Accessibility links

Breaking News

አለም አቀፍ የብርታት ሴቶች ሽልማት


የዚህ ዓመቱ የብርታት ሴቶች ሽልማት፣ ለ21 ሴቶች ተሰጥቷል። ከሱም ሰባቱ አፍጋኒስታን ውስጥ በለይቶ ማጥቃት የተገደሉ ናቸው ሲል፣ የዛሬው ርዕሰ-አንቀጽ ሀተታውን ይጀመራል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በተደረገ፣ ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን በተገኙበት፣ የሽልማቱ ስነ-ሰርአት ባሰሙት ንግግር፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለ15 ዓመትት ያህል ሰላምና ፍትህ እንዲኖር፣ ሰብአዊ መብትና የጾታ እኩልነት እንዲከበር በሚያደርጉት ጥረት፣ ልዩ ብርታትና የአመራር ብቃት ላሳዩ፣ በአለም ዙርያ ላሉ ሴቶች፣ አለም አቀፍ የብርታት ሴቶች ሽልማት ሲያበርክት መቆየቱን ገልጸዋል።

የቤላሩስ ተወላጅ ማሪያ ካለስኒካቫ ከተሸላሚዎቹ ሴቶች መካከል ናቸው። በቤላሩስ ለ26 አመታት ያህል በስልጣን ላይ ባለው፣ የአለክሳንደር ሉካሸንኮ አገዛዝ ላይ፣ እሳቸውና ተባባሪዎቻቸው ታሪካዊ የሆነ ትግል ሲያካሄዱ ቆይተዋል። ከአጨቃጫቂው ምርጫ በሁዋላም፣ ለሚገጥማቸው እስራት በብርታት ተጋፍጠዋል።

ፎዮ ፎዮ ኦንግ በርማ ውስጥ ለመሪነት በማደግ ላይ ያሉ ሴት ናቸው። ዘ ዊንግስ ተቋም የተባለው ድርጅታቸው፣ ወጣቶች በተለያዩ የዘርና የሃይማኖት ቡድኖች መካከል እንዲለዋወጡ በማድረግ ያገናኛል። ለሰላም ግንባታና አእርቅም ይሰራል።

ሌላዋ ተሸልሚ ማክሲሚለን ንጎ እምቤ፣ የካሜሩን ተወላጅ የታወቁ የሰብአዊ መብት ጠበቃ ናቸው። ለአክቲቪስቶች ጥብቅና በመቆማቸው እስራት ገጥሟቸዋል። ለሰብአዊ መብት በመቆም፣ ከሲቪል ማህበርሰብ ጋር ሆነው ድምጻቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። በካሜሩን የሚካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነት፣ መፍትሄ እንዲያገኝ በሚያደርጉት ጥረት፣ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለዋል።

ቻይናዊትዋ ዋንግ ዩ፣ በሀገሪቱ ከታወቁት፣ የሰብአዊ መብት ጠበቆች አንዷናቸው። ለአክቲቪስቶች ጥብቅና በመቆማቸው፣ እስራት ገጥሟቸዋል።

የኮንጎ ዲሞክራስያዊት ሪፑብሊክዋ ጁልያን ሉሰንጅ፣ የወሲብ ጥቃትን በመታገል የታወቁ አክቲቪስት ናቸው።

ሌሎቹ አለም አቀፍ የብርታት ሴቶች ሽልማት ያገኙት ሴቶች፣ የኮሎምቦዋ ማየርሊስ አንጋሪታ፣ የጓተማላ ዳኛ ኤሪካ አይፋን፣ ከኢራን ሾህሬህ ባያት፣ ከኔፓል ሙስካን ኻቱን፣ ከሶማልያ ዛህራ ሞሐመድ እህመድ፣ከስፓኝ ሲስተር አሊሽያ ቫካስ ሞሮ፣ ከሽሪላንካ ራኒታ ጋናራጃ፣ ከቱርክ ካናን ጉሉ፣ ከቬንዙየላ ደግሞ አና ሮዛርዮ ኮንትሬራስ መሆናቸውን ርዕሰ-አንቀጹ ዘርዝሯል።

ብዙውን ጊዜ “ለሰብአዊ መበት በደል ተጋላጭ የሚሆኑት ሴቶችና ልጃገረዶች ናቸው” ሲሉ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን አስገንዝበዋል።

“የሴቶችና የልጃገረዶች የእኩልነት መብት እንዲሁም ክብር የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የሆነውም ለዚህ ነው። የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያችንን የሴቶችና የልጃገረዶች መብትንና የሚያስፈልግዋቸውን ነገሮች አሳቤ ውስጥ አስገብተን ስንቀይስ ፖሊሲያችን የተሻለ ውጤትና ስብእና ይኖረዋል። በሰዎች ህይወትም ዘላቂ ለውጥ ማምጣቱ አይቀርም።” ብለዋል።

ብሊንከን ለተሸላሚዎቹ ባደርጉት ንግግር፣ “አለማችን የተሻለ ፍትሃዊ፣ የተረጋጋች፣ ሰላማዊና ነጻ እንድትሆን እያደርጋችሁ ነው።” ዩናይተድ ስቴተስ እናንተን በመርድትዋ ኩራት ይሰማታል” ማለታቸውን በመጥቀስ፣ የአለቱ ርዕሰ-አንቀጽ፣ ሀተታውን አብቅቷል።

XS
SM
MD
LG