Accessibility links

Breaking News

የፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ንግግር


ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ንግግር ባደረጉ ወቅት
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ንግግር ባደረጉ ወቅት

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ባሰሙት ንግግር የዓለም ማኅበረሰብ በግዙፍ ዓለማቀፍ ትግል ውስጥ መሆኑን ማስገንዘባቸውን በማውሳት ርዕሰ አንቀጹ ሃተታውን ጀምሯል።

"በዓይን የማይታየውን ጠላት ብርቱ ፍልሚያ ገጥመነዋል፤ እርሱም በ188 ሃገሮች ለቁጥር የሚያዳግት ህዝብ የገደለው የቻይናው ቫይረስ ነው" ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ አለ ጹሁፉን ሲቀጥል ዩናይትድ ስቴትስ ኮቪድ አስራ ዘጠኝን ለመዋጋት ብርቱ እንቅስቃሴ አድርጋለች። ለህሙማን የመተንፈስ አጋዥ መሳሪያዎችን ለሌሎችም ለሚያስፈልጋቸው ሃገሮች መለገስ እንዲቻል ተረፍረፍ አድርጋ አምርታለች። አዋጭ የሆኑ መድሃኒቶችም በመስራት ላይ ነች ብሏል።

ባሁኑ ጊዜ የመጨረሻ ደረጃ የሰው ላይ ሙከራ ላይ ያሉ ሦስት የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶች ያሉ መሆኑን ፕሬዚዳንት ትረምፕ መናገራቸውን ርዕሰ አንቀጹ ጠቅሶታል።

"ክትባቱን እናከፋፍላለን፣ ቫይረሱን እናሸንፈዋለን፣ ዓለማቀፉን ወረርሺኝ እናስወግደዋለን፤ እናም እስካሁን ታይቶ የማያውቅ አዲስ የብልጽግና የትብብር እና የሰላም ምዕራፍ እንጀምራለን" ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ለመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ባሰሙት ንግግራቸው ቻይና በፈጸመቻቸው ተግባሯ በተጠያቂነት መያዝ እንዳለባት አስገንዝበዋል።

"ቫይረሱ በተቀሰቀሰባቸው የመጀመሪያዎቹ ቀናት ቻይና የሀገር ውስጥ በረራዎቹዋን ዘጋችና ቫይረሱ ዓለም ላይ እንዲሰራጭ ወደውጭ የሚጓጉዝ በረራዎች ፈቀደች፤ የቻይና መንግሥት እና የዓለም የጤና ድርጅት (ያው ቻይና እንደምትቆጣጠረው የታወቀ ነው) በሃሰት ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው እንደሚዛመት ማስረጃ የለም” ብለው ተናገሩ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻይናን በተፈጥሮ አካባቢ ላይ በምታደርሰው ጥፋትም ተጠያቂ ሊያደርጋት ይገባል ሲሉ ፕሬዚዳንት ትረምፕ ማሳሰባቸውን ርዕሰ አንቀጹ ጠቅሷ።

"ቻይና በየዓመቱ ብዙ ሚሊዮን ቶን ፕላስቲክ እና ቆሻሻ ውቅያኖሶች ውስጥ ትደፋለች፥ በሌሎች ሃገሮች የባህር ክልል እየገባች ከመጠን አልፋ አሳ ታጠምዳለች፥ ብዛት ያለው የባህር ቅሪተ አካል ክምችት ታወድማለች፥ ከማናቸውም ሌላ ሃገር የበለጠ ብዛት ያለው መርዛማ ሜርኩሪ ነው ወደከባቢ አየሩ የምትለቀው፤ ከቻይና የሚወጣው የካርቦን ልቀት ከዩናይትድ ስቴትስ የሚወጣውን በዕጥፍ ገደማ ይበልጣል ፥ አሁንም እየጨመረ ነው" የተባበሩት መንግሥታት ውጤታማ ድርጅት ለመሆን ከፈለገ በዓለም ላይ ባሉት ተጨባጭ ችግሮች ላይ ማትኮር ይኖርበታል ሲሉ ፕሬዚደንት ትረምፕ አሳስበዋል።

ከእነርሱም መካከል ሽብርተኝነት፥ ሴቶችን መጨቆን፥ በግዳጅ ማሰራት፥ ሱስ አስያዥ ዕጾች እና መድሃኒቶችን ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ማዘዋወር፥ ሰዎችን ለወሲብ መጠቀሚያነት በድብቅ ማጓጓዝ፥ ሰዎችን በሃይማኖታቸው ምክንያት ማሳደድ ፥ በሚኖሩበት አካባቢ በሚከተሉት ሃይማኖት ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ማህበረሰቦችን ከቀያቸው ማስወጣት የመሳሰሉት መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ትረምፕ መዘርዘራቸውን ጠቅሶ ርዕሰ አንቀጹ ጽሁፉ አብቅቷል።

XS
SM
MD
LG