በየዓመቱ መስከረም ወር ላይ በሚመጣው የመጀመሪያው ሰኞ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ሠራተኞችዋ ለሃገሪቱ ብልጽግና የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ እለቱን አክብራው ትውላለች ይላል የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ ጽሁፉን ሲጀምር፡፡
እኤአ ሰፕቴምበር 5 /1882 ወደ አስር ሺ የሚጠጉ ወንዶችና ሴቶች፣ በኒዮርክ ማንሃተን ጎዳናዎች ላይ ባደረጉት ሰልፍ የመጀመሪያውን የሠራኞች ቀን አክብረዋል፡፡ የኒው ዮርክ ማዕከላዊ የሠራተኞች ማኅበር፣ ከፍተኛውን የሥራ ክፍያና አንተስተኛውን የሥራ ሰርዓትን እንዲሁም ምቹና የተሻሉ የሥራ ሁኔታዎችና እንዲኖሩ የታገሉ ሠራተኞችን ከፍ ከፍ ለማድረግ እለቱ እንዲከበር ማድረጉንም ርዕሰ አንቀጹ አስታውሷል፡፡
እለቱ “የድል በዓልምb ቢሆን፣ የተከፈለው መስዋዕትነትም የታሰበበት ነበር” ያለው ርዕሰ አንቀጽ፣ ሠራተኞቹ ለከባዱ ሥራቸው ተመጣጣኝ ክፍያ ለጠየቁበት ዓላማ ሲሉ፣ አደባባይ የወጡበትን የክፍያ ቀናቸውን እንኳ፣ አሳልፈው የሰጡበት መሆኑንም ጠቅሷል፡፤
በዚህ ዓመት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሠራኞቹ ላይ አዲስ አጋጣሚ በመፍጠር እስከዛሬ ዓይተነው የማናውቀው ልዩ ፈተና ደቅኗል” ብሏል ርእሰ አንጹ፡፡ “የኮሮናቫይረሰን ወረርሽኝን መስፋፋት ለመግታት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሠራተኞች፣ ለወራት ከቤታቸው እየሠሩ ቢሆንም በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ወረርሽኙን በግንባር እንዲፋለሙ ተጠርተዋል” ብሏል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ ሠራተኞችና የህክምና ባለሙያዎችም ለቫይረሱ የተጋለጡን በማስታመም፤ ለሞት ያጣጣሩትን ከጎን ቆሞ በማጽናት፣ የሌሎችን ህይወት ለመታደግ ሲሉ፣ የራሳቸውን ህይወት ሳይቀር ለአደጋ እንደሰጡ በመጥቀስ ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩት የጤና ባለሙያዎችና ሠራተኞች፣ ውድ ህይወታቸውን የከፈሉ መሆኑን ርዕሰ አንቀጹ አስረድቷል፡፡
ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠል፣ “ሌሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩና አንተስተኛ ክፍያ የሚከፈላቸው ሠራተኞች ደግሞ የሃገሪቱ እንቅስቃሴ እንዳይገታና እንዲቀጥል ያደረጉ ናቸው፡፡ ሌሎች እንዲገመቡ፣ እህሉ አሁንም ቢሆን መዘራት፣ መብቀል፣ መዘገጃጀት፣ መሰራጨትና ለገቢያም ቀርቦ መሸጥ አለበት፡፡ በመላ አገሪቱ የፖስታ መልዕክት እየተለየ በየአድራሻው መላክ አለበት፡፡ የኃይል ሰጪና አመንጪ ተቋማት ላይ የሚሰሩ የመጠጥ ውሃን የሚንከባከበኩ ሥራ ላይ የተሰማሩት ሁሉ ለሃገሪቱ ህልውና ከፖለቲካው አስተዳደርና አመራር ላይ ካሉ ሰዎች ወይም ለወረርሽኙ እልባት ለመስጠት፣ ስርጭቱንም ለመግታት፣ በተደራጀ ሁኔታ ለመመራትም ከሚሰሩት ሁሉ ያነሰ አስተጽኦ ያላቸው አይደሉም፡፡” ብሏል፡፡
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “ብዙ ነገሮች በሚያስፈልጉበት በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንኳ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ፍጹም የማይረታ ጥንካሬ ያላት መሆኑን፣ ዓለም እያስተዋለ ነው፡” ማለታቸውን የገለጸው ርዕሰ አንቀጽ፣ ፕሬዚዳንቱ “ በአገራችን ምድር ሁሉ ጀግኖቹ በያሉበት ለተግባር እየተሽቀዳደሙ ነው፣ ዶክተሮቹና ነርሶቹ የቻሉትን ነፍስ ሁሉ ለማዳን እንቅልፍ አልባ ሌሊቶቹን አሳልፈዋል፡፡ ገበሬዎች ትራክተር ነጂዎች ግሮሰሪ ሰራተኞች መደብሮቻችን እንዲሞሉና ሰዎች እንዲመገቡ አድርገዋል፡፡ ቤተሰቦች ጎረቤቶቻቸውን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ረድተዋል፡፡ ጠቅላላው ማህበረሰቡ ይህን ቀውስ ድል ለመንሳት በአንድነት ተሰልፈዋል፡፡” ማለታቸውን ርዕሰ አንቀጹ አስረድቷል፡፡
በመጨረሻም “ይህ ሁሉ ለዚህች አገርና ለአገሪቱም ህዝብ የተከፈለ ዋጋ ሲሆን ፣ የአገራችን ህዝብ ምን ማድረግ እንደቻለና ፣ በዚህም የምን ያህል ሰው ህይወት ሰው ማዳን እንደተቻለ ታይቷል፡፡” በማለት ርዕሰ አንቀጹ ጽሁፉን ደምድሟል፡፡