Accessibility links

Breaking News

የህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለፍትህ ሽማልት ፕሮግራም፣ አድናን አቡ ዋሊድ አል ሳ ኻራዊ፣ ወይም አቡ ዋሊድ በመባል የሚታወቀውን ሰው በመለየት፣ ወይም፣ ያለበትን አድራሻ በመጠቆም ያመላከተ ሰው፣ እስከ 5ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ወረታ ይከፈለዋል፣ ይላል የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ ጽሁፉን ሲጀምር፡፡

ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠል፣ አይሲስ ጂ ኤስ ዋና መሠረቱን ያደረገው፣ ማሊ ውስጥ፣ በማሊና ኒጀር ወሰን አካባቢ፣ መሆኑን ይገልጻል፡፡ እኤአ፣ ግንቦት 2015፣ ከአይሲስ ጋር፣ አጋርነቱን የገለጸ መሆኑንም ያስረዳል፡፡ በመቀጠልም፣ በአቡ ዋሊድ የሚመራው ይህ አሸባሪ ቡድን፣ በጥቅምት 4/2017፣ ኒጀር ውስጥ፣ በማሊ ወሰን አቅራቢያ በሚንቀሳቀሰው፣ በዩናትይትድ ስቴትስ እና ናይጄሪያ የጋራ ቃኚ ጦር ላይ፣ ጥቃት በመሰንዘር፣ አራት የዩናይትድ ስቴትስ እና አራት የናይጄሪያ ወታደሮችን ገድሏል” ሲል ርዕሰ አንቀጹ አስረድቷል፡፡

እኤአ ግንቦት 16/2018 ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ምኒስቴር አቡ ዋልድን በማዘዣ ትዕዛዝ 13224 መሠረት፣ በልዩ ዓለም አቀፍ አሸባሪነት ተለይቶ እንዲታወቅ የተፈረጀ መሆኑንም ርዕሰ አንቀጹ ይገልጻል፡፡ በተመሳሳሳይ ሁኔታም፣ አይሲስ ጂ ኤስ በስደትና ዜግነት 219 ድንጋጌ መሠረት፣ በውጭ አገር፣ የሽብር ድርጅትነት የተፈረጀ መሆኑንንም፣ ርዕሰ አንቀጹ አስታውሷል፡፡

ለፍትህ ፕሮራግም የሚሰጠው ሽልማት፣ በዩናይትድ ስቴት የውጭ ጉዳይ ምኒስቴር፣ የዲፕሎማቲክ ደህነንት አገልግሎት የሚተዳደር መሆኑንም ርዕሰ አንቀጹ ገልጿል፡፡ ከተመሰረተበት እኤአ 1984 ጀምሮ ፕሮግራሙ፣ ሽብርተኞችን ወደ ፍርድ ለማምጣትም ሆነ የዓለም አቀፍ ሽብርተኞች ያቀዱትን የሽብር አደጋዎችን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ ጠቃሚ መረጃዎችን ላቀበሉ 100 ለሚደርሱ ሰዎች ወደ 150 ሚሊዮን ዶላር የተከፈለ መሆኑንም ርዕሰ አንቀጹ አስረድቷል፡፡

በመቀጠልም፣ አቡ ዋልድ አል ሰኻ ራዊን አስመልክቶ የተሻለ መረጃ ያለው ማንኛውም ሰው /Rewards for Justice/ የሚለው ድረ ገጽ ወይም /website/ ማለትም /www.rewardsforjustice.net; ላይ በመሄድ ወይም በኤሜል አድራሻ info@rewardsforjustice.net; መልዕክት በመላክ፣ ወይም በየአቅራቢያዎቹ ባሉ የአሜሪካ ኤምባሲ ወይም ቆንስላዎች በመሄድ፣ ኢንፍሮሜሽን ማቀበል የሚቻል መሆኑን፣ ርዕሰ አንቀጹ አስታውቋል፡፡

በመጨረሻም ሁሉም መረጃዎች አሰተማማኝና በጥብቅ ሚስጥር የሚያዙ መሆናቸውን በመግለጽ ርዕሰ አንቀጹ ጽሁፉን ደምድሟል፡፡

XS
SM
MD
LG