Accessibility links

 
በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛትና ብሔራዊ አንድነት ላይ የተጋረጡ አደጋዎች
Breaking News

በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛትና ብሔራዊ አንድነት ላይ የተጋረጡ አደጋዎች


የኤርትራ ወታደር ዩኒፎርም የለበሱ አዲግራት ከተማ አቅራቢያ
የኤርትራ ወታደር ዩኒፎርም የለበሱ አዲግራት ከተማ አቅራቢያ

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛትና ብሔራዊ አንድነት ላይ የተጋረጡ አደጋዎች እንደሚያሳስቡት በመግለፅ የዛሬው ርእሰ አንቀፅ ሐተታውን ይጀምራል።

ከእነዚህ ከተደቀኑ አደጋዎች አንዱ ደግሞ በትግራይ ክልል ውስጥ ያለው ቀውስ ነው - ይላል።

የትግራይ ሕዝብ ከፍተኛ በሆነ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እና በደሎች እየተሰቃየ ነው። ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ሰዎች ደግሞ የምግብ ዋስትና ያስፈልጋቸዋል። ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ በአስቸኳይ የሚያስፈልጉ የሰብዓዊ እርዳታዎች በኢትዮጵያና በኤርትራ ወታደሮች እንዲሁም በሌሎች ታጣቂ ኃይሎች እንዲታገዱ ተደርገዋል ይላል።

“ዩናይትድ ስቴትስ ግድያዎችን፣ ማፈናቀሎችን፣ ሥር የሰደዱ የፆታ ጥቃቶችንና ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና በደሎችን እጅግ አጥብቃ ታወግዛለች፡፡” ሲሉ በቅርቡ ባወጡት መግለጫ የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፤ “ትግራይ ውስጥ የውኃ ምንጮች፣ ሆስፒታሎች እና የህክምና ተቋማትን ጨምሮ የወደሙት የሰላማዊ ዜጎች ንብረቶች ሁሉ በእኩል አሳዝነውናል።” ማለታቸው በርእሰ አንቀፁ ላይ ተጠቅሷል።

“የኢትዮጵያ መንግሥት በሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ጥቃቶቹ ተሳታፊ የሆኑትን ሁሉ ተጠያቂ በማድረግ፣ የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት በመጠበቅም ሆነ የሰብአዊ እርዳታው ተደራሽነት እንዲኖር በማድረግ ሕዝባዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣም የአሜሪካ መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል” ይላል ርእሰ አንቀጹ።

ብሊንከን "ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጥረቶች ቢደረጉም፣ በትግራዩ ግጭት ተሳታፊ የሆኑ ወገኖች ግን ግጭቱን ለማቆምም ሆነ ፖለቲካዊ ቀውሱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የወሰዱት፣ ይህ ነው የሚባል ምንም ዓይነት እርምጃ" የለም ብለዋል፡፡

“የኤርትራ መንግሥት በይፋ የገባውን ቃል ጠብቆ ወታደሮቹን ዓለም ወደሚያወቀው የኤርትራ ግዛት ክልል እንዲመልሳቸው እንጠይቃለን” በማለት ጥሪያቸውን ያቀረቡት አንተኒ ብሊንከን ይህ የማይሆን ከሆነና በክልሉ የሚካሄደው ግጭትና ጠብ አጫሪነቱ በአስቸኳይ ካልቆመ፣ የሚያስፈልገውን አጣዳፊ የሰአብዊ እርዳታ በስፋት ማዳረስ ስለማይቻል አሁን የሚታየው የምግብ እጥረት ወደ ረሀብ አደጋ ሊያመራ ይችላል” በማለትም በአካባቢው ተደቅኗል ስላሉት አደጋ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ካለው አስከፊ ሁኔታ አንፃርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አንተኒ ብሊንከን የቪዛ እቀባ መጣሉን ይፋ ባደረጉበት ወቅት “በትግራይውስጥ ያለው ቀውስ እንዲፈጠርም ሆነ እንዲወሳሰብ በማድረግ ተጠያቂ በሆኑ ግለሰቦች፣ በአሁኖቹና በቀድሞዎቹ የኢትዮጵያና ኤርትራ መንግሥት ባለሥልጣናት፣ ወታደራዊ የደኅንነት አባላት፣ እንዲሁም የአማራ ክልል ኃይሎችና መደበኛና መደበኛ ላልሆኑ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/ አባላት፣ የቪዛ ማዕቀብ እንዲደረግ የተወሰነ መሆኑን አስታውቃለሁ" ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንተኒ ብሊንከን፣ የቪዛው ማዕቀብ በኢትዮጵያ ትግራይ ውስጥ ባለው ህዝብ ላይ በተፈጸመው ያልተገባ ጥቃት የተሳተፉ ወይም በደል የፈጸሙ፣ በክልሉ የሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እንዳይደርስ ያደናቀፉትንም ሁሉ የሚመለከት መሆኑን ገልጸው እቀባው በዚህ ድርጊት የተሳተፈውን ሰው የቅርብ ቤተሰቦችንም ሊጨምር ይችላል በማለት አስረድተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብሊንከን ሌሎች መንግሥታትም ዩናይትድ ስቴትስ የወሰደችውን አቋም እንዲደግፉና እንዲቀላቀሉ ጥሪአቅርበዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ዩናይትድስቴትስ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የኢኮኖሚና የደኅንነት ነክ እርዳታዎች ላይ መጠነ ሰፊ የሆኑ ገደቦችን አስቀምጣለች።

ሚኒስትሩ አያይዘውም “በሰዓብአዊ እና ወሳኝ በሆኑ ዘርፎች የምንሰጠውን እርዳታ እንቀጥልበታለን” ብለዋል፡፡

ኤርትራን በሚመለከትም “ዩናይትድ ስቴትስ ለኤርትራ እንዳይሰጡ የወሰነቻቸውን መጠነ ሰፊ የእርዳታ ማዕቀበኞችን አሁንም ትቀጥልበታለች” በማለት ያለውን አቋም ገልጸዋል፡፡

ትግራይ ውስጥ ያለው ቀውስ እንዲወገድ፣ ኢትዮጵያውያን እርቅና ውይይት አድርገው አሁን የገጠማቸውን መከፋፈል እንዲያስወግዱ ለመርዳት ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፏን ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኗን በመግለፅ ርእሰ አንቀፁ ተደምድሟል።

ኤርትራን በሚመለከትም “ዩናይትድ ስቴትስ ለኤርትራ እንዳይሰጡ የወሰነቻቸውን መጠነ ሰፊ የእርዳታ ማዕቀበኞችን አሁንም ትቀጥልበታለች”በማለት ያለውን አቋም ገልጸዋል፡፡

ትግራይ ውስጥ ያለው ቀውስ እንዲወገድ፣ ኢትዮጵያውያን እርቅና ውይይት አድርገው አሁን የገጠማቸውን መከፋፈል እንዲያስወግዱ ለመርዳት ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፏን ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኗን በመግለፅ ርእሰ አንቀፁ ተደምድሟል።

XS
SM
MD
LG