Accessibility links

Breaking News

የማይነጣጠሉት መብቶችና አስፈላጊነታቸው


The Committee of Five present their work, the first draft of the Declaration of Independence, in June 1776, from John Trumbull’s 1819 painting.
The Committee of Five present their work, the first draft of the Declaration of Independence, in June 1776, from John Trumbull’s 1819 painting.

የአሜሪካ መሥራች አባቶች የነፃነት አዋጁን ሰነድ ሲያዘጋጁ የማይነጣጠሉ መብቶችን የመኖር የነፃነት እና ደስታን የመሻት አይነጠሌ መብቶች ሲሉ ገልፀዋቸዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖሊሲ ዕቅድ ቀረጻ ዳይሬክተር ፒተር በርኮዊትዝ እነዚህ የሰው ልጅ ሁሉ በሰውነቱ የተላበሳቸው ናቸው ዛሬ ሰብዓዊ መብቶች ስንል እነሱን ማለታችን ነው ሲሉ ማስገንዘባቸውን በመግለፅ የዛሬ ርዕሰ አንቀጽ ጹሁፉን ጀምሯል።

እነዚህ መብቶች ደግሞ አሉ አስከትለው በሃገር ውስጥ የአሜሪካውያንን መብቶች ብቻ ለማስከበር የቆሙ ሳይሆኑ የትክክለኛ የውጭ ፖሊሲያችንም መሰረት ናቸው።

በ1948 በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ዓለምቀፍ ድንጋጌ እንዲጸድቅ የተደረገውን ትግል በመራንበት ጊዜም ተሟግተንላቸዋል፤ ከሁለቱም የፖለቲካ ፓርቲዎች ለነዚህ መብቶች ከበሬታ የተሟገቱ ፕሬዚዳንቶች አሉ፤ ሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ በሰውነቱ ክብር ይገባዋል የሚለው ዕምነት አሜሪካ የቆመችበት መሰረት አካል ነው።

የውጭ ጉዳይ ማይክ ፖምፔዎ ልዩ ኃላፊነት የተሰጠው የማይነጣጠሉ መብቶች አጥኚ ኮምሽን ከአንድ ዓመት በፊት ማቋቋማቸውን ዳይሬክተር በርኮዊትዝ የተናገሩትን ርዕሰ አንቀጹ በመጥቀስ ይቀጥላል።

"የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዎ አሜሪካ በውጭ ፖሊሲዎቹዋ፥ የምስረታዋ ሰነዶች በሆኑት-- በነጻነት አዋጁ እና በህገ መንግሥቷ ውስጥ በፅናት የቆመችላቸውን የሰብዓዊ መብቶች እንዲፈትሹ መሰረቱንም እንዲያጠናክሩ የኮሚሽኑን አባላት ጠይቀዋቸዋል።

በ1948 በፈረምነው የሰብዓዊ መብቶች ዓለምቀፍ ድንጋጌ መሰረት አሜሪካ ለሰብዓዊ መብት ከበሬታ ያላት የፀና ቁርጠንነት በህገ መንግሥታዊ ባህላችን ውስጥ የሰረፀ መሆኑን እንድንረዳው እንዲያግዙም ጭምር ርዕሰ አንቀጹ በመቀጠልም ዩናይትድ ስቴትስ ከእያንዳንዱ ሃገር ባላት ግንኙነት ውስጥ ሁሉ እነዚህ የማይነጣጠሉት መብቶች ቀጥተኛ ሚና ያላቸው መሆኑንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖሊሲ ዕቅድ ዳይሬክተሩ አስረድተዋል ብሉዋል።

ምሳሌ ለመጥቀስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዎ ሙስሊም ዊገሮች በቻይና ማጎሪያ ካምፖች መታሰራቸውን በተደጋጋሚ አውግዘዋል፥ በ1980ዎቹ ሮናልድ ሬገን በሶቪየት ህብረት በየእስር ቤቱ ጭካኔ በተመላበት አኳሃን ስለታሰሩ ተቃዋሚዎች ሰብዓዊ መብት ተሙዋግተዋል።

ይህ አስተዳደርም የራሱዋን ዜጎች አፍና የምታሰቃየውን የኢራን እስላማዊ ሪፖብሊክ እንደተጋፈጣት የምናየው ነው፤

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መሰረቱ ሙሉ በሙሉ ሰብዓዊ መብት ብቻ አለመሆኑ ዕውነት ቢሆንም የሰብዓዊ መብት ከበሬታ የውጭ ፖሊሲያችን ቁልፍ አካል ነው በማለት የዛሬው ርዕሰ አንቀጽ ጽሁፉን አብቅቷል።

XS
SM
MD
LG