Accessibility links

Breaking News

ዓለምን እንዲታገል መርዳት


ቡድን 7 ሲደመር በሚል መጠርያ የሚታወቁት ዲሞክራስያዊ ሃገሮች፣ ቢያንስ 870 ሚሊዮን የኮቪድ 19 የክትባት መድሀኒትን ለማጋራት ቃል ገበተዋል ሲል፣ የዕለቱ ርእሰ-አንቀጽ ሀተታውን ጀምሯል። ይህ የክትባት መድሀኒት፣ ባለፈው የካቲት ወር እንደሚሰጥ ከተገለጸው የክትባት መድሀኒት ጋር ሲደመር፣ እስከ መጪው አመት ባለው ጊዜ፣ ከአንድ ቢልዮን በላይ እንደሚሆን፣ ግማሹን የክትባት መድሃኒት የምትለግሰው፣ ዩናይትድ ስቴትስ መሆንዋን ርእሰ-አንቀጹ ገልጿል።

“በዓለም አቀፍ ጉዳይ ላይ ቅድሚያ የምንሰጠው አስተማማኝ፣ ውጤታማ፣ ተደራሽና መጠነኛ ዋጋ የሚጠይቅ የክትባት መድሃኒት፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሃገሮች ማቅረብ ነው። ይህ የሚደረገውም ሰዎች በብዛት ሲከተቡ፣ አለምን እንደሚጠቅም እሳቤ ውስጥ በማስገባት ነው” ሲሉ፣ የቡድን 7 መሪዎቹ ባወጡት መግለጫ አስገንዝበዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ጆ ባይደን፣ ሀገራቸው ስለምትለግሰው የክትባት መድሀኒት መጠን ካስታወቁ በኋላ የተሰማውን፣ ታሪካዊ የልገሳ ቁርጠኛነትን በመልካም ተቀብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ወደ 100 ለሚጠጉ ሃገራት፣ የኮቪድ 19 የክትባት መድሀኒት ለመለገስ ስትል፣ ግማሽ ቢልዮን የሚሆን የፋይዘር ባዮቴክ የክትባት መድሃኒት እንደመትገዛ፣ ፕሬዚዳንት ባይደን የቡድን ሰባቱ ጉባኤ ሲጀመር አስታውቀው ነበር። የክትባቱ መድሀኒት ከሚቅርብላቸው ሃገሮች መካከል፣ 92 ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገሮች ይገኙባቸዋል። የዓለም አቀፉን ወረረሽኝ ለመከላከል፣ የክትባት መድሀኒት አቅርቦቱ፣ እጅግ የሚያስፈልጋቸው ሃገሮች መሆናቸውን ርእሰ-አንቀጹ አመላክተዋል። ፕሬዚዳንቱ እንደገለጹት፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከማንኛዋም ሀገር የበዛ፣ የኮቪድ 19 ክትባት መድሀኒት በመግዛት ትለግሳለች።

“በዩናይትድ ስቴትስ የሚቀርበው ግማሽ ቢልዮን የሚሆን፣ የኮቪድ-19 የክትባት መድሃኒት እንደተመረተ ወድያውኑ፣ በመጭው ነሃሴ ወር ይላካል” ብለዋል ፕሬዚዳንት ባይደን። ሁለት መቶ ሚልዮን የሚሆነው፣ በያዝነው ዓመት እንደሚከፋፈል። 300 ሚልዮኑ ደግሞ፣ እአአ አቆጣጠር በመጪው ዓመት የመጀመርያ አጋማሽ ላይ እንደሚቀርብ፣ ፕሬዚዳንት ባይደን ማስታወቃቸውን፣ ርእሰ አንቀጹ ጠቁሟል።

ዩናይትድ ስቴትስ ግማሽ ቢልዮን የሚሆን፣ የኮቪድ-19 የክትባት መድሃኒት ለመለገስ ቃል የገባችው፣ ከዚህ ቀደም በለገሰቸው ላይ ተጨማሪ ነው። አሜሪካ ቢያንስ 80 ሚልዮን የኮቪድ-19 የክትባት መድሀኒት መለገስዋን፣ ሁለት ቢልዮን ዶላር ደግሞ፣ ኮቫክስን ለመርዳት መስጠትዋን፣ ፕርዚዳንት ባይደን አስታውቀው ነበር። ኮቫክስ አስተማማኝና ውጤታማ የሆነ የኮቪድ 19 የክትባት መድሃኒት፣ በአለም ደረጃ ለማቅረብ የሚሰራ፣ አለም አቀፍ የሀገሮች ስብስብ ነው።

የቡድን ሰባት ሃገሮች፣ ለመለገስ ቃል ከገቡት የክትብት መድሃኒት ጋር ሲደመር፣ ከአምና አንስቶ ከ 2 ቢሊዮን በላይ የሚሆን የክትባት መድሀኒት፣ በገንዘብና በማምረት ለአለም ለማቅርብ መቻላቸውን ርእሰ-አቀጹ ገልጿል። ቡድን 7 በተጫማሪም፣ በያዝነውና በመጪው አመት፣ ቢያንስ አንድ ቢልዮን አስተማማኝና ውጤታማ የክትባት መድሀኒት፣ በተለያዩ ሀገሮች እንዲመረት ማቀዱን፣ ርእሰ አንቀጹ አክሏል።

የቡድን 7 ሃገሮች፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለማሻነፍ የሚያደርጉት ጥረት፣ በቅርቡ በገቡት ቃል ላይ ብቻ ሳይወሰን፣ ለረጅም ጊዜ የሚቀጥል መሆኑን፣ በቡድን 7 ሃገሮቹ መካከል፣ ግልጽ የሆነ መግባባት እንዳለ፣ ፕሬዚዳንት ባይደን አስገንዝበዋል ሲል፣ የዕላቱ ርእሰ-አንቀጽ ሃተታውን አብቅቷል።

XS
SM
MD
LG