት ይፈልጋሉ፡፡ ብለው መናገራቸውን በመግለጽ ርእሰ አንቀጹ ጹሁፉን ደምድሟል፡፡

XS
SM
MD
LG