ዩናይትድ ስቴትስና የቡድን ሰባት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሩስያው ተቃዋሚ መሪ አለክሰይ ናቫልኒን መታሰር አውግዘዋል። አሜሪካ ከካናዳ፣ከፈረንናይ፣ ከጀርመን፣ ከኢጣልያ፣ ከጃፓንና ከብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በመተባበር፣ የእውቁ ተቃዋሚ መሪ እስራትን ያውገዙት፣ የፖለቲካ አላማ አለው በማለት መሆኑን፣ የእለቱ ርዕሰ አንቀች ገልጿል።
አለክሰይ ናቭልና የታሰሩት፣ ከጀርመን ወደ ሩስያ እንደተመለሱ ሲሆን፣ የቡድን ሰባት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ፣ “አሁኑኑ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ” ጥሪ አድርገዋል።
ሚኒስትሮቹ ባወጡት መግለጫ፣ “በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞችና ጋዜጤኞች መታሰራቸውም፣ በጽኑ እንዳሳሰባቸው ገልጸው፣ ሩስያ ብሄራዊና አለም-አቀፍ ግዴታዋን በማክበር፣ እአአ ባለፈው ጥር 23 የሰላማዊ መሰባሰብ መብታችድውን በመጠቀማቸው የታሰሩትን እንድትፈታ ጥሪ ማድረጋቸውን፣ ርዕሰ-አንቅጹ ጠቁሟል።
ፖሊሶች የመናገር መብታቸውን በተገበሩ ሰዎች ላይ፣ ሀይል መጠቀማቸው ተቀባይበት የለውም። ይህ ድርጊት ለተቃዋሚዎች፣ ለሲቪሉ ማህበረሰብ፣ ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ሩስያ ላሉት ነጻ ድምጾች፣ ምህዳሩ የጠበበ መሆኑን ያሳያል ሲል፣ የቡድን ሰባት መገለጭ ማስገንዘቡን፣ ርዕሰ-አንቀጹ አውስቷል።
አለክሰይ ናቫልኒ ባለፈው ነህሴ ወር፣ ኖቪቾክ ቡድን በተባለው የነርቭ ኤጀንት ዝርያ ተመርዘው፣ ግድያ ተሞክሮቻቸው እንደነበር፣ ኖቪቾክ ግሩፕ የተባለው፣ በሶቭየት ህብረት አገዛዝ ወቅት የተሰራ፣ የኬሚካል መሳርይ መሆኑን ርእሰ-አንቀጽ ጠቁሟል።
የቡድን ሰባት ሚኒስትሮች ታድያ፣ ማንኛውንም አይነት ኬሚካል መሳርያ መጠቀም፣ አለም አቀፍ ደንብን የሚጻረር በመሆኑ፣ ተቀባይነት የለውም ማለታቸውንና የሩስያ ባለስልጣኖች፣ በጉዳዩ ለይ ምርመራ እንዲያካሄዱ፣ ሩስያ በኬሚካል መሳራያ አጠቃቀም ውል ላይ ያላትን ግዴታ መሰረት በማድረግ፣ ተአማኒ ማብራሪያ እንድትሰጥ እንጠይቃለን ማለታቸውን፣ ርዕሰ-አንቀጹ ገልጿል።
በተቃዋሚ ፖለቲከኛ ላይ ኬሚካል መሳርያ መጠቀም፣ በዛም ላይ የናቫልኒን መታሰር፣ ሩስያ ውስጥ ዲሞክራሲን፣ ነጻ ድምጾችንና የፖለቲካ ብዘሀነትን በበለጠ የማሰናከል ተግባርን ያባብሳል።
ሩስያ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶችን አስመልክቶ፣ በአለም አቀፍ ስምምነት መሰረት፣ ያላትን ግዴታ እንድትፈጽም። በግዛትዋ ያሉትን ሰዎች ሁሉ የመናገር ነጻንትን ላካተቱ መብቶች ዋስትና እንድትሰጥ፣ ቡድን ሳባት አሳስቧል።
ዩናይትድ ስቴትስና የቡድን ሰባት አጋሮችዋ፣ የኬሚካል መሳርያ ውልን ለማክበር ቁርጠኛች ናቸው። ሩስያ ውስጥ ዲሞክራሲና የህግ ተገዢነት እንዲኖር፣ ሰብአዊ መብት እንዲከበር ለመደገፍ፣ ለሩስያው ሲቪል ማህበረሰብ
ያላቸውን ድጋፍ ለማጠናከርም ቁርጠኞች ናቸው ሲል፣ የዕለቱ ርዕሰ-አንቀጽ ሃተታውን አብቅቷል።